2013-04-24 15:27:40

የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ


RealAudioMP3 20ኛ ዓመቱን ያጠናቀቀው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ምክንያት በማድረግ የቫቲካን ረዲዮ በተከታታይ በሥነ አቢያተ ክርስቲያን ጉባኤዎችና የቲዮሎጊያ ሊቅ የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል በአባ ዳርዩዝ ኮውላዝዪክ አማካኝነት የሚያቀርበው ሳምንታዊ አስተምህሮ በመቀጠል፣ ትላንትና አባ ኮዋልዝዪክ ባቀረቡት 23ኛው ክፍለ አስተምህሮ የአዳም ኃጢአት ላይ በማተኮር ቀደምት የሰብአዊ አበው እግዚአብሔርን ለመተካት ያደረጉት ውሳኔ የሚመለከት ርእሰ ጉዳይ ሲሆን እግዚአብሔር እግዚአብሔርነቱን ሊነጥቀው ለቃጣው ለታበየው ሰው ለብቻው እንዳልተወውም በማዳን እቅድ በሙላት ተገልጦልናል፦ በኦሪት ዘፍጥረት፦ “እግዚአብሔር መልካም እንደሆነ አየ” የሚል ቃል ተጽፎ እናገኛለን፣ በዚህ ብቻ ሳይወሰን የአዳም ኃጢአት ታሪክ ተጽፎም እናገኛለን። ኦሪት ዘፍጥረት ምዕ. 3 ቍ. 3፦ “ነገር ግን በገነት መካከል ካለው ከዛፉ ፍሬ እግዚአብሔር አለ እንዳትሞቱ ከእርሱ አትብሉ፣ አትንኩም” የሚለው የመጽሓፍ ቅዱስ ቃል አባ ኮውልዚዪክ አስታውሰው ከዚህ ጋር በማያያዝ በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ቁ. 396፦ የአዳም ኃጢአት፣ ነፃነት ሲፈተን “እግዚአብሔር ሰውን በርሱ አምሳል ፈጠርው ወዳጁም አደረገው፣ ሰው መንፈሳዊ ፍጡር ነውና በዚህ ወዳጅነት መጽናት የሚችለው በፈቃደኝነት ለእግዚአብሔር በመገዛት ብቻ ነው። ‘በጎውን ከክፋት ለመለይት የሚያችለውን የዕወቅት ዛፍ’ እንዳይበላ የተጣለበት እገዳ ይኽን በግልጽ ያስቀምጣል። ከዚህ ዛፍ በበላህበት ቀን በርግጥ ትሞታለ። በጎን ከክፉ ለመለይት የሚያስችለው የዕውቀት ዛፍ፣ ሰው ፍጡር እንደ መሆኑ በፈቃደኛነት መቀበልና ከልቡ ማክበር የሚግባውን ከቶ የማይታለፍ ገደብ በምሳሌነት ያስገነዝባል። ሰው ያለፈጣሪው መኖር የማይችል ለፍጥረት ሕግጋትና የነፃነትን አጠቃቀም ለሚወስኑት የሥነ ምግባር ደንቦች መገዛት ያለበት ፍጡር ነው” ከሚለው ሃሳብ ጋር በማያያዝ ያ የዕውቀት ዛፍ ሰው ፍጡር በመሆኑ ያለው ፍጡራዊ ውስንነት የሚገልጥ ምልክት ነው። ሆኖም ይኽ ውሱንነት ማለትም ፈተና ውስንነት የለህም የሚል ነው ብለዋል።
የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ አዳምና ሄዋን በፈጣሪ ላይ ያላቸውን እምነት ልባቸውን በመዝጋት እምቢ በማለት የፈጣሪ ቦታ በገዛ እራሱ ለመተካት ይጣጣራሉ። የታደለውን ነጻነትን ያምጻል (ቍ. 387 እና 397 ተመልከት)። በጠቅላላ የዘር ማጥፋት አመጽ ማለትም እልቂት ያጋቡት ዘረኝነት ናዚ ማርክሳዊና ሌሊናዊ ማኦነት ጽንሰ ሓሳቦች የተመለከትን እንደሆነ ያ እግዚአብሔርን ለመተካት የሚለው የሰው ፈተና ጽንሰ ሓሳብ በማድረግ የመልካምና የክፋት መመዘኛ ገዛ እራሳቸውን በማድረግ ሰው አለ እግዚአብሔር ያሉ ናቸው። ዘመናዊነትንም ጭምር የተመለከትን እንደሆነ የቤተሰብ ባህርይ የሚያዛቡ እንደ እግዚአብሔር መሆን የሚለው ሰይጣናዊነት የሚገልጡ የተለያዩ ምልክቶች የተሞላ ነው። እግዚአብሔር አይዋሽም። ኃጢአት ሞትን ይወልዳል፣ ወንዱና ሴቲቱ (አዳምና ሔዋን) ፍርሃት ተከናንበው፣ እርስ በእርሳቸው ይወቃቀሳሉ፣ እንደ እግዚአብሔር ለመሆን ያደረጉት ሙከራ እራቁታቸው ያስቀራቸዋል። እኛም በሕይወታችን የዚህ ዓይነቱ ኃጢአት እንፈጽማለን ነገር ግን ጌት ፈጽሞ ለብቻችን አይተወንም። ዘፍጥረትና የማዳን እቅድ ታሪክ ቀጣይ ነው” በማለት ያቀረቡት አስተምህሮ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.