2013-05-27 17:58:55

ትርፍ ለማግኘት ለሚደረገው አምልኮ ንዋይን እምቢ በማለት ለአጋርነት ኅብረተሰባዊ ቦታ እንደሚያገኝ ማድረግ አለብን፤


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ባለፈው ቅዳሜ ቸንተሲሙስ አኑስ ፕሮ ፖንተፊቸ በሚባለው ተቅዋም በዝመናችን ስላለው ምጣኔ ሃብታዊ ቀውስና ሥራ አጥነት ለመያየት ባዘጋጀው ውይይት ለተሳተፉት በቅዱስ ጴጥሮስ ተቅብለው ባነጋገሩበት ወቅት “ትርፍ ለማግኘት ለሚደረገው አምልኮ ንዋይን እምቢ በማለት ለአጋርነት ኅብረተሰባዊ ቦታ እንደሚያገኝ ማድረግ አለብን፤ የዕለት እንጀራ ለማግኘት እስካለመቻል ድረስ የሚያደርገን የዘመናችን የምጣኔ ሃብትና ገንዘብ አካሄድ የባሰው ቍሳዊ ድህነት ነው ምክንያቱም የሰው ልጅ የሥራ መብትን ስለሚጥስ ሲሉ” በተለይ የሥራአጥነት ቀውስ ወዲያውኑ መፈታት ያለበት መሆኑን አሳስበዋል፣ “የሥራአጥነት ችግር ማለት ሥራ ማጣትና የነበረህን ሥራ የማጥፋት ሁኔታ በሰፊ የም ዕራብ ሃገሮች እንደበባህር የፈሰሰ ዘይት እየተዛመተ ስትመለከት ያሳስባል የድህነት ድንበሮችም እየተስፋፉ ነው፣ ዕለታዊ እንጀራን ለማግኘት እንኳ የሚያስችል ሥራ ከማጣት የባሰ ቍሳዊ ድህነት እንደሌለም ላስምርበት እወዳለሁ ይህም የሰው ልጅን የሥራ መብት የሚነጥቅ ነው” ሲሉ የዘመናችን ድህነት አሳሳቢነት ከገለጡ በኋላ የጉባኤው ተሳታፊዎች ስመ ጥር ር.ሊ.ጳ ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ የዛሬ 20 ዓመት ተቅዋሙን ሲመሰርቱት አደራ ያሉት የአጋርነት ወይም የትብብር ጉዳይ በማንሳት “አጋርነትን እንደገና መመልከት” በሚል መሪ ሓሳብ ስለነበር ለዚህም ቅዱስነታቸውን የሚከተለውን አስተያየት ሰጥተዋል፣ “እጅግ ድኃ የሆኑ ወገኖችን የመርዳት ቀለል ያለ አካሄድ አይደለም የሚያስፈልገው፤ ነገር ግን የመላው ዓለም አሰራርን ማስተንተን ያስፈልጋል፡ ይህንም የሰው ልጅ መሠረታዊ መብቶች የሁሉም የሰው ልጆች መብቶች በተጨባጭ የሚጠበቁበት መንገድ በማፈላለግ እንዴት አድርጎ ያለውን አሰራርና አመራር ማሳደስና መሻሻል እንደሚቻል ማጤን ያስፈልጋል፣ ይህች በምጣኔ ሃብታዊ የዓለማችን ክፍል ደስ የማትል አጋርነት የምትል ቃል እንደ መጥፎ ቃል ለማለት ያህል መብትዋን ጠብቀን በኅብረተሰባችን ውስጥ ተገቢ ቦታዋን እንድትይዝ ይሁን፣ አጋርነት ወይም ትብብር ትርፍ ነገር አይደለም፤ ኅብረተሰባዊ ምጽዋት አይደለም፤ ኅብረተሰባዊ ዕሴት ነው ስለዚህ ኅብረተሰባዊ ዜግነትዋን ትጠይቀናለች፣ መብትዋ ነውና፣ ሲሉ በዘመናችን ያሉትን የሥልጣን የትርፍ ማግኘት የገንዘብ ጣዖቶች ከሰው ልጅ በላይ ዋጋ አግኝተው የስራና አሰራር ሕግ ሆነው ስለሚታዩ ከሁሉ በላይ ሰብ አዊነትን በማስቀደም የሰው ልጅ ከሁሉ በላይ መሆኑን ማስገንዘብ እንዳለባቸው አደራ በማለት አሳስበዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.