2013-05-21 17:52:03

ጌታ ኢየሱስን በልበ ሙሉነት ለመቀበል ከእመቤታችን ድንግል ማርያም እንማር፣


ይህንን ያሉት ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ የእመቤታችን ድንግል ማርያም ጉልት የሆነውን ወርኃ ግንቦት በማስታወስ እ.አ.አ እፊታችን ግንቦት 31 ቀን በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ጸሎተ መቍጠርያ እንደሚመሩ በማመልከት ትዊተር በተሰኘው የዘመናችን መገናኛ ብዙኃን አማካኝነት በላኩት አጭር መል እክት ነበር፣ የመል እክቱ ይዘት “በልበ ሙሉነት ኢየሱስን በሕይወት ለመቀበል ፍቃደኞች መሆንን ከእመቤታችን ድንግል ማርያም መማር አለብን” ይላል፣ መልእክቱ በአት ፖንቲፈክስ በሚለው የር.ሊ.ጳ የትዊተር የኢንተርነት የመል እክት ሳጽን የሚተላለፍ ሆኖ ከደንበኞቹ በብዛት የሚከታተሉት አንደኛ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ሁለት ሚልዮን አምስት መቶ አሥራ አንድ ሺ ስድስት መቶ ሲሆኑ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ በእስፓኒሽ ቋንቋ ሆኖ ሁለት ሚልዮን ሶስት መቶ ሰባ ሶስት ሺ ሁለት መቶ መሆናቸው ከቅድስት መንበር የወጣ ዜና ያመልክታል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.