2013-05-03 14:39:49

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ በልባችን ሰላም እንዲሰፍን በቅዱስ ፍራንቸስኮስ ዘአሲዚ አማላጅነት እጸልይ


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ትላትና በአሲዚ ከተማ ከሚገኘው የቅዱስ ፍራንቸስኮ ዘአሲዚ ቅዱስ አጽም ያረፈበት ቅዱስ ሥፍራ በድምጸ ምስል ተቀርጾ በቀጥታ ለሁሉም እንዲታይ በመደረጉ ምክንያት በዚህ የድምጸ መስል መሣሪያ በመጠቀም ቅዱስ ፍራንቸስኮ በልባችን ሰላም እንዲሰፍን አማልድልን በማለት የደገሙት ጸሎት በ"sanfrancesco.org" ድረ ገጽ በኩል ታትሞ መቅረቡ የቅዱስ ፍራንቸስኮ ገዳም የዜናና ኅትመት ቢሮ አስታውቀዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በቅዱስ ፍራንቸሰኮ ገዳም ዘአሲዚ አቃቤ አባ ማውሮ ጋምበርቲና ቅዱስ ፍራንቸስኮ የኢጣሊያ ጠባቂ ቅዱስ የተሰየመው መጽሔት ዋና አስተዳዳሪ አባ ኤንዞ ፎርቱናቶ የተሸኙት የቅዱስ ፍራንቸስኮ ንኡሳን ወንድሞች ማኅበር ጠቅላይ አለቃ አባ ማርኮ ታስካ ትላትና ጧት ተቀብለው እንዳነጋገሩ የቅዱስ ፍራንቸስኮ ገዳመ የዜናና ኅትመት ቢሮ ካሰራጨው ዜና ለመረዳት ሲቻል፣ በተካሄደው ግኑኝነት ቅዱስ ፍራንቸስኮ የኢጣሊያ ጠባቂ ቅዱስ መጽሔት የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸክሶ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ እንዲሆኑ ከተመረጡ በኋላ በሳቸው ታሪክ ላይ ያተኮረ ለንባብ የበቃው የመጽሔት ልዩ ሕትመት ለቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. መለገሱ የገለጠው የገዳሙ የዜናና ኅትመት ቢሮ መግለጫ አክሎ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ለቅዱስ ፍራንቸስኮ ዘአሲዚ ገዳምና ለማኅበሩ አባላት ሐዋርያዊ ቡራኬ ማስተላለፋቸውና የማኅበሩ ወንድሞች ስለ ቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ እንዲጸልዩ አደራ እንዳሉ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.