2013-05-10 15:30:08

ዓለም አቀፍ የካቶሊካዊትና የአንግሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የጋራ ድርገት ጉባኤ


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 29 ቀን 2013 ዓ.ም. በብራዚል ሪዮ ደ ጃነይሮ ከተማ በሚገኘው በቅዱስ በነዲክቶስ ገዳም የካቶሊካዊትና የአንግሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ዓለም አቀፋዊ የጋራው ድርገት ያካሄደው ሦስተኛው የጋራው ውይይት እ.ኤ.አ. መጋቢት 8 ቀን 2013 ዓ.ም. መጠናቀቁ ሲገለጥ፣ ይህ በብራዚል የተካሄደው ሦስተኛ መደበኛው የሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን ዓለም አቀፋዊ የጋራው ድርገት ጉባኤ በደቡብ ክፍለ ዓለም ለመጀመሪያ መሆኑም ሲነገር፣ በበርኒንግሃም የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ በርናርድ ሎንግለይና በጉይልፎርድ የአንግሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ክርስቶፈር ሂል በጋራ ሊቀ መንበርነት የተመራ የብራዚል ጉባኤ የዛሬ ሁለት ዓመት በፊት፦ “ቤተ ክርስቲያን ሱታፌ ክልላዊና ኵላዊነት” እንዲሁም “በሱታፌ፣ ክልላዊና ኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ትክክለኛውና ቅነኛው የሥነ ምግባር አስተምህሮ ለይቶ በማጤን መከተል” በሚል ርእሰ ጉዳዮች ተመርቶ የተካሄደው ውይይት በማስቀጠልና በመከተል የጋራ ሰነድ አርቆ ለንባብ ለማብቃት ታልሞ የተካሄደ መሆኑም ከጉባኤው ፍጻሜ ከተሰጠው የጋራው መግለጫ ለመረዳት ተችለዋል።
ጉባኤው የቤተ ክርስቲያን ባህርይና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለውሳኔዎች ተኪዶ የሚያግዘው መንገድና ሁነት ለመለየትና ብሎም ውሳኔ ለማስተላለፍ የሚደግፉት መዋቅሮቿ ጭምር ያለው ቲዮሎጊያዊ አመክንዮ ለመለየት የተካሄደ መሆኑ የገለጠው የጋራው የመግለጫ ሰነድ አክሎ፣ ሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን በተናጥል የሚከተሉትና ስለ ተወያዩበት ቲዮሎጊያዊ መሠረታዊ አመክንዮ ጉዳይ በተመለከተ የሰጡበት ሥልጣናዊ አስተምህሮ በማስደገፍ ይኸንን ጉዳይ የሚነካ ሥነ ምግባራዊ ጥያቄዎች ላይ ያተኮረ የአንድ ቀን ውይይት መካሄዱና ከዚህ ጋር በማያያዝም ሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን በጋራ በተወያዩበት ርእሰ ጉዳይ ሥር የሰጡበት የጋራ አስተያየት በተናጥል ለአቢያተ ክርስትያናቸው እንደሚያስረክቡም ተገልጠዋል።
ሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን ያጠናቀሩት አምስት ውሳኔዎች ላይ በማተኮርም ውይይት በማካሄድ፣ ውሳኔውን ለውኅደት ታቅዶ በሚካሄደው የጋራ ውይይቶቻቸው ዘንድ በአግባብነቱ አያይዞና አሳክቶ ለማስቀመጥ የሚያስችል አስተዋጽኦ ለማጠናቀር እንዲቻልም የድርገቱ አባላት ሰነዳቱን በጥልቀት እንደመረመሩም ከተሰጠው የጋራ መግለጫ ለመረዳት ሲቻል፣ ይህ የጋራው ጉባኤ እ.ኤ.አ. በ2006 ዓ.ም. በአገረ ቫቲካን በቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛና የእንግልጣርና የመላ አንግሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ልኂቅ የበላይ መንፈሳዊ መሪ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ሮዋን ዊሊያምስ መካከል ከተካሄደው የጋራው ግኑኝነት በኋላ ከዚህ ቀደም የነበረው እ.ኤ.አ. በ 1970 ዓ.ም. የጋራው ቀዳሚው ድርገት በማቋቋም ቀጥሎ በ 1983 ዓ.ም. ሁለተኛው የጋራ ድርገት አቁሞ እ.ኤ.አ. በ 16ኛው ክፍለ ዘመን ለመለያየት የዳረገው ማእከላዊ ጥያቄ አጢኖ የተከሰተው ልዩነት አስወግዶ ወደ ነበረው ውኅደት ለመመለስ እንዲቻል የተቋቋመ ሥስተኛው የጋራ ድርገት መሆኑ ሲገለጥ፣ ይህ የጋራው ድርገት ያጋጠመው ውጣ ውረድና ከሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ ቀጥሎ የተጨበጡት አመርቂ ውጤቶች ይኽም እ.ኤ.አ. በ 1971 ዓ.ም. ስለ ቅዱስ ቁርባን በ 1973 ዓ.ም. ስለ ሚሥጢረ ክህነት እ.ኤ.አ. ከ 1976 እስከ 1981 ዓ.ም. የቤተ ክርስቲያን ሥልጣን ርእሰ ጉዳይ ሥር በተደረገ በጋራ ያወጡት ሰነዶች የሚመለከት የሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን ለውህደት ያቀናው የጋራው ውይይት ፈር የሚያስይዝ አወንታዊ ተጽእኖ ያለው ውጤት መረጋገጡም አይዘነጋም።
እንደሚታወሰውም እ.ኤ.አ. በ 1994 ዓ.ም. አንግሊካዊት ቤተ ክርስትያን ሴቶች ለሚሥጢረ ክህነት እንዲሁም በ 2008 ዓ.ም. ሴቶች ለቅብአተ ጵጵስና ከፈቀደችበት ዓመታት ጀምሮ በሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን መካከል ያለው ቲዮሎጊያዊ ልዩነት ከፍ እያለ መምጣቱ ቢታወቅም ቅሉ፣ ይኽ የተከስተው ቲዮሎጊያዊ ልዩነት ሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን በ 2005 ዓ.ም. “ቅድስት ድንግል ማርያም ጸጋና ተስፋ በክርስቶስ” በሚል ሥነ ማርያም ጥናት ላይ ያተኮረ የጋራው ሰነድ ለማጽደቅ አለ ማገዱንም የሚታወስ ነው።
ሌላው የሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን ለውህደት ያቀናው ግኑኝነት የነካው እ.ኤ.አ. በ 2005 ዓ.ም. በአንግሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሴቶች ለሚሥጢረ ክህነትና ለጵጵስና እንዲሁም ሁለት ዓመት ቀደም ብሎ በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት የምትገኘው አንግሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አባል የሆኑት ጳጳስ ግብረ ስዶማዊ ዝምባሌ እንዳላቸው ከገለጡበት ዓመት ወዲህ ግብረ ሶዶማዊ ዝምባሌ ላላቸው ጋብቻ የሚፈቅድ የተደረሰው ውሳኔ ምክንያት የተከሰተው ልዩነት የካቶሊካዊትና የአንግሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ለውኅደት ያቀናው የጋራው ውይይት እጅግ እንደነካውና በሁለቱ አቢያተ ክርስቲያን መካከል ያለው ግብረ ገባዊ ጥያቄ መሠረትም አቢይ ልዩነት እንዳስከተለና በአንግሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የተቀሰቀስው ውስጣዊ አለ መግባባት ምክንያትም ወደ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ለመመለስ የሚሹ የሚያቀርቡት ጥያቄ መሠረት የአንግሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጳጳሳትና ካህናት እንዲሁም ምእመናን የሚያቀርቡት ጥያቄ የሚመለከትና ወደ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን መመለስ ያላቸው ፈቃድ መሠረት ለመቀበል የሚያግዘው እ.ኤ.አ. ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ “Anglicanorum Coetibus- አንግሊካዊ ቡድን” በሚል ርእስ ሥር በ 2009 ዓ.ም. በደነገጉት ውሳኔ መሠረት በእንግልጣር በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት በአውስትራሊያ ውሳኔው መሠረት በማድረግ መደበኛ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ደንብ ተከታታይ አካል እንዲቆም ማድረጋቸውም ይታወሳል።








All the contents on this site are copyrighted ©.