2013-05-17 08:58:39

የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ


RealAudioMP3 20ኛ ዓመቱን ያጠናቀቀው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ምክንያት በማድረግ የቫቲካን ረዲዮ በተከታታይ በሥነ አቢያተ ክርስቲያን ጉባኤዎችና የቲዮሎጊያ ሊቅ የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል በአባ ዳርዩዝ ኮውላዝዪክ አማካኝነት የሚያቀርበው ሳምንታዊ አስተምህሮ በመቀጠል፣ ትላንትና አባ ኮዋልዝዪክ ባቀረቡት 26ኛው ክፍለ አስተምህሮ በተአምኖተ እምነት ዘንድ ባለው እንደ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አባላት መጠን በሁለተኛው ክፍል የምንናዘዘው ቅድስት ሥላሴ ላይ በማተኮር፦ የአብ ዘለአለማዊ አንድያ ልጅ በመንፈስ ቅዱስ ሥራ አማካኝነት በቅድስት ድንግል ማርያም ማሕጸን አድሮ ሥጋችን ለበሰ፥ “ከድንግል ማርያም ተወለደ ‘የካቶሊክ እምነት ስለ ማርያም ያለው እምነት መሠረት በክርስቶስ ላይ ያለው እምነት ነው፣ ስለ ማርያም የሚያስተምረውም በበኩሉ በክርስቶስ ላይ ያለውን እምነት በሚገባ ያብራራል’(ቁ. 487)። ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ኢየሱስ ክርስቶስ መለኮታዊ አካል ሁለት ባህርይ ያለው መሆኑ ማለትም መለኮታዊና ሰብአዊ ባህርይ ስትናዘዝና ስታምን ቅድስት ድንግል ማርያም በእውነት Theotokos እመ እግዚአብሔር መሆንዋ ትናዘዛለች (ቍ. 4959 ተመልከተ)። ስለዚህ ስለ ማርያም ስንናገር እግዚአብሔር በተረጋገጠ የታሪክ ወቅት ሰው ሆኖ መምጣቱን ነው የምናረጋግጠው።
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ማርያም ስታከብር ሁሌ ድንግል መሆንዋ በመከተል ነው። የማርያም ተጨባጭና ዘለአለማዊ ድንግልና የሚናዘዝ እምነት ነው። የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ቍ. 496 ስለ ማርያም ድንግልና፥ “ከእምነቷ መሠረት ጀምሮ ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ሥራ ብቻ በድንግል ማርያም ማሕፀን የመፀነሱና ሥጋ ለብሶ የመወለዱን ይህን ታሪክ በማረጋገጥ ቤተ ክርስቲያን እምነቷን ገልጻለች፣ ‘ኢየሱስ ያለ ወንድ ዘር በመንፈስ ቅዱስ ትፀንሰ’። አበው በድንግልና በሆነው ጽንስ ያስተዋሉት የኛን በመሠለው ስብዕና የመጣ በእርግጥ የእግዚአብሔር ልጅ የመሆኑ ምልክት ነው።…።” በመቀጠልም በቍጥር 503፦ “ የማርያም ድንግልና እግዚአብሔር በወልድ ሥጋ በመልበስ ላይ የነበረው ፍጹም ተነሳሽነት ያሳያል” ስለዚህ የእግዚአብሔር ፈቃድና አነሳሽነት የሚያረጋግጥ ነው። በቁ. 505፦ “በድንግልና ስለ ተፀነሰው ኢየሱስ አዲሱ አዳም በእምነት አማካይነት በመንፈስ ቅዱስ የተመረጡ ልጆችን አዲስ ልደት ያስተምራል፣ ‘ታዲያ ይህ ነገር እንዴት ሊሆን ይችላል?’ በመልኮታዊ ሕይወት መሳተፍ ከእግዚአብሔር በመወለድ እንጂ ከአዳም ወይም ከሥጋ ፈቃድ ወይም ከወንድ ፈቃድ አይመጣም።…”። ዮሓ. 1.13፦ “የሥጋ ክብር ከሰው ክብር ሳይሆን ከእግዚአብሔር ነው”
መልአኩ ማርያምን “ጸጋ የሞላሽ ሆይ” በማለት ሰላምታን ያቀርብላታል፣ ቤተ ክርስቲያንም ወደ ምሉእ እውነት በመንፍስ ቅዱስ ተመርታ የዚህ ጸጋ የሞላሽ እውነትን በመረዳት ማርያም ንጽሕትና ድንግል አለ አዳም ሐጢኣት የተንጸነሰች ያላደፈች ኃጢኣት ያልነካት ስትል የማይሻር የእምነት አንቀጽ ለመደንገግ በቅታለች፥ ቍ. 491 ተመልክተ።
በዚህ መልኵ እግዚአብሔር ማርያም መረጠ። ስለዚህ መመረጧ በነጻነት መልስ ለመስጠት አላገዳትም መመረጧ ነጻነቷን አልነጠቀም ይኽም ሉቃን 1፣37-38፦ …እነሆ እኔ የእግዚአብሔር አገልጋይ ነኝ፣ እንተ እንዳልህ ይሁንልኝ” በማለት በሰጠቸው መልስ ያረጋግጥልናል። የእግዚአብሔር ጥሪ ነጻነት የሚጥስ ወይንም የሚነጥቅ አይደለም በማለት ያቀረቡት አስተምህሮ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.