2013-05-22 15:49:09

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ፦ ቤተ ክርስቲያን ወደ ፊት እንድትል የምትከተለው ብቸኛው መንገድ የሥልጣን ሳይሆን የአገልግሎት መንገድ ነው


RealAudioMP3 ለአንድ ክርስቲያን ከፍ ማለት እንደ ክርስቶስ ገዛ እራስን ዝቅ ማድረግ ማለት መሆኑ ላይ በማተኮር ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ትላትና ጧት በአገረ ቫቲካን የቅድስት ማርታ የእንግዳ መቀበያ ሕንፃ ባለው ቤተ ጸሎት የቫቲካን ረዲዮ ሠራተኞች የአገረ ቫቲካን መስተዳድር የጎብኚዎችና የመንፈሳውያን ነጋድያን ጉዳይ የሚከታተለው ቢሮ ሠራተኞች በኢየሱሳውያን ማኅበር የሚታተመው ካቶሊካዊ ሥልጣኔ የተሰየመው መጽሔት ዋና አዘጋጅ የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል አባ አንቶኒዮ ስፓዳሮ የአፍቅሮተ ዘ ቤት ካቶሊካዊ እንቅስቃሴ ሊቀ መንበር ማርያ ቮቸና ምክትላቸው ጃንካርሎ ፋለቲ የተሳተፉበት በራዲዮ ቫቲካን ምክትል ዋና አስተዳዳሪ የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል አባ አንድረይ ኮፕሮቭስኪ ተሸኝተው በመሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ ኢየሱስ ስለ ሕማማቱ ሲናገር ደቀ መዛሙርቱ ግን ፊተኛውና ወኃላኛው ማን ይሆን እያሉ እርስ በእርሳቸው ሲከራከሩ እንደነበር የሚያወሳውን የዕለቱ ምንባበ ወንግሌ ተንተንርሰው ባሰሙት ሥልጣናዊ ስብከት፦ “ብዙውን ጊዜ በቤተ ክርስቲያን የሥልጣን እሽቅድድም ይታያል፣ ሆኖም የኢየሱስ ወንጌል የዚህ ዓይነቱ ሹኩቻ ጨርሶ መኖር እንደሌለበት ነው የሚያስገነዝበው። ምክንያቱም እውነተኛው ሥልጣን እራሱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠው አብነት፣ እርሱም የአገልግሎት ሥልጣን ነው” እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ ገለጡ።
“እውነተኛው ሥልጣን እርሱ ኢየሱሱ እንዳደረገው ማለትም ሊገለገል ሳይሆን ሊያገለግል መምጣቱ በተግባር የኖረውና ያስተማርው የአገልግሎት ሥልጣን ነው። ይኽ ደግሞ የመስቀል አገልግሎት ነው። እርሱ በመስቀል ላይ እስከ መሞት ገዛ እራሱን አዋረደ ዝቅ አደረገ፣ ስለዚህ በቤተ ክርስቲያን ወደ ፊት ለማለት የሚመራው መንገድ ከመስቀል መንገድ ውጭ ሌላ መንገድ የለም አይኖርምም፣ ለክርስቲያን ከፍ ማለትና ማደግ ገዛ እራስን ዝቅ ማድረግ ማለት ነው። ይኽ ወርቃማው የክርስትናው መመሪያ ካልተከተልን መቼም ቢሆን ጌታች ኢየሱስ ክርስቶስ ሥልጣን በተመለከተ የሰጠው የቃልና የሕይወት መልእክት ለመረዳት አንችልም” እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዚጠኛ ጂሶቲ አያይዘውም ቅዱስ አባታችን፦ ብዙውን ጊዜ ያሰው ለአንድ አቢይ ኃልፊነት ተሾመ ለአንድ ትልቅ ኃላፊነት በቃች፣ ይኽ ተሾመ ወይንም ማዕርግ ጨመረ የሚል ቃል ቤተ ክርስቲያን የምትገለገልበት ቃል ቢሆንም ሆኖም ቤተ ክስቲያን ይኸንን ቃል ስትጠቀም ከመስቀል ጋር በማያያዝ ነው። ገዛ እራስ ዝቅ በማድረግ የሚጨመረው ማዕርግ እርሱ ነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በበለጠ ለመምሰል የሚያበቃን” እንዳሉ ገልጠዋል።
ቅዱስ አባታችን ያሰሙት ሥልጣናዊ ስብከት ሲያጠቃልሉ፦ “የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መንገድ የአገልግሎት መንገድ ነው። ቅዱስ ኢግንዛዮስ ዘ ለዮላ በመንፈሳዊ ሱባኤ ሰነዳቱ ጌታን መስቀል ስጠኝ ሲል የሚደግመው ጸሎት ይገኛል። ጌታ በማገልገል እንደፈጸመው ሁሉ እኛም እርሱን እንከተል፣ ተከተሉኝ ነው የሚለው። በቤተ ክርስቲያን እውነተኛው ሥልጣን የአገልግሎት ሥልጣን ነው። ለማደግ ዝቅ ማለት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በቃልና በሕይወት ያስተማረን ወርቃማው ደንብ ብቻ ነው ክርስቲያን የሚያደርገን ዝቅ ለማለት እንድንችል ዘቅ የማለት ጸጋ ጌታ እንዲሰጠን እንለምነው። እንዲህ ይሁንልን።” እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቱ ገለጡ።







All the contents on this site are copyrighted ©.