2013-04-26 16:04:02

የቅድስት መንበር የዜና ማኅተም ክፍል መግለጫ


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 25 ቀን 2013 ዓ.ም. የቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል ተጠሪ የቫቲካን ረዲዮ ዋና አስተዳዳሪ አባ ፈደሪኮ ሎምባርዲ ከቀትር በኋላ በቅድስት መንበር የተለያዩ አገሮች የውጭ የኅትመትና የቴሌቪዥን ልኡካን ጋዜጠኞች በቅድስት መንበር የዜናና ማኅተም ክፍል በሚገኘው የጉባኤ አዳራሽ ተቀብለው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፦ በዚህ እ.ኤ.አ. በ 2013 ዓ.ም. የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሐዋርያዊ ጉብኝት መርኃ ግብር እ.ኤ.አ. ከሐምሌ 23 ቀን እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2013 ዓ.ም. በብራዚል ሪዮ ደ ጃነይሮ ‘ወደ ዓለም ሕዝብ ሁሉ ሂዱ…የእኔ ደቀ መዛሙርት አድርጉአቸው’ (ማቴ. 28.19) የሚል ቃለ ወንጌል መርህ በማረግ በሚካሄደው ዓለም ዓቀፍ የወጣቶች ቀን ሱታፌ የሚፈጽሙት ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት በስተቀረ በ 2013 ዓ.ም. የሚፈጽሙት ሌላ ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደማይኖር ነው” ብለዋል።
አባ ሎምባርዲ አክለውም፦ “ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ምናልባት በኢጣሊያ አሲዚ ከተማ ሐውጾተ ኖልዎ ያካሂዱ ይሆናል። በዚህ እ.ኤ.አ. በ 2013 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው ቀዳሜ ዓዋዲ መልእክት ይደርሱ ይሆናል። ምክንያቱም ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16 እምነት ማእከል ያደረገ ዓዋዲ መልእክት ሊደርሱ አቅደው ያካሄዱት ጥናት ያካተተ የተዉት የማስታወሻ ሰነድ ያለ በመሆኑ ቅዱስ አባታችን ይኸንን በማጤን የሚደርሱት ዓዋዲ መልእክት እምነት በተሰኘው ርእሰ ጉዳይ ዙሪያ ያተኮረ ሊሆን እንደሚችል ይገመታል” ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ በዚህ እ.ኤ.አ. 2013 ዓ.ም. በዚህ በያዝነው ወር ፍጻሜ ወይንም በግንቦት ወር ቀዳሜ ሳምንት ውስጥ ከሚገኙበት ከካስተል ጋንደልፎ ሐዋርያዊ ሕንፃ በአገረ ቫቲካን ወደ ሚገኘው የባህታውያን ገዳም እንደሚዛወሩ ገልጠው፣ “ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ሁሉም እንደሚያውቀው ከሚኖሩበት በአገረ ቫትካን ከሚገኘው የቅድስት ማርታ ሕንፃ ወደ ሐዋርያዊ መኖሪያ ሕንፃ የመዛወሩ እቅድ ያልቸው እንደማይመስል ነው” ብለዋል።
የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት ጉዳይ ተጠሪ ዶክተር አልበርቶ ጋስባሪ በቅርቡ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በብራዚል የሚያካሂዱት ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት እቅድና ሂደቱንም ጭምር ለይቶ ቅድመ ዝግጅቱ ለማመመላከት በሪዮ ደጃነይሮ የሥራ ጉብኝት አካሂደው መመለሳቸውንም አባ ሎምባርዲ አስታውሰው፣ በሪዮ ደጃነይሮ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በእንኳን ደኃና መጣችሁ የአቀባበል ሥነ ሥርዓት መሠረት በሚፈጸመው በዓል ቀጥለውም በፍኖተ መስቀል ሥነ ሥርዓትና ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን የፍጻሜ ዋዜማ ሥነ ሥርዓትና ቀጥሎም በነገታው የሚቀርበው የበዓሉ ማጠቃለያ መሥዋዕተ ቅዳሴ በመምራት እንደሚሳተፉ አባ ሎምባርዲ ገልጠው የሰጡትን ጋዜጣዊ መግለጫ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.