2013-04-19 15:33:55

የእንግልጣርና ወይለስ ብፁዓን ጳጳሳት በአገረ ቫቲካን


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 17 ቀን 2013 ዓ.ም. ረቡዓዊ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ አቅርበው እንዳበቁ እዚህ በሮማ ለመንፈሳዊ ሱባኤ የሚግኘው የእንግልጣርና ወይለስ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት አባላት ብፁዓን ጳጳሳት ተቀብለው ማነጋገራቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
በዚህ በተካሄደው ግኑኝነት የወስትምኒስተር ልኂቅ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ኮርማክ ሙርፍይ ኦኮኖር መሳተፋቸው ሲገለጥ፣ ስለ ተካሄደው ግኑኝነት አስደግፈው የወስትሚንስትር ሊቅ ጳጳሳት የእንግልጣርና ወይለስ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ቪንሰንት ኒኮላስ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ “ከቅዱስ አባታችን ጋር ለመገናኘት ዕድል በማግኘታችን ደስተኞች ነን። ቅዱስ አባታችን ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን አዲስ ደስታና ተስፋ እያስገኙ ናቸው። ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጌታ በሳቸው አማካኝነት የጸደይ ሕይወት እንድትኖር እያደረገ ነው። በእውነቱ ለቤተ ክርስቲያናችን የጸደይ ወቅት ነው በማለት ይኽ ደግሞ የእሳቸው ሃሳብ ብቻ ሳይሆን መላ ብፁዓን ጳጳሳት ካህናት የመንፈሳዊ ማኅበር አባላት ምእመናን የሚመሰክሩት ሓቅ ነው። ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በስብከታቸውም ሆነ በሚያቀርቡት አስተምህሮ፣ በረቡዓዊ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ወዘተ. የሚጠቀሙበት ቃልና ምልክት የብዙ ልብ እየማረከ ነው” ካሉ በኋላ፦ “የቅድስት አባታችን ትህትና የዋህነት ግልጽነት የሚጠቀሙባቸው ቃላት በታላቋ ብሪጣንያ የብዙ ልብ እየሳበ ከመሆኑም ባሻገር፣ ቤተ ክርስቲያንና ሕዝብ (ምእመናን) ከምን ግዜም በበለጠ እንዲቀራረቡ እረኞችና መንጋ መካከል ያለው መቀራረብ ጥብቅ እያደረገ ነው። ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን የጸደይ ወቅት ነው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ያልሆኑት የሌሎች ሃይማኖቶችና አቢያተ ክርስቲያን ምእመናን ጭምር ቅዱስነታቸውን ለማዳመጥ የሚያሳዩት ጉጉት በቅርብ ያረጋገጥኩት ተመክሮ ነው” ነው ብለዋል።
ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. በ 2010 ዓ.ም. በእንግልጣር የፈጸሙት ሐዋርያዊ ጉብኝት ለብዙ ምእመን ወደ እምነት ዳግም መመለስ እንዳደረገና ይኽ የጌታ ድንቅ ሥራ በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ አማካኝነት ቀጣይነት ተረጋግጦ ሕዝቡ በሳቸው ትህትናና አስተምህሮ እየተማረከ መሆኑ ገልጠው፣ ለተናቁት ለሚሰቃዩት በሚሰዋ ፍቅር ቅርብ የመሆኑ የሁሉም በተለይ ደግሞ የቤተ ክርስቲያን ተልእኮ እያጎሉ ሁሉም ይኸንን ፍቅር እንዲኖር እያነቃቁ መሆናቸውም አብራርተዋል።
በመጨረሻውም እየተካሄደ ያለው መንፈሳዊ ሱባኤ ሰብአዊ ድኽነታችን በጌታ ፊት ሊያስፈራን ሳይሆን በበለጠ ወደ እርሱ ለመቅረብ የሚያበቃን ሰብአዊ አጋጣሚ መሆን እንዳለበት በተለያየ መልኩት ማለትም በስብከት በጸሎት እየተኖረ ነው። ደካማነታቸውን ፍጹም አለ መሆናቸው ወደ ጌታ የሚያቀርብ ምክንያት ከሆነ ሰብአዊ ውስንነታችን እያስፈራንም ስለዚህ በሰው ልብ ውስጥ ያለው ጥልቅ ጥማት የሚያረካው ዘለዓለማዊ ሕይወት የሕይወት ውኃ የሆነው እግዚአብሔር ነው። ብፁዓን ጳጳሳት ካህናት የመንፈሳዊ ማኅበር አባላት ልኡካነ ወንጌል ሁሉም ምእመን በጠቅላላ ይኸንን ዘለዓለማዊው የማያልቀው የሕይወት ውኃ ሊያገለግል መጠራቱ የሚስተነተንበት ስባኤ መሆኑ ገልጠው የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.