2013-05-17 08:56:04

ብፁዕ ካርዲናል ራቫዚ፦ በእምነትና በሥነ ጥበብ መካከል ውይይት ማነጽ


RealAudioMP3 በኢጣሊያ ቨነዚያ ዘንድሮ እ.ኤ.አ. ከሰኔ አንድ ቀን እስከ ህዳር 24 ቀን 2013 ዓ.ም. በሚከበረው የሥነ ጥበብ 55ኛው መግለጫ የቅድስት መንበር የሥነ ጥበብ ሃብትና ቅርስ ሱታፌ በእምነትና በወቅታዊው ሥነ ጥበብ መካከል ያለው ተወያይ መንፈስ የሚያንጸባርቅ እንደሚሆን የባህል ጉዳይ ተንከባካቢ ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ ካርዲናል ጃፍራንኮ ራቫዚ ሱታፌው በተመለከተ ትላትና በቅድስት መንበር የዜናን ኅትመት ሕንፃ በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ ተገኝተው ከሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ለመረዳት ተችለዋል።
ብፁዕነታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከቱትም፣ በዚህ በአሁኑ ወቅት በእምነትና በሥነ ጥበብ መካከል ተከስቶ ያለው ፍች እርሱም ካለ እምነት ስምምነት የተከሰተውን መለያየትና ፍች ለመጠገን ያግዝ እንደሚሆንና፣ ስለዚህ በእምነትና በሥነ ጥበብ መካከል የተከሰተው ፍች ጨርሶ ግኑኝነቱን የሚክድ አለ መሆኑ አብራርተው፣ በዚህ በቨነዚያ በሚቀርበው የሥነ ጥበብ መግለጫ የቅድስት መንበር ሱታፌ በእምነትና በሥነ ምርምር መካከል ያለው እውነተኛው ውይይት የሚያነቃቃ ነው። ወቅታዊው የሥነ ጥበብ ሰዋስዉ እምነትን የሚያገል ቢመስልም ቅሉ እምነት ለማግለል የሚከተለው ሥልት እምነት የሚገልጥ ሆኖ ነው የሚገኘው፣ ስለዚህ የጥንቱ በእምነትና በሥነ ጥበብ መካከል ያለው ግኑኝነት የሚቀስር መሆኑ ገልጠዋል።
የቨነዚያ በየሁለት ዓመት የሚካሄደው የሥነ ጥበብ መግለጫ ሊቀ መንበር ፕሮፈሰር ፓውሎ ባራታ በዚህ የሥነ ጥበብ መግለጫ የቅድስት መንበር ሱታፌ አስመልከተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፣ የቅድስት መንበር መሳተፍ እጅግ አስፈላጊና የሥነ ጥበብ መግለጫ ሃብታም የሚያደርግ፣ ሥነ ጥበብ መላው ሰው የሚያጠቃልል ይኸንን የሚመሰክር መሆኑ አብራርተዋል።
የቫቲካን ቤተ መዘክር ዋና አስተዳዳሪ ፕሮፈሰር አንቶኒዮ ፓውሉቺ በበኩላቸውም የቅድስት መንበር ሱታፌ በዚህ የሚካኤልአንጀሎ አራት መቶኛው ዝክረ ዓመት በሚታሰብበት ወቅት በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል፣ ሲሉ የቫቲካን ቤተ መዘክር የወቅታዊው ሥነ ጥበብ ሃብት አስተዳዳሪ ሚኮል ፎርቲ የቅድስት መንበር ሱታፌ በዘፍጥረት ቀጥሎ የተከሰተው ውጥንቀጥ ቀጥሎ የተረጋገጠው የአፍዲስ ፍጥረት ክዋኔ አዲስ ተስፋና አዲስ ሰብአዊነት የሚገልጥ የሥነ ጥበብ ሃብት አማካኝነት የሚገለጥ ነው ብለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.