2013-04-22 15:06:33

የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ጉባኤ አስተምህሮ ጸሎተ ንግሥተ ሰማይ


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 21 ቀን 2013 ዓ.ም. ጸሎት ንግሥተ ሰማይ ከመድገማቸው ቀደም በማድረግ ባቀረቡት ሥልጣናዊ አስተምህሮ፣ ዕለቱ የጥሪ ቀን የሚከበርበት መሆኑ ማስታወሳቸውና በተለያዩ የዓለምችን ክልሎች የሚታዩት ግጭቶች ሰላማዊ መፍትሔ እንዳያገኙ ጥሪ ባቀረቡበት አስተምህሮ ቅዱስነታቸው በዮሓንስ ወንጌል የተገለጠው እርሱም የእረኛውና የበጉ ምሥል ላይ በማተኮር፦ ኢየሱስ ከሐዋርያት ጋር ሊያጸናው የሚሻው ወዳጅነት ጓደኝነት ያንን እርሱ ከአባቱ ጋር ያለው ግኑኝነት የሚያንጸባርቅ እንዲሆን ይሻል። ይኽም አንዱ በአንዱ ላይ የሚሰጠውና የሚኖረው ታማኝነት ፍጽሙ ሱታፌና የአባላነት መንፈስ እጅግ የሚጎላበት ጥብቅ ግኑኝነት የሚል ነው። ኢየሱስ ከአባቱ ጋር ባለው ግኑኝነት ላይ የጸና ሱታፌ ይኖረን ዘንድ ይጠራናል ይኽ ደግሞ ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወት የሚሸኝ መንገድ ነው” እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፋውስታ ስፐራንዛ ገለጡ።
“በጎቼ ድምጼን ለይተው ያውቃሉ የሚለው የጌታ ቃል እንዴት ደስ የሚያሰኝ ቃል ነው። የድምጽ ሚሥጢር፣ ገና በእናት ማሕጸን እያለን የእርሱ ድምጽን የመለየት ብቃት የታደልን ነን፣ በምናዳምጠው ድምጽም ፍቅር ወይንም ጸረ ፍቅር መሆኑ ለይተን እንረዳለን። ድምጹ የፍቅር ወይስ የጥላቻ መሆኑ ለመለየት እንችላለን። የኢየሱስ ድምጽ ልዩ ነው። የእርሱ ድምጽ የፍቅር ድምጽ ነው። ከሌሎች ዓይነት ድምጾች ለይተን እናውቀውም ዘንድ እንማር። እርሱ የሞትን ጥልቅ ጉድጓድ በሚሻግረው በሕይወት ጎዳና ላይ ይመራናል። በኢየሱስ ድምጽ የተማረኩ መሆኔ ስገነዘብ፣ የእርሱ ድምጽ ልቤን የሚያቃጥል ሲሆን በእውነቱ እግዚአብሔር የፍቅር የእውነት የሕይወትና የውበት ምኞት አኑሮዋል። ኢየሱስ ፍቅር እውነት ሕይወትና ውበት ነው። ኢየሱስ ሙላት ነው” እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ስፐራንዛ አስታወቁ።
ኢየሱስ በቅርብ ይከተሉት ዘንድ የሚጋብዝ ቃሉ በተለያየ ምኞትና ውጣ ውረድ አማካኘንት ገልጦላቸሁ ይሆናል። የኢየሱስ ሓዋርያ የመሆን ፍላጎት በውስጣችሁ አዳምጣችሁ ሊሆን ይችላል። እናንተ ይኸንን ታስባላችሁ? ኢየሱስ ከእኛ ከእኔ ምን ይፈልጋል የሚል ጥያቄ እናቅርብለት። ይኸንን ጥያቄ ለማቅረብ መፍራት አይገባንም። የወጣትነት እድሜ በዚህ ዓይነት መንፍስ ለአበይት ዓላማ ለማዋል በሚል ፍላጎት ላይ ለማኖር እትፍሩ። በብርታት ኢየሱስ ከእኔ ምን ትፈልጋለህ የሚለውን ጥያቄ አቅርቡለት” ካሉ በኋላ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ዕለቱ ዓለም አቀፍ የጥሪ ቀን መሆኑ በማስታወስ፦ ዛሬ የክህነት ማዕርግ ስለ ተቀበሉት የሮማ ሰበካ አዳዲስ ካህናት እንጸልይ፣ እነዚህ አሥሩ ወጣቶች ጌታ ላቀረበላቸው ጥሪ አሺ በማለት መልስ ሰጥተዋል። በእውነት እንዴት እጹብ ድንቅ ነው” እንዳሉ ስፐራንዛ አመለከቱ።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በአጸደ ቅዱስ ጴጥርስ የተሰበሰቡት በብዙ ሺሕ የሚገመቱት ምእመናን ያቀረበላቸው ጭበጫባ ስማቸውን በመደጋገም ያሰማው የነበረው ኃይለኛ ድምጽ ኢየሱስን የሚጠራ ድምጽ ይሁን እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ፋውስታ ስፐራንዛ ገልጠው። በመጨረሻም በቨነዝዋላ ተከስቶ ያለው ፖለቲካዊ ውጥረት በውይይት መንፈስ ረግቦ ሰላም እንዲጸና አደራ በማለት፣ የአገሪቱ የፖለቲካና የመንግሥት አካላት አመጽ በሚያገል በጸናው የውይይት መንፈስና በእውነት ላይ ተመሥረተው የሕዝብና አገር ጥቅም በማስቀደም የተከሰተው አለ መግባባት በሰላማዊ መንፈስ እንዲፈቱ ማሳሰባቸውና ምእመናን ሁሉ ስለ ሰላም እንዲጸልዩና ስለ ቨነዝዌላ በተስፋ ላይ የጸና ሰላም በማቅረብ የኮሮሞቶ ቅድስት ድንግል ማርያም ስለ አገሪቱ ታማልድ፣ በደቡባዊ ምዕራብ ቻይና በተከሰተው አደገኛው ርእደ መሬት ለተጎዱትና ለሚሰቃዩት ሁሉ እንጸልይ፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዚሁ ዕለት ብጽእና ያወጀችላቸው እ.ኤ.አ. በ 1618 ዓ.ም. የደም ሰአማዕትነት የተቀበሉት ኢጣሊያዊ አባ ኒኮሎ ሩስካ ለሰጡት የቃልና የሕይወት ምስክርነት ጌታን እናመስግን። ወጣቱ ትውልድ ሕይወቱ በመልካም አላማ ላይ እንዲያውለው ይርዳን በማለት በዚህ የዛሬ 50 ዓመት በፊት ር.ሊ.ጳ. ጳውሎስ ስድስተኛ ውሳኔ መሠርት በኩላዊት ቤተ ክርስቲያን በሚከበረው የጥሪ ቀን ስለ ጥሪ ሁሉ እንዲጸልይ አደራ በማለት፣ ቅዱስ አኒባለ ማሪያ ዘፈረንሳይ የጥሪ ጸላይ ሓዋርያ አማላጅነት በጌታ ማሳ የሚሰማሩ ብዙ ሰራተኞች ይልክ ዘንድ በአማላጅነቱ እንጸልይ በማለት ጸሎት ንግሥተ ሰማይ አሳርገው ቡራኬ ሰጥተው መሰናበታቸው ፋውስታ ስፐራንዛ አስታወቁ።







All the contents on this site are copyrighted ©.