2013-04-18 08:49:52

የሐዘን መግለጫ መልእክት


RealAudioMP3 ከትላትና በስቲያ በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ከተማ ቦስቶን ዓለም አቀፍ የማራቶን ውድድር በመካሄድ ላይ እያለ የተጠመዱ ቦምቦች ፍንዳታ ያስከተለው የሞትና የመቁሰል አደጋ ምክንያት ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለቦስቶን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲባል ሲን ኦማለይ የሐዘን መግለጫ የቴለግራም መልእክት ማስተላለፋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አመለከተ።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ባስተላለፉት የቴሌግራም መልእክት በሰው ሕይወት ላይ ያስከተለው የሞትና የመቁሰል አደጋ ልባቸው እጅግ በሐዘን እንደነካውና በእውነቱ የዚህ አይነቱ ተግባር ትርጉም የሌለው ጸረ ሰብአዊ ተግባር አውግዘው፣ የተጎዱትን ለመደገፍ በመረባረብ ላይ የሚገኙት የአደጋ የመከላከያ ኃይል አባላት የበጎ ፈቃድ ማኅበር አባላት ሕዝብ አመስግነው፣ የቦስቶን ሕዝብ በተጣለው የክፋት መንፈስ ጥቃት ተደናግጦ ተዘግቶ እንዳይቀር አደራ በማለት የክፋትን መንፈስ በመልካም መንፈስ በመታገል በመተባበር ቅንና ነጻ ሰላም የተሞላው ሕብረተሰብ ለማነጽ በሚደረገው ጥረት አቢይ አስተዋጽኦ ያበረክት ዘንድ አደራ በማለት በተለይ ደግሞ የሞት አደጋ ላጋጠማቸው እግዚአብሔር በመንግሥቱ እንዲቀበላቸውና ለሟቾች ቤተሰብ መጽናናቱን ያድላቸውም ዘንድ እንደሚጸልዩ ማረጋገጣቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.