2013-04-22 15:12:45

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ ለብ ያለ ማኅበረ ክርስቲያን የኢየሱስ ቤተ ክርስቲያን መገንባት አይቻለውም


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 20 ቀን 2013 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እንደተለመደው በቅድስት ማርታ የእንግዳ መቀበያ ሕንፃ ውስጥ በሚገኘው ቤተ ጸሎት በሚሠዋ ፍቅር የቅዱስ ቪንቸንሶ ዘፓውሊ ደናግል ማኅበር ሥር የሚተዳደረው በሮማ ሕጻናትና እንዲሁም በድኽነት ጫንቃ ሥር የሚገኙት ቤተ ሰቦችን የሚደግፉ የሕጻናት ጉዳይ ተንከባካቢ የበጎ ፈቃድ ማኅበር አባላት በተሳተፉበት ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ በዕለቱ ምንባብ ላይ ተንተርሰው፦ “ለብ ያለው ክርስቲያን በኢየሱስ ክርስቶስ ሳይሆን በገዛ እራስ ልክነት የሚመዘን ቤተ ክርስቲያንን ለመገንባት የሚሻ ነው” በሚል ሃሳብ ላይ ያነጣጠረ ስብከት ማሰማታቸው ያረገውን በሥዋዕተ ቅዳሴ የተከታተሉት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ሰርጆ ቸንቶፋንቲ ገለጡ።
ቀዳሚው ማኅበረ ክርስትያን ካጋጠመው ስደትና መከራ በኋላ በተረጋጋና ሰላም በሰፈነበት ሁነት ጸንቶ በመጓዝና በፈሪሃ እግዚአብሔርና በመንፈስ ቅዱስ እየተጽናና ያድግ እንደነበር የሚለው የግብረ ሐዋርያት ቃል ላይ በማተኮር፦ በፈሪሃ እግዚአብሔር ይኽም እርሱን በመስገድ ብቻ የሚኖረው የእግዚአብሔር ህልውና ሳይሆን የእግዚአብሔር ህልውና መልካም ነገር ሁሉ በመፈጸም በሚኖረውና በሚገልጠው መንፈስና ተግባር በእግዚአብሔር ጎዳና መራመድ የቤተ ክርስቲያን አግባብ ነው። መጽናናትና ደስታ የተሞላው ጉዞ ነው። ይኽ ደግሞ ከመንፈስ ቅዱስ መጽናናት የሚገኝ ዓይነተኛ መለያ ነው። ወደ ፊት እንድንል የሚያደርገን ኃይል ነው” ደቀ መዛሙርት በኢየሱስ ኃይለኛው ቃል ተደናግጠው እርስ በእርስ በማጉረምረም ይኽ ደግሞ መሰናክል አድርገው በመመልከት መምህራቸውን ለብቻው ሲተዉት፦ ደቀ መዛሙርቱ ለብቻው ትተዉት ከእርሱ ርቀው በመሄድ ይኽ የተለየው ሰው ልንፈጽመው የማይቻለንን ነገር ያመለክትልናል ኃይለኛ የሆነ ነገር ነው የሚናገረን። በዚህ እርሱ በሚያመለክተው መንገድ መራምድ አደገኛ ነው። ስለሆነም እንጠንቀቅ ራቅ ብለን እንከተለው። ኢየሱስን ያደንቁታል ሆኖም የሚለው ሁሉ ግራ የሚያጋባ ነውና ከመቅረቡ ይልቅ ራቅ ብለን ከእርሱ ጋር እጅግ ሳንቀላቀል ብንከተለው ነው የሚሻለው” ይላሉ። አንዳንድ የማኅበረ ክርስቲያን አባላት የኢየሱስ ክርስቶስ ስም በመመስከር የደም ሰማዕትነት የተቀበሉ ኢየሱስን በርቀት በጠቋሚ የመልእክት መቀበያ መሣሪያ አማካኝነት ሳይሆን ከእርሱ ጎን በመሆን በእርሱ መንገድ የተራመዱ መሆናቸው ቅዱስ አባታችን ሲያብራሩ፦ እነዚህ ሰማዕታት ጌታ ለቅዱስ ጴጥሮስ ‘እናንተም እኔን ትታችሁ ልትሄዱ በርቀት በጠቋሚ የመልእክት መቀበያ መሣሪያ ተመርታችሁ ልትከተሉኝ ትወዳላችሁን?’ ሲል ያቅረበለትን ጥያቄ ጠንቅቀው የተረዱ ናቸው። ‘ጌታ ሆይ አንተ የዘለዓለም ሕይወት ቃለ አለህና ከአንተ ርቀን ወደ ማን እንሄዳለን’ ሲል ይመልስለታል። ይኽ ዓይነቱ መልስ ምሉእ ተከትሎ የሚጠይቅ በመሆኑም እርሱ ብቻ የዘለዓለም ሕይወት ቃል ያለው መሆኑ ታምነው የሚከተሉት ቁጥር በጣም አነስተኛ ሆኖ ነው የሚገኘው” ካሉ በኋላ በመጨረሻ፦ “ቤተ ክርስቲያን በፈሪሃ እግዚአብሔርና በመንፈስ ቅዱስ በመጽናናት ጸንታ እያደገች ትሄድም ዘንድ ስለ ቤተ ክርስቲያን እንጸልይ። ጌታ ኢየሱስ መከተል ጽናት ብርታት የሚጠይቅ በመሆኑ በዚህ ተደናግጠን ሁሉም የሚስማማበት ነው ከሚባለው ጸረ ኢየሱስ ከሆነው የማጉረምረምና ከመሰናከል ፈተና ጌታ ነጻ ያውጣን። እንዲህም ይሁን” በማለት ያሰሙት ሥልጣናዊ ስብከት እንዳጠቃለሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ቸንቶፋንቲ ገለጡ።








All the contents on this site are copyrighted ©.