2013-04-24 15:24:37

ብፁዕ ካርዲናል ፐል፦ መማክርት እንጂ ፈጻሚ አካል አይደለንም


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የአንዲት ቅድስት ሐዋርያዊት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ተባባሪዎች የበላይ ሐዋርያዊ መስተዳድር መዋቅር ለማደስ ያላቸው እቅድ መሠረት በዚህ ሐዋርያዊ እቅድ የሚተባበሩዋቸው አማካሪዎች ከተለያዩ አገሮች የተወጣጡ ስምንት ብፁዓን ካርዲናሎችና ብፁዓን ጳጳሳት መመልመላቸው የሚታወስ ሲሆን፣ የዚህ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የተመለመለው የብፁዓን ካርዲናሎች መማክርት ጉባኤ አባል በአውስትራሊያ ሲድነይ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ጆርጅ ፐል ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፣ አማካሪዎች እንጂ ፈጻሚ አካል አይደለንም በማለት ውሳኔው የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ነው። እኛ ተራ አማካሪዎች እንጂ ፈጻሚ አካል አይደለንም፣ ቅዱስ አባታችን ለዚህ ላቆሙት የብፁዓን ካርዲናሎች ጉባኤ ግምገማ የሚሰጡ የዚህ ጉባኤ የማጽደቅና ውድቅ የማድረግ ውሳኔ የሚጠይቁ ሳይሆን ወሳኔው የእሳቸው የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት የሮማ ጳጳስ ነው። ስለዚህ በሚፈጽሙት ኅዳሴ ለሚያቀርቡት ጥያቄ መልስ ለመስጠትና ለማጣራት በሚሹት ርእሰ ጉዳይ ቀርቦ ለመደገፍ ነው ብለዋል።
ስለዚህ ቅዱስ አባታችን የአንዲት ቅድስት ሓዋርያዊት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ተባባሪዎች የበላይ ሐዋርያዊ መስተዳድር መዋቅር ለማደስ ያላቸው እቅድ እግብ ለማድረስ በሚያደረጉት ጥልቅ ጥናት ቀርቦ ለመደገፍ ነው። ግብረአዊ ሃሳባዊ ድጋፍ በማቅረብ ቅዱስነታቸው ለሚያቀርቡት ጥያቄ ይኽ የመለመሉት የብፁዓን ካርዲናሎችና ብፁዓን ጳጳሳት ጉባኤ መልስ ለመስጠትና ኅዳሴው እግብ ለማድረስ የሚደግፍ የመሻርም ሆነ የማጽደቅ ስልጣንና መብት የለውም በተጨማሪም ኅዳሴው እንዲህ መሆን ወይን ይኽ መሆን አለበት በማለት የሚደራደር ወሳኝ አካል ማለት እንዳልሆነ ገልጠው የሰጡትን ቃለ ምልልስ እዚህ ላይ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.