2013-05-13 15:41:25

ብፁዕ አቡነ ቸሊ፦ ቤተ ክርስቲያን በማኅበራዊ ድረ ገጽና ከሁሉም ጋር አብራ ለመጓዝና የጉዞአቸው ተካፋይነቷን ታረጋግጣለች


RealAudioMP3 ትላትና እሁድ በየዓመቱ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አዘጋጅነት 47ኛው ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ቀን ታስቦ መዋሉ ሲገለጥ፣ ቀኑን ምክንያት በማድረግ የመገናኛ ብዙኃን ጉዳይ የሚከታተለው ጳጳሳዊ ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡን ክላውዲዮ ማሪያ ቸሊ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ይኽ 47ኛው ዓለም አቀፍ የመገናኛ ብዙኃን ቀን መሪ ቃል፦ “ማኅበራዊ ድረ ገጽ፣ የእውነትና የእምነት በር፣ አዲስ የአስፍሆተ ወንጌል ሥፍራ” የሚል መሆኑ አስታውሰው። ቅድሱነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በሥነ አኃዝ የተራቀቀው አዲስ የመገናኛ ብዙኃን ሁሉም ማኅበረሰብ የሚገናኝበት ሃሳቡ የሚገልጥበት አዲስና አዳሽ አደባባይ መሆኑና፣ አዲስ ማኅበረሰብ የሚከወንበት ሥፍራ ነው በማለት ገልጠዉት እንደነበርም አስታውሰው፣ ይህ አዲሱ የመገናኛ ሁነት ለቤተ ክርስቲያን አዲስና አቢይ ተጋርጦ ነው። ስለዚህ የዚህ አዲስ መሣሪያ ተጠቃሚነቷ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መልእክት ለሁሉም ለማዳረስ የሚል ዓላማዋ ለማረጋገጥ የሚደግፍ ምስክርነት የምታቀርብበት አዲስ ሥፍራ ነው። ስለዚህ ተጋርጦነቱ አሉታዊ ሳይሆን አወንታዊ ነው። በመሆኑም በዚህ አዲስ መሣሪያ አማካኝነት ሩቅ ለሚገኙት ሁሉ ቅርብ በመሆን ምስክርነት በማቅረብ እንዲሁም እሴቶችን በማነቃቃት የዓለም ማኅበርሰብ ለማነጽ በሚደረገው ሂደት ተቀዳሚ ሚና ትጫወትም ዘንድ እንዳደረጋት ገልጠዋል።
ቤተ ክርስቲያን በአዲስ የማኅበራዊ ድረ ገጽ አማካኝነት የምትሰጠው ምስክርነትም ሆነ የምታቀርበው መልእክትና ሕንጸት ፕሮፓጋንዳዊ ተግባር ወይንም በገበያ የመሳተፉ ምርጫ ሳይሆን፣ ከሁሉም ጋር በመሆን በሕይውት በአዲስ የሕይወት ጎዳና አብራ በመጓዝ የአዲስ ሕይወት መመዘኛ እርሱም በግላዊና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት መካከል ያለው ግኑኝነት ታበሥራለች። ስለዚህ በድረ ገጽ አማካኝነት የቤተ ክርስቲያን ህላዌ ይፋዊ ተግባር የሚከተል ሁሉን ለመምሰል በሚል መሠረት ሥር ወንጌን ማቅረብ ሳይሆን፣ ከኢየሱስና ከወንጌሉ ጋር የተገናኘ ሕይወት የሚለግሰው ለውጥና ይኸንን በተመለከተም ምስክርነት የምታቀርብበት በጌታ የተለወጠ አዲስ ሕይወት የሚገለጥበት መሣሪያ ነው። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በዚህ አዲስ መሣሪያ አማካኝነት ይኸንን ነው የሚፈጽሙት። ማለትም እምነት ተስፋና ፍቅር እንዲሁም በኢየሱስ ማመን ያለው ጸጋ የሌሎች ስቃይና መከራ ተካፋይ በመሆን እውነተኛ ሕይወት ያበሥራሉ ብለዋል።
አስፍሆተ ወንጌልና ወንገላዊ ሕይወት በማኅበራዊ ድረ ገጽ በኩል የሚተካ ሳይሆን ወንጌላዊ ሕይወት የሚመሰከርበት ሩቅ ለሚገኘው በቃለ እግዚብሔር ቅርብ በመሆን ይኽ የሕይወት ቃል በሁሉም እንዲጎላና የሕይወት ትርጉም ለሚሹ ሁሉ የሁሉም ለሁሉም ዋቢ መሆኑ ለማረጋገጥና ለማወጅ የሚያገለግል መሣሪያ መሆኑ አብራርተው የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.