2013-04-26 16:14:43

ስሎቫኪያ፦ የተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን ለውህደት ዓለም አቀፍ የመናብርተ ጥበብ ጉባኤ


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ከግንቦት 9 ቀን እስከ ግንቦት 10 ቀን 2013 ዓ.ም. በስሎቫኪያ ርእሰ ከተማ ብራቲስላቫ የተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን ለውህደት የሚያደረጉት ጥረት ለማነቃቃትና በተለይ ደግሞ በቅድስት መንበርና በሩሲያ መካከል የአቢያተ ክርስቲያን ለውህደት ታልሞ በሚደረገው የጋራ ውይይት እንዲጀመር ለማነቃቃት በሚል ሃሳብ ላይ ያተኮረ ዓለም አቀፍ የመናብርተ ጥበብ ዓውደ ጥናት ሊካሄድ መወሰኑ ሲር የዜና አገልግሎ አስታወቀ።
ይህ ጉባኤ በመናብርተ ጥበብ የሥነ ታሪክ ዘርፈ ጥናትና የሞስኮና የመላ ሩሲያ ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግኑኝነት ጉዳይ ሐዋርያዊ ቢሮ፣ በሩሲያ የዓለም አቀፋዊ የሥነ ታሪክ ተቋም፣ በብራቲስላቫ የምትገኘው የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ቀርሎስና መተዎዲዮስ የቲዮሎጊያ መንበረ ጥበብ በጋራ ያዘጋጁት መሆኑ የገለጠው ሲር የዜና አገልግሎት አክሎ፣ የጳጳሳዊ የሥነ ታሪክ ሥነ ምርምር ኮሚቴ አባል የሥነ ታሪክ ሊቅ ኤሚሊያ ህራቦቨክ ይህ የተለያዩ አቢያተ ክርስቲያን የውኅደት የጋራ ሂደት ርእስ ሥር ሊካሄድ የተወሰነው ጉባኤ ዓላማ ለውኅደት ታቅዶ የሚደረገው ጉዞ የሚያተኩርባቸው ጥንታውያንና አስከ አለንበት ዘመን እየተወራረሱ የመጡት ታሪካዊ ጥያቄዎች በጋራ ለይቶ ለመመልከትና በእነዚህ ጥያቄዎች ዙሪያ የሥነ ታሪክ ጥናት የሚሰጠው መልስና የሚያካሂደው ጥናት መጻኢና ብሎም በዚሁ የጥናታ ዘርፍ ዋቢ የሆኑትን ታሪካዊ ሰነዶች እርሱም በቫቲካን በሩሲያ እና በተለያዩ ቤተ ምዘክሮች የታቀቡት ሰነዶችን ለይቶ በጥልቀት ለመመልከት የሚል መሆኑ ሲገለጡ በዚህ በሚካሄደው ዓውደ ጥናት ከተለያዩ 9 አገሮች የተወጣጡ 20 ሊቃውንት አስተምህሮ እንደሚያቀርቡና በተጨማሪም ዓውደ ጥናቱ በኤውሮጳ ማእከላዊ አቢይ ሞራቪያ ክልል የሚገኘው የቀርሎስና መቶዎዲዮስ ታሪካዊ ቤተ መዘክር 1150 ዓመት ምሥረው በሚታሰብበት ዓመት የሚካሄድ መሆኑ ሲር የዜና አገልግሎት አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.