2013-04-19 15:26:01

ኃይለኛ የተስፋ ንፋስ


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ብፁዓን ጳጳሳት ለ visita “ad Limina ማለትም በየአምስቱ ዓመት በቫቲካን ሐዋርይዊ ጉብኝት ለማከናወንና ከመንበረ ጴጥሮስ ጋር ያላቸውን ትሥሥር፡ ውህደት ለመመስከር ብሎም ለማጽናት፡ ለቅዱስ ኣባታችን ር.ሊ.ጳ. የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ታዛዥነታቸውን፡ አንድነታቸውን ለመመስከር እዚህ ሮማ ቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ ለመሳለና ስለ ቤተክርስትያናቸው ወቅታዊና አንግብጋቢ ርእሰ ጉዳዮች አስደግፈው ከቅዱሱ አባታችን ጋር በመነጋገርም መሪ ቃል የሚያገኙበት ሐዋርያዊ ጉብኝት ምክንያት ከትላትና በስቲያ በሐዋርያዊ መንበራቸው በኢጣሊያ የትረቪዞ ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት የመጀመሪያው ቡድን ተቀብለው ካነጋገሩ በኋላ ቀጥለውም ሁለተኛው የምክር ቤት ብፁዓን ጳጳሳት ቡድን ትላትና ተቀብለው አንዳነጋገሩ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ስለ ተካሄደው ግንኙነት አስደግፈው የኡዲነ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ አንድረያ ብሩኖ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ “በእውነቱ የተካሄደው ግንኙነት የተዋጣለትና የወንድማማችነት መንፈስ የጎላበት ሲሆን፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. የብፁዓን ጳጳሳት ሐዋርያዊነት ኅብረት ያንጸባረቁበት ሁነት መደማመጥ የታየበትና ስለ የውሉደ ክህነትና የገዳማዊ ሕይወት ጥሪ በመወያየትም ወጣት ትውልድ ለሚጠራው ጌታ የማዳመጥ ቅድመ ዝግጁነት ይኖረውም ዘንድ በቁምስናዎች በተናጥል ከአበ ነፍስ ጋር በሚከናወነው መንፈሳዊ ግኑኝነት እማካኝነት ማነጽ ያለው አስፈላጊነት የተሰመረበት ሰፊ ውይይት የተካሄደበት ግኑኝነት ነበር” ብለዋል።
“በቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ አማካኝነት እግዚአብሔር በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ኃይለኛ የተስፋ ንፋስ እያነነቃቃ ነው። ሕዝብ ማለትም ከቤተ ክርስቲያን ርቆ የነበረው ቅዱስ አባታችን በሚሰጡት ወንጌላዊ ምስክርነት ምክንያት እጅግ እየተነካ ወደ ቤተ ክርስቲያን እየተመለሰ ነው። ስለዚህ በእያንዳንዱ ምእመን ልብ ውስጥ ያነቃቁትና እያንቃቁት ያለው መንፈሳዊ ጥማት የሚያረካው ጌታ ነውና የእግዚአብሔር መሣሪያ የሆኑት ብፁዓን ጳጳሳት ልኡካነ ወንጌል ካህናትና ገዳማውያን ለዚህ ዓላማ ቅዱስነታቸውን በመታዘዝ የተገቡና ዝግጁዎች መሆን ይጠበቅባቸዋል ያሉት ብፁዕ አቡነ ብሩኖ አያይዘውም፦ እየተስፋፋ ባለው ፖለቲካዊና ኤኮኖሚያዊ ቀውስ ምእመናን ጥልቅ የተስፋ እስትንፋስ በቤተ ክርስቲያን ከሚገለጠው እምነት ያገኙ ዘንድ አስፈላጊ ነው። ይኽ ደግሞ ከቀቢጸ ተስፋነት ያድናል። ስለዚህ ቅዱስ አባታችን ይኽ አይነቱ ተስፋ በሁሉም ልብ ውስጥ እያነቃቁ ናቸው” በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.