2013-04-22 15:19:26

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ምኅረት በመስጠት አትሰልቹ፣ እረኞች እንጂ ሹማምንት እይደላችሁም


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 21 ቀን ዓለም አቀፍ የገዳማዊ ሕይወት የክህነት ጥሪ ቀን በሚከበርበት ዕለት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለአሥር የሮማ አቢይ ዘርአ ክህነት ተማሪ ዲያቆናት የክህነት ማእርግ መስጠታቸው የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ ገለጡ።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው ማእርገ ክህነት ከመስጠታቸው ቀደም በማረግ ገና የቦኖስ አይረስ ሊቀ ጳጳሳት እያሉ እንደሚያደርጉት መንፈሳዊ ልምድ፣ እርሱም ምሥጢረ ክህነት ከሚቀበሉት ዲያቆናት ጋር በመሆን የቅድስት ድንግል ማርያም ጥበቃና አማላጅነት ከ10 የሮማ አቢይ ዘርአ ክህነት ምስጢረ ክህነት ከሚቀበሉት ጋር በመሆን መጸለያቸው የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ አያይዘው ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ከሮማ ኅየንተ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል አጎስቲኖ ቫሊና ጋር በመሆን በሠሩት መሥዋዕተ ቅዳሴ በእያንዳንዱ አሥሩ ዲያቆናት እራስ ላይ እጃቸው በማኖር ማዕርገ ክህነት ፈጽመው አቅፈውም ሰላም በማለት ያሳዩት ምልክት በእውነቱ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውን ለዚህ ሚሥጢር በመጥራት የእርሱ የእረኛናነትና የክህነት ተልእኮ በማሳተፍ ቀጣይነቱ ያረጋገጠበት መሆኑ የሚገልጥና ኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ዓመታዊ የጥሪ በዓል በምታከብርበተ ዕለት የሰጡት የሠሩት ምሥጢረ ክህነት በመሆኑም ክህነት ያለው ጥልቅ ምስጢር እንዲጎላ የሚያደርግ ዕለት ነው ብለዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው ከተሾሙበት ዕለት ጀምሮ ይኽው ለመጀመሪያ ግዜ በሠሩት ሚሥጢረ ክህነት ባሰሙት ስብከት፦ “ለእኔና ከእኔ በኋላ ለሚመጡት ብፁዓን ጳጳሳት ታዣዝ ትሆናለህን?” ለሚለው ሚሥጢረ ክህነት ለሚቀበለው ዲያቆን ኵላዊት ቤተ ክርስቲያን ለምታቀርበው ጥያቄ እያንዳንዱ ዲያቆን፦ “አዎን እፈጽመውም ዘንድ ቃል እገባለሁ” ከተሰኘው መልስ ቀጥሎ ቅዱስ አባታችን፦ “ገና በእናትህ ማሕጸን ውስጥ እያለህ ጌታ ባንተ ያነቃቃው ሥራ እስከ ፍጻሜ ያድረሰው” በሚል ቃል ድልው በማለት ማዕርገ ክህነት ከሰጡ በኋላ፦ “ለሁሉም ያንን በደስታ የተቀበላችሁት ቃለ እግዚአብሔር አቅርቡ። ቃለ እግዚአብሔርና እምነት በመጀመሪያ ላስተላለፉላችሁ ቅድመ አያቶቻችሁ ወላጆቻችሁ የትምህረተ ክርስቶስ አስተማሪዎቻችሁን አስታውሱ። የእምነት ጸጋ ያስተላለፉላችሁ ናቸውና። ቃለ እግዚአብሔር የግል ንብረታችሁ አለ መሆኑም መቼም ቢሆን እንዳትዘነጉ፣ ቃለ እግዚአብሔር በቤተ ክርስቲያን የሚታቀብ የእግዚአብሔር ቃል እንጂ የእናንተ ቃል አይደለም። መቼውም በክርስቶስና በቤተ ክርስቲያኑ ስም መሃሪዎች ለመሆን አትሰልቹ። በቅብአ ቅዱስ አማካኝነት የታመሙትን ስቃይ ታቀላላችሁ፣ ለአረጋውያን የዋሆች ለመሆን አትፍሩ። መጋቢያን ማለትም እረኞች እንጂ ሹማምነቶች አይደላችሁም። በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ሸማግሌዎች እንጂ ደላላዎች አይደላችሁም። የመልካሙ እረኛ ምስልና አብነት በፊታችሁ አስቀድማችሁ ይኸንን ለማገልገል እንጂ ሊገለገል ያልመጣውን የጠፋውን ሊያድም የመጣው እረኛ ተከተሉ” እንዳሉ አለሳንድሮ ጂሶቲ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.