2013-04-29 17:28:42

ሁላችን የእግዚአብሔር ሕዳሴን እንድንቀበል የተጠራን ነን፣


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትናንትና እሁድ እኩለ ቀን በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ የንግሥተ ሰማያት ጸሎት ከማሳረጋቸው በፊት በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ ለቅብአ ሜሮን ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ ለመሳተፍ ከመላው ዓለም ከተሰበሰቡ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ቅብዓ ሜሮን ለመቀባት የመጡ ወጣቶች ባቀረቡት አስተምህሮ “ሁላችን የእግዚአብሔር ሕዳሴን እንድንቀበል የተጠራን ነን፣” ሲሉ ካሳሰቡ በኋላ በባንግላደሽ ባንድ የጨርቓ ጨርቕ ፋብሪካ በተነሳው አደጋ ለተጐዱ ወገኖች ቅርበታቸውን ገልጠዋል፣
“በዚሁ ልዩ ጊዜ በባንግላደሽ በተከስተው የአንድ ፋብሪካ መፈራከሽ ሰለባ ስለሆኑት ልዩ ጸሎት ለማሳረግ እወዳለሁ፣ ቅርበቴንና አጋርነቴን በአደጋው ቤተ ሰቦቻቸው ተጐድቶዋቸው በአዘን ለሚገኙ ቤተ ሰቦች እገልጣለሁ፣ የሠራተኞች መብት እንዲጠበቅና ዋስትናቸውም እንዲረጋገጥ ከልቤ ጥልቀት የመነጨ ጥሪን አቀርባለሁ” ሲሉ የተሰማቸውን ሓዘን ገልጠዋል፣
በቅ.ጴጥሮስ አደባባይ ወደ ነበሩ ሰዎች መለስ በማለትም በሕይወት ዘመናችን ውስጥ በመንፈስ ቅዱስ መኖርንና የእግዚአብሔር ሕዳሴን በሕይወታችን መቀበል እንዴት እንደምንችል የምታስተምረን እመቤታችን ድንግል ማርያም ስለሆነች በዚሁ ዕለት ቅብ አ ሜሮን ለተቀበሉት ሁሉ ለእርሷ በማማጠን እንዲህ ብለዋል፣
“እያንዳንዱ ክርስትያን! እያንዳንዳችን የእግዚአብሔር ቃልን ለመቀበል የተጠራን ነን፤ እንዲሁምኢየሱስን በልባችን ውስጥ ለመቀበልና ለሌሎች ለማስፋፋት የጠተራን ነን፣ እመቤታችን ድንግል ማርያም በጽርሐ ጽዮን ከሐዋርያት ጋር መንፈስ ቅዱስ እንዲወርድ ለመነች እኛም ሁሌ በጸሎት በምንተባበርበት ጊዜ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታን ለመቀበልና ከሞት የተነሣውን ኢየሱስ ለመመስከር በዚህችዋ መንፈሳዊት እናት እየተደገፍን ነው፣
“ይህንን በተለይ ለእናንተ ዛሬ ምሥጢረ ሜሮን ለተቀበላችሁ እለዋለሁ፤ ጌታ ለሚጠይቃችሁ ነገር ሁሉ ንቁ እንድትሆኑና በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ለመኖርና ለመጓዝ እመቤታችን ድንግል ማርያም ትርዳችሁ፣
አይዞ! በርቱ! እግዚአብሔር መጥፎ ነገርን ለመቋወምና ወደ ፊት እንድንራመድ ብርታት ይሰጠናል፣ ሲሉ ወጣቶችን አበራትተዋል፣
ቅዱስነታቸው በቅዳሴ ባሰሙት ስብከትም ይህንን ነበር በኃይለ ቃል ተናገሩት “ጌታን መከተል መንፈሱ የሕይወታችን ጨለማ ወገኖች እንዲለውጥ መፍቀድ ማለትም ከእግዚአብሔር ፈቃድ ጋር የማይስማሙ ጠባዮቻችን እንዲሁም ኃጢአቶቻችን እንዲያጥብ መፍቀድ ሲሆን ይህ ግን ብዙ ዕንቅፋቶች እንዳሉ ማለት ከእኛ ውጭ በዓለም በውስጣችንም ሳይቀር በልቦቻችን ይገኛሉ፣ ሆኖም ግን ችግር እና ፈተና ወደ እግዚአብሔር ክብር ለመድረስ በሚደረገው ጉዞ ልክ ለኢየሱስ በመስቀል እንዳጋጠሙት ለእኛም ያጋጥሙናል፤ ፈተናዎቹን ለማሸነፍ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ስላለን አይዞዋችሁ፣ በእምነት ጉዞ አችሁ በጌታ ጽኑ ተስፋ በማኖር በርቱ፣ ብለዋል፣
“ወጣቶች ተጠንቅቃችሁ ስሙኝ! ጉዞ አችሁ አንጻራዊ ይሁን! ይህ ለልባችሁ መልካም ነገር ነው፤ ሆኖም ግን ተቃራኒውን ጐዳና ለመራመድ ብርታት ያስፈልጋል ይህንን ብርታት ደግሞ ጌታ ይሰጠናል፣ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ጓደኝነትን ያላደናቀፍን እንደሆነና ሁሌ ለእርሱ ቦታ የምንሰጥ ከሆነ እንዲሁም ከእርሱ ጋር አንድ ሆነን ከኖርን ሊያስፈሩን የሚችሉ ችግሮችና ፈተናዎች የሉም፤ ይህ ሁሌ እውነት ነው፣ ደካሞች ድኃዎች ኃጢአተኞች ሆነን በሚሰማን ግዜም ሳይቀር ምክንያቱም እግዚአብሔር ለደካማነታችን ኃይል ለድህነታችን ሃብት ለኃጢአታችን ንስሓ ይሰጠናልና ሲሉ አበራትተዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.