2013-04-18 08:57:51

የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ


RealAudioMP3 20ኛ ዓመቱን ያጠናቀቀው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ምክንያት በማድረግ የቫቲካን ረዲዮ በተከታታይ በሥነ አቢያተ ክርስቲያን ጉባኤዎችና የቲዮሎጊያ ሊቅ የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል በአባ ዳርዩዝ ኮውላዝዪክ የሚያቀርበው ሳምንታዊ አስተምህሮ በመቀጠል፣ ትላንትና አባ ኮዋልዝይክ በሰው ነፍስና አካል የእግዚአብሔር ምስል አለ በሚል ሃሳብ ላይ በማተኮር 22ኛው ክፍለ አስተምህሮ ማቅረባቸው ሲታወቅ። የሰው ልጅ ክብር በእግዚአብሔር የእግዚአብሔር አምሳል ተክኖ ከመፈጠሩ የሚመነጭ መሆኑ አባ ኮዋልዝዪክ የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ቍ. 356፦ “ከሚታየው ፍጥርት ሁሉ ሰው ብቻ ነው ፈጣሪውን ሊያውቅና ሊወድ የሚችለው። ስለ እርሱነቱ በእግዚአብሔር ፈቃድ የተፈጠረ ፍጡር እርሱ ብቻ ሲሆን፣ በዕውቀትና በፍቅር የእግዚአብሔር ሕይወት እንዲካፈል የተጠራው እርሱ ብቻ ነው። የተፈጠረው ለዚህ ዓላማ እንደ መሆኑ የክብሩም መሠረታዊ ምክንያት ይኸው ነው” የሚለውን የሰው ልጅ ክብር ምንጭ በማብራራት፣ ሌሎች ፍጥረታት ለምሳሌ ወፎች ሌሎች እንስሶች ጌታን በህላዌአቸው (ህልውናቸው) የሚወድሱ ሲሆኑ፣ ነገር ግን ሊያውቁትና ሊያፈቅሩት አይችሉም፣ የእግዚአብሔር መስተንክርነት የሚገልጡ ቢሆንም በእርሱ እምሳያና አርአያ አልተፈጠሩም ብለዋል።
በኦርት ዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ቁ. 26፦ “ሰውን በአምሳያችን እንፍጠር አለ” የሚል ቃል እናነባለን፣ በእግዚአብሔር አርአያና አምሳያ መፈጠር ማለት ምን ማለት ነው? እንሥራ የሚል ቃል የተጠቀመው ይኽ የኦሪት ምዕራፍ ብዙህነትን ያመለክታል። አንዳንድ የቤተ ክርስቲያን አበው በዚህ የብዙሃን ግስ ዘንድ የመለኮታዊ አካላት ጥልቅና ውስጣዊ ውይይት እንዳለ የሚገልጥ ነው በማለት ይተነትኑታል። በቅድስት ሥላሴ ካለው ውህደት የተፈጠርን ነን። ይኽ ማለት ደግሞ ከሌሎች ጋር በሚኖረን ግኑኝነት ብቻ ነው ሰብአዊ የምንሆነው። ማንም ሰው ከሌላ ሰው ጋር ካልተገናኘ ሰብአዊ ሊሆን አይችልም፣ አለ ማኅበራዊ ገጽታና ዝምባሌ ማንም ሰው ሊኖር እንደማይችል ነው ብለዋል።
“በተጨባጭ የሰው ልጅ ምሥጢር ትርጉም የሚኖረው ሥጋ በለበሰው ቃል ምሥጢር ብቻ ነው” (ቅ. 359)” የሚለውን ሃሳብ መሠረት በማድረግ የእግዚአብሔር አምሳያ የሚለው ቃል ሚሥጢረ የሆነውን ቃል የሚገልጥ በዚህ ቃል የስው ልጅ እውነተኛው የሰብአዊነት ምሥጢር ብርሃን ይቀዳጃል። እግዚአብሔር ሰውን በመፍጠር ኢየሱስ ክርስቶስን ያያል። ማለት ትስብእቱን ይመለከታል። በኢየሱስ ሰው ልጅ በሙላት ይገለጣል ብለዋል።
የሰው ሥጋ ከእግዚአብሔር አምሳያ ክብር ይጋራል፣ በትክክል የሰው ሥጋ የሚሆንበት ምክንያትም በረቂቅ ነፍስ እስትንፋስ ማግኘቱና በክርስቶስ ሥጋ የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንዲሆን የታቀደው መላው የሰው አካል ነው። ስለዚህ ሰው ሥጋና ነፍስ ቢሆንም አንድ ፍጡር ነው። በሥጋዊ ሁኔታ የምድራዊውን ዓለም ነገሮች በውስጡ ያካትታል፣ ጌታ ሙሉውን ሰው ለማዳን ይሻል፣ ስለዚህ ድህነት የሰው መንፍሳዊውና ሥጋዊው አድማሱን የሚያጠቃልል ነው በማለት ያቀረቡትን አስተምህሮ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.