2013-04-19 15:30:23

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ፦ ለማኅበራዊ ፍትህ መረጋገጥ የሁሉም ኃላፊነት


RealAudioMP3 በአርጀንቲና ወታደራዊ አምባ ገነናዊ ሥርዓት በስልጣን ላይ በነበረበት ወቅት በአገሪቱ ንፁሓን ዜጎች ላይ በፈጸመው ሽብርና ጅምላዊ ቅትለት ሳቢያ ውዶቻቸው ልጆቻቸው ወዳጆቻቸው ያጡት የወላጅ እናቶች በፕላዛ ደ ማዮ ለሚጠራው የእናቶች ማኅበር ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ቅድስት መንበር የውጭ ግኑንነት ጉዳይ ምክትል ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ ብፁዕ አቡነ አንቶኒየ ካሚለሪ ፍሪማ የተኖረበት መልእክት ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባስተላለፉት መልእክት በፈላጭ ቆራጭ አምባ ገነናዊ ሥርዓት ወቅት ለሞት የተዳረጉት ንፁሓን ዜጎች ተዘክሮ በሁሉም ልብ ታትሞ በመላ አርጀንቲና የሚከበር መሆኑ አስታውሰው፣ ልጆቻቸውን ወዳጆቻቸውን የቤተሰቦቻቸውን አባላት ያጡት እናቶች ምንም’ኳ የተፈጸመው አሰቃቂው የቅትለቱ ተግባር የታሪክ ትውስት ሆኖ ቢቀርም እነዚህ እናቶች ያጋጠማቸው ሃዘንና ስቃይ በልብ ታትሞ የቀረ ሁሉም የዚህ ስቃይና ሃዘን ተካፋይነቱ የተረጋገጠ መሆኑና ሃዘኑ የሁሉም ሃዘንና ተዘክሮው መሆኑ ገልጠው ለሁሉም የዚህ ማኅበር እናቶች ሐዋርያዊ ቡራኬ በማስተላለፍ ጽናትና ብርታት ከጸሎት መሆኑም የገለጡት ቅዱስ አባታችን፣ በጸሎታቸው ሁሉንም እናቶች እንደሚያስቡ በማረጋገጥ እነዚህ እናቶች ለቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ እንዲጸልዩም አደራ ማለታቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
መጽናናት ሰላምና ፍትህ ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት እግዚአብሔር በሚሰጠው ኃይል የሚከወን ነው። ድኽነትን ኢፍትኃዊነትን በቆራጥነት ታግሎ ለማጥፋት የሚደረገው ትግል የእግዚአብሔር ኃይል የሚጠይቅ ነው። ለሚሰቃዩት በድኽነት ጫንቃ ሥር ለሚገኙት ለሚፈናቀሉት ለሚሰደዱት ሁሉ ቅርብ በመሆን በመደጋገፍ የእግዚአብሔር ፍቅር ይመሰክር ዘንድ አደራ ያሉት ቅዱስ አባታችን፣ የሕዝብ የጋራው ጥቅም ለማረጋገጥና ለመንከባከብ ኃላፊነቱን የለበሱት አካላት የሕዝብ ጥቅም በማረጋገጥ ተግባር ተግተው ለሚሰቃዩት ቅርብ በመሆን እኩልነትና መደጋገፍ የተሰኙትን እሴቶች ያስቀድሙ ዘንድ አደራ እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.