2013-04-18 08:54:22

የቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ትላትና 86ኛው ዓመት ዕድሜአቸው ተከበረ


RealAudioMP3 ትላትና እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 16 ቀን 2013 ዓ.ም. ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲቶስ 16ኛ 86ኛ ዓመተ እድሜአቸው እንዳከበሩ ሲገለጥ፣ ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 16 ቀን 1927 ዓ.ም. በጀርመን ባቪየራ ክፍለ ሃገር በምትገኘው ማርክትል ኣም ኢን ከተማ ቀዳመ ስዑር በሚዘከርበት ቀን መወለዳቸውና ስለዚህ በበዓለ ፋሲካ ቅዳሜ ወደ እሁድ በሚያሸጋግረው ሌሊት ምሥጢረ ጥምቀት መቀበላቸው እ.ኤ.አ. በ 1990 ዓ.ም. በተጻፈው የብፁዕ ካርዲናል ጆሰፍ ራትዚንገር የሕይወት ታሪክ መጽሓፍ ዘንድ ተመልክቶ ይገኛል።
እ.ኤ.አ. ሰነ 2 ቀን 2012 ዓ.ም. በሚላኖ ከተማ በተከበረው ዓለም አቀፍ የቤተሰብ ጉባኤ ተገኘተው ከአንዳንድ ወጣቶች ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ የሕጻንነት ጊዚያቸውን በማስታወስ የሰጡት መልስ የሚወለደው ሕጻን የእግዚአብሔር ፍቅርና ፈቃድ መግለጫ ነው እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ ያስታውሳል።
ጆሰፍ ራትዚንገር በቤተሰብ ውስጥ ሰንበትን ማክበር የተማሩ ቅዳሜ ለእሁድ ቅዳሴ ማዘጋጃ እንዲሆን ተብሎ የእሁድ ምንባብ እቤት ውስጥ አባታቸው በማንበብ ቃለ እግዚአብሔር በማዳመጥ እሳቸውና ወንድማቸው ገዮርግ ለሰንበት ሊጡርጊያ እንዲህ ባለ ደስታ ይሰናዱ እንደነበር ሲያስታውሱ፦ እሁድ በቅዳሴ መበሳተፍ የሚኖሩበት ክልል ለሳሊስበርግ ቅርብ በመሆኑም ጥዑም ውሁድ ሚዚቃ ለማፍቀር በተለይ ደግሞ የሞዛርት ሹበርት ሃይድን እና የሌሎች ታላላቅ የጥዑም ሙዚቃ ቅኝት ደራስያን ድርሰተ ሙዚቃና ቅኝት ጋር የተዋወቁና የዚህ ዓይነቱ ሙዚቃ በማፍቅር ያደጉ መሆናቸው የቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የሕይወት ታሪክ መጽሓፍ ዘንድ ተመልክቶ ይገኛል።
እርስ በእርስ መፈቃቀር ከቤተሰብ እምነት በቤተሰብ አንድ መንፈስ ሆኖ መኖርን መተሳሰብን የተማሩ ቀጥሎ አምባ ገነናዊ ሥርዓት ባስከተለው ችግር ጦርነትና እርሃብ በመደጋገፍ በመተሳሰብ ክብር ያንን የቀውጢው ዘመን ያለፉ መሆናቸውና በቤተሰብ የሚኖር የእርስ በእርስ መፈቃቀር ተግባር፣ በተናንሽ ነገር ደስታን የሚሰጥ ይኽም ለእኔ ሳይሆን ለእኛ ተብሎ በመኖር የሚገለጥ ፍቅር በመሆኑ መተሳሰብ የሚመሰከርበት ቅዱስ ሥፍራ መሆኑ የታሪክ ማኅደራቸውን የጠቀሰው የቅድስት መንበር መግለጫ ያስታውሳል።







All the contents on this site are copyrighted ©.