2013-04-26 16:09:19

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፦ ለማኅበራዊ ፍትህ መረጋገጥ የሁሉም ኃላፊነት


RealAudioMP3 በአርጀንቲና ወታደራዊ አምባ ገነናዊ ሥርዓት በስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት በአገሪቱ ንፁሓን ዜጎች ላይ በፈጸመው ሽብርና ጅምላዊ ቅትለት ሳቢያ ውዶቻቸው ልጆቻቸው ወዳጆቻቸው ያጡት የወላጅ አያት እናቶች በፕላዛ ደ ማዮ ለሚጠራው ማኅበር ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅድስት መንበር የውጭ ግንኙነት ጉዳይ ምክትል ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ አንቶኒየ ካሚለሪ ፊርማ የተኖረበት መልእክት ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታውቆ እንደነበር የሚዘከር ሲሆን፣ ቅዱስነታቸው እ.ኤ.አ. ሚያዚያ 24 ቀን 2013 ዓ.ም. በመሩት ረቡዓዊ የትምህረተ ክርስቶስ አስተምህሮ ለተሳተፉት የአያት እናቶች ደ ፕላዛ ደ ማዮ ማኅበር ልኡካን አባላት ባሰሙት የትምህርተ ክርስቶስ ፍጻሜ ሰላምታን አቅርበው፣ ይህ ማኅበር አምባ ገነናዊ ወታደራዊ መንግሥት ለሞት የዳረጋቸው የአገሪቱ ዜጎች ዝክረ ታሪክ ህያው ለማረግ በሚያደርገው ጥረት አበረታተው ከማኅበሩ አባላት ጋር ባካሄዱት ግኑኝነትም ለማህበሩ አባላት አባታዊ ሰላምታ አቅርበው ሓዋርያዊ ቡራኬ ሰጥተው መሰናበታቸው የገለጠው ሎ ሶርቫቶረ የተሰየመው የቅድስት መንበር ዕለታዊ ጋዜጣ በትላትና ኅትመቱ በመግለጥ፣ የማኅበሩ አባላት አያት እናቶች በበኩላቸውም ከቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ጋር የተካሄደው ግኑኝነት ለመላ የአርጀንቲና ሕዝብ ወላጆቻቸውና ልጆቻቸው ወዳጆቻቸውን ላጡት ታሪክ አቢይ ግምት የሰጠ ተስፋ ያነቃቃ ግኑኝነት ነበር በማለት አስተያየት መስጠታቸውም አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.