2013-04-26 16:12:01

ብፁዕ ካርዲናል በርቶነ፦ የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ረቡዓዊ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ


RealAudioMP3 የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ ብፁዕ ካርዲናል ታርቺዚዮ በርቶነ ትላትና በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በእምነት ዓመት ምክንያት ለጳጳሳዊ የሳሊዚያን መንበረ ጥበብ ኣባላትና የጥበብ ማደሪያ ቅድስት ድንግል ማርያም መንፈሳዊ ነጋድያን ተቀብለው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሰሙት ስብከት የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ረቡዓዊ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ለማዳመጥ ከውጭና ከውስጥ የሚሰባሰበው የምእመን ብዛት የሚያስደንቅ ብቻ ሳይሆን እያንዳንዷ ዕለተ ረቡዕና እሁድ የመልአከ እግዚአብሄር ጽሎት ግባኤ አስተምህሮ ዕለተ ሰንበት ዘፋሲካ ይመስላል፣ ቅዱስነታቸው ወጣት ትውልድ የሚማርኩ ሁሉም ወደ ክርስቶስ እንዲያመራና ከእርሱ ጋር እንዲገናኝ የሚደግፉ ወደ ታደሰው ፋሲካ የሚመሩ መሆናቸው በዕለተ ረቡዕ የሚሰበሰበው የሕዝብ ብዛት ያረጋግጠዋል። በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የሚሳበውና የሚማረከው የሕዝብ ብዛት የሚያዳምጠው ሥልጣናዊ ትምህርት በልቡ በማሰላሰል ይለወጥ ዘንድ እንዲያበረታታውና ተለወጦ ሌሎችን ወደ ክርስቶስ እንዲማርክ ለልኡክነት የሚያነቃቃ ይሆን ዘንድ ተስፋችን ነው፣ የቅዱስ አባታችን ሥልጣናዊ አስተምህሮ ለማዳመጥ የሚሰበሰበው የህዝብ ብዛት ደስ የሚያሰኝ የሚያስደንቅ ተአምር ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.