2013-04-19 13:16:14

እምነት የእግዚአብሔር ስጦታ ነው፣ ከእርሱ ጋር ፊት ለፊት ተገናኝተን የምንወያይበት መሣርያም ነው፣


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በትረ ሥልጣን ዘመንበረ ጴጥሮስ ከያዙ ጀምሮ ልማዳዊ እየሆነ የሚመጣ ያለው በየጥዋቱ ከተለያዩ የቫቲካን አካላት ጋር በመሆን በየጥዋቱ በቫቲካን ውስጥ በሚገኘው የቅድስት ማርታ እንግዳ መቀበያ ቤተ መቅደስ በሚያሳርጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ የሚያቀርቡት አጠር ያለ ስብከት ነው፣
ትናንትናም እንደልማዳቸው ስለ እምነት በተለይ ደግሞ ኢትዮጵያዊው የንግሥት ህንደኬ ዣንደረባ እግዚአብሔር በልቡ ባኖረው እምነትና ሐዋርያ ፊሊጶስን ወደ እርሱ በመላክ በኢየሱስ አምኖ ወዲያውኑ እንዲጠመቅ መጠየቁና በመንፈስ ቅዱስ ተመልቶ እምነት በሰጠው ደስታና ሰላም ተሸኝቶ መንገዱን እንደቀጠለ ገልጠዋል፣ ከኢየሱስ የምናገኘው ደስታና ሰላም የዚህ ዓለም ሰላምና ደስታ ሳይሆኑ ነጻ የሚያደርጉ ከእግዚአብሔር ጋር እንድንወያይ የሚያደርጉን ናቸው፣
“እምነት ያለው ዘለዓለማዊ ሕይወት አለው፣ ሕያው ነው፤ ሆኖም ግን እምነት ስጦታ ነው የሚሰጠንም እግዚአብሄር አብ ነው፣ እኛ ይህንን የእምነት ጉዞ መቀጠል አለብን፤ ይህንን ጉዞ በምናከናውንበት ጊዜ አንዳንዴ በጉዳያችን ተይዘን ለጉዳያችን ቅድምያ በመስጠት ኃጢአተኞች በመሆናችን ልንሳሳት እንችላለን ሆኖም ግን እግዚአብሔር ሁሌ መሓሪ ስለሆነ ማረን ብለን ከጠይቅነው ይምረናል፤ ስለዚህ ተስፋ ሳንቍርጥ ወደፊት እንገስግስ፣ በዚሁ መንገድ ስንጓዝ ለኢትዮጵያዊ ዣንደረባ እንደሆነ ሁሉ ለእኛም ይገለጥልናል፣
የምናምነው በቅድስት ሥላሴ እግዚአብሔር አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ነው፣ በእምነት ደግሞ ከማንኛቸው ወይም ከአብ ወይም ከወልድ ወይንም ከመንፈስ ቅዱስ ጋር እንወያያለን፣ እግዚአብሔር አካል አለው፣ እንጂ እንዲያው አምናለሁ ብሎ የሚታለፍ አይደለም፣ የዘመናችን አደጋም ይህ ነው፣ እግዚአብሔርን እንደ ማንኛ ኃይል ወይም ሁኔታ መግለጥና በግድየለሽነት መመላለስ መሆኑን ሲገልጡ በየትኛው እግዚአብሔር ታምናለህ ብለው ይጠይቃሉና፤“አምላካክችን እንደ ሽቱ የተሰራጭ! ዝም ብሎ ተበትኖ ያለ በሁሉም ስፍራ የሚገኝና ማንነቱ የማይታወቅ አይደለም፣ እኛ በእግዚአብሔር አብ ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ እናምናለን፣ በሶስት አካላት እናምናለን፣ ከእግዚአብሔር ስንነጋገር ደግሞ ከሶስቱም ካንዳቸው እንነጋገራልን እምነት ማለትም ይህ ነው፣ ጌታ በወንጌሉ እንደሚለን “እግዚአብሔር አብ ካልሳበው በስተቀር” ወደ እኔ ሊመጣ የሚችል የለም፤ ስለዚህ ወደ ኢየሱስ መሄድ ኢየሱስን ማግኘት ኢየሱስን ማወቅ የእግዚአብሔር ስጦታት መሆኑን ያመለክታል፣ ይህንን ስጦታ ማሳደግና መጠበቅም የእኛ ፈንታ ነው ሲሉ ስብከታቸውን ደምድመዋል፣







All the contents on this site are copyrighted ©.