2013-05-01 15:18:15

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ;


ውድ ወንድሞቼና እኅቶቼ! እንድምን አላችሁ!
ዛሬ እ.አ.አ. የወርኃ ግንቦት መጀመርያ ቀን የቅዱስ ዮሴፍ በዓል ስናከብር በዘልማድ ለእመቤታችን ድንግል ማርያም የተጐለተ ወርኃ ግንቦትንም እናስታውሳለን፣ በዚሁ ግኑኘታችን በኢየሱስ ምድራዊ ሕይወት እንዲሁም በቤተ ክርትያንና በሕይወታችን ዋና ሚና ስለነበራቸው ሁለት አጠር ያሉ ትምህርቶች ለማቅረብ እወዳለሁ፤ አንደኛው ስለሥራ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ስለኢየሱስ የሚናገር አስተንትኖ ይሆናል፣
ኢየሱስ አገር ቤቱ በሆነችው የናዝሬት ከተማ ተመልሶ በቤተ መቅደስ ከወገኖቹ ጋር ስላደረገው ውይይት የሚገልጥ በቅዱስ ማቴዎስ ወንጌል ከተጻፉ ፍጻሜዎች በአንዱ የተመለከትን እንደሆነ ወገኖቹ ስለጥበቡ በማድነቅ “ይህን ጥበብና ተአምራት ይህ ከወዴት አገኘው? ይህ የጸራቢ ልጅ አይደለምን?” (ማቴ 13፤54-55) ብለው ይጠይቃሉ፣ ኢየሱስ በእግዚአብሔር ሥራ ከማርያም በመወለድ በታሪካችን ይገባል፤ በመሀከላችን ይመላለሳል፤ ይህንን ሁሉ ሲያደርግ እንደሕጋዊ አባት በሚንከባከበውና የሥራ ጥበቡን በሚያስተምረው ቅዱስ ዮሴፍ ተሸኝቶ ነው፣ ኢየሱስ በአንድ ቤተ ሰብ እንዲያው ቅድስት ቤተ ሰብ ውስጥ ተወልዶ ከቅዱስ ዮሴፍ የጥርበት ጥበብን በመማር ከእርሱ ጋራ ደግሞ ኃላፊነቱን ድካሙን እና ችግሩን እግኒሁም ከዚሁ ድካም የሚገኘውን እርካታ እያጣጣመ በናዝሬት ከተማ ተወልዶ ይኖራል፣
ይህ ፍጻሜ የሥራ አስፈላጊነትና ክብር ያስረደናል፣ በኦሪት ዘፍጥረት እግዚአብሔር የሰው ልጅን እንደፈጠረና ምድርን እንዲሞላትና እንዲገዛ እንደፈጠረው ይነግረናል፣ ይህ ማለትም ምድርን ሳይበዘብዝ እንዲያፈራትን እንዲጠብቃት በሥራውም እንዲንከባከባት ኃላፊነት እንደተሰጠው ያመልክታል (ዘፍ 1፤28፣ 2፤15 ተመልከት)፣ ሥራ ከእግዚአብሔር የፍቅር ዕቅድ አንድ ክፍል ነው፤ ፍጥረትን ሁሉ ለማፍራትና ለመንከባከብ የተጠራን እና በዚህም ከእግዚአብሔር የፍጥረት ሥራ እንድንተባበር የተጠራን ነን፣ ሥራ ከሰው ልጅ ክብሮች አንዱ ነው፣ ሥራ ክብር ያለብሰናል፣ ሥራው ባከናወና ገናም እየሠራ ካለው ከእግዚአብሔር ጋር እንድንመሳሰል ያደርገናል፣(ዮሐ 5፤17) ማንነታችንና ቤተሰባችንን እንድንጠብቅ ያደርገናል፣ ለአገራችን ዕድገትም አስተዋጽኦ እንድናደርግ ይረዳናል፣ ባለነው ዘመን በተለይ ደግሞ ባሁኑ ጊዜ በብዙ የበለጸጉ አገሮች አጋጥሞ ባለው የምጣኔ ሃብት ቀውስ በሥራ አጥነት ስለሚሰቃዩ በተለይ ደግሞ ወጣቶች ሳስብ በዓለማችን ስለሚካሄደው የግል ጥቅም ሩጫና ማኅበረሰባዊ ኢፍትሓዊነት እንዲታረም እጠይቃለሁ፣
ለሁላቸው ለማቅረብ የምሻው ጥሪም ይህ ነው፤ እያንዳንዳችሁ ለአጋርነትና ለትብብር እንድትተጉ እየጠራሁ ሥራ ለመፍጠር የተቻላችሁን ያህል እንድትጥሩ አደራ እላለሁ፣ ይህ ማለትም ሰብ አዊ ክብርን ማስቀድምና ስለእርሱ ማሰብ ሲሆን ከሁሉ በላይ ለማማጠን የምወደው ተስፋ እንዳትቆርጡ ነው፤ ቅዱስ ዮሴፍ ብዙ ችግር እንደነበረው እሰቡ፤ ሆኖም እምነትን ሳያጠፋ በተስፋ ሁሉንም አሸነፈ ይህንን ያደረገበትም እግዚአብሔር እንዳይተወው በተማመኑ ነው፣ ለሁላችሁም የምጠይቀው በተለይ ደግሞ ለወጣቶች አደራ የምለው በዕለታዊ ተግባሮቻችሁ በሚገባ እንድትጠመዱ ነው፤ ትምህርታችሁና ጥናታችሁ እንዲሁም ከሌሎች ጋር ያላችሁ ግኑኝነትን በማበረታት እርስ በእርሳችሁ እየተራዳዳችሁ በመጓዝ መጻኢ ሕይወታችሁ አሁን በምታደርጉት እንደሚወሰን ታስታውሱ ዘንድ ነው፣ ፍርሓት አይኑራችሁ! አይዞ! ለሥራ ለመስዋዕትነትና ለመጻኢ ሕይወታችሁ አለፍርሓት ተጓዙ፤ ሕያው ተስፋ ይኑራችሁ! በአድማሱ ሁሌ ብርሃን አለና፣
በአሁኑ ግዜ እጅግ ስለሚከብደኝ ሌላ ነገር አንድ ቃል ለመናገር ፍቀዱልኝ፤ “የባርነት ሥራ” ተብሎ ሊጠራ የሚችለው በዘመናችን እየተከሠተ ያለው ሰውን ወደ ባርነት ስለሚጥል ሥራ ነው፣ በመላው ዓለም ስንት ሰዎች ናቸው የዚህ ባርነት ሰለባ ሆነው ያሉ? በዚሁ ሁኔታ ሰዎች የሥራ ባርያዎች ሆነው ይገኛሉ፣ እንደእውነቱ ከሆነ ግን ሰዎች ክብር እንዲኖራቸው አገልግሎት ማበርከት የነበረው ሥራ ነው፣ በእምነት ወንድሞችና እኅቶች ለሆኑና ለባለ በጎ ፈቃዶች ሁላቸው ሰዎችን እንዲህ በሚያገላታ የሥራ ባርነት ሁነኛ እርምጃ እንዲወስዱ እማጠናለሁ፣
ሌላው ሁለተኛ ሓሳቤ ደግሞ በዕለታዊ ኑሮ አችን ስለሚያግጥሙ ጉዳዮች ነው፣ ቅዱስ ዮሴፍና እመቤታችን ድንግል ማርያም በኅብረት የነበራቸው ዋና ነገር አንድ ብቻ ነበር እርሱም ኢየሱስ ነበር፣ እነርሱ በኃላፊነትና በፍቅር ኢየሱስን ይሸኙና ይንከባከቡ ነበር፤ ስለእኛ ሰው የሆነውን ሕጻን ለማሳደግ ሁሉን ነገር በልባቸው እያኖሩ ይሰሩ ነበር፣ ወንጌልን የተመልከትን እንደሆነ ቅዱስ ሉቃስ በወንጌሉ ሁለቲ ይህንን የእመቤታችን ዝንባሌ እንዲያው የቅዱስ ዮሴፍም የሆነው ዝንባሌን እንዲህ ሲል ያመለክታል፤ “እነኚህን ነገሮች እያስተነተነች በልብዋ ታኖረው ነበ” (ሉቃ 2፤19፤51) ይላል፣ ጌታ ኢየሱስን ለመስማት ማስተንተኑን መማር ያስፈልጋል፤ ቀጣይ በሕወታችን መኖሩን መረዳትና ከእርሱ ጋር ለመወያየት አንዴ መቆምና በጸሎት አስፈላጊውን ቦታ መስጠት ያስፈልጋል፣ እያንዳንዳችን እንዲሁም ዛሬ ረፋድ በአደባባዩ በብዛት የምትገኙ እናንተ ወጣቶችም ጭምር ለጌታ የትኛውን ቦታ እሰጣለሁ? ከጌታ ጋር ለመወያየት ምኑን ያህል እቆማለሁ? ብለን መጠየቅ ያስፈልጋል፣ ወላጆቻችን ከሕጻንነታችን ጀምረው በየዕለቱን ቀኑን በጸሎት መጀመርና መፈጸም እንዳለብን አስተምረውናል፣ ይህንን የሚያደርጉት ደግሞ የእግዚአብሔር ጓድኝነትና ፍቅር እንዲሸኘን ሊያስተምሩን ስለፈለጉ ነው፣ በዕለታዊ ሕይወታችን ብዙ ጊዜ ጌታን እናስታውስ፣
ዛሬ የምንጀምረው የግንቦት ለእመቤታችን ድንግል ማርያም የተሰጠ ወር በመሆኑም የመቍጠርያ ጸሎት ምንኛ ያህል አስፈላጊና ቆንጆ ጸሎት መሆኑን ለማሳሰብ እወዳለሁ፣ በሰላመ ቅዱስ ገብርኤል መልአክን ስንጸልይ የኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት ምሥጢርን እናስተነትናለን፤ ምክንያቱም እንደ ድንግል ማርያምና ቅዱስ ዮሴፍ የሕይወቱ አንኳር የያዙ ሁኔታዎችን እናስተነትናለን፤ ጌታ ኢየሱስ የሕይወታችንና የአስተሳሰባችን እንዲሁም የተግባሮቻችን አንኳር እንዲሆን ይሁን፣ በዚሁ ወር ጸሎተ መቁጠርያ በቤተ ክርስትያን በቤተሰቦች እና ጓደኛሞች አብረው ቢጸልዩት እንዴት ቆንጆ በሆነ ነበር፤ ምክንያቱም ጸሎተ መቁጠርያ ለኢየሱስና ለእመቤታችን ድንግል ማርያም የሚቀርብ በመሆኑ ነው፣ በኅብረት የሚደረግ ጸሎት የቤተሰብ እንዲሁም የጓደኛሞች ሕይወትን ያጸናል፤ ከቤተ ሰብ ጋር አብረንና እንደቤተሰብ ለመጸለይ እንማር፣
ውድ ወንድሞችና እኅቶች! ለቅዱስ ዮሴፍና ለእመቤታችን ድንግል ማርያም ዕለታዊ ሕይወታችን ለሚያለብሰን ሓላፊነቶች ታማኞች እንድንሆናን እምነታችንን በዕለታዊ ተግባሮቻችን በታማኝነት እንድንኖር በሕይወታችን ለጌታ ሰፊ ቦታ እንድንሰጥ ስለእርሱ ለማስተንተን አንዴ እንድንቆም እንዲረዱን እንለምናቸው፣








All the contents on this site are copyrighted ©.