2013-05-22 15:56:06

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ጸሎት ስለ ኦክላሆማ ከተማ


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ትላትና በትዊተር የማኅበራዊ ማገናኛ ድረ ገጽ ባለው የግል አድራሻቸው አማካኝነት በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት በምትገኘው በኦክላሆማ ከተማ የተከሰተው ኃይለኛ አውሎ ንፋስ በሰውና በንብረት ላይ ያስክተለው አቢይ ጉዳት ጠቅሰው፦ “የአደጋው ሰለባ የሆኑት ከ50 በላይ ስለ ሚገመቱ እንጸልይ፣ ገና ስላልተገኙትም እንጸልይ፣ በተለይ ደግሞ ሕጻናትን እናስብ፣ ጌታ ሆይ ጸሎታችን ስማ” የሚል የጸሎት መልእክት ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ ሲያመለክት፣ ይህ በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት በምትገኘው በኦክላሆማ ከተማ በተከስተው በሰዓት ውስጥ 300 ኪሎ ሜርት ፍጥነት ባስመዘገበው ኃይለኛ አውሎ ንፋስ ለሞት የዳረጋቸው ዜጎች ብዛት በውኑ ባይታወቅም እስካሁን ድረስ 20 ሕጻናት የሚገኙባቸው በጠቅላላ 91 ሰዎች ለሞት መዳረጋቸው ለማወቅ ሲቻል፣ ቅዱስ አባታችን ትላትና ጧት በመሩት ምስዋዕተ ቅዳሴ የቀረበው የምህለላ ጸሎት ስለ ተጎዱት ለሞት አደጋ ስለ ተዳረጉት በጠቅላላ ስለ ሁሉም በተከተው ኃይለኛው አውሎ ንፋስ ለተለያየ አደጋ ስለ ተጋለጡን እንጸልይ በሚል በሳቸው በተደገመው ጸሎት መጠቃለሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሳልቫቶረ ሳባቲኖ ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.