2013-04-18 08:51:26

በቦስቶን የተጣለው የፍንዳታ አደጋ


RealAudioMP3 የተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ፈደራላዊ የመርመሪ ቢሮ አንድ የስምንት ዓመት ዕድሜ የሚገኝባቸው በጠቅላላ ሦስት ሰዎች ለሞት ሌሎች ሃያ እጅግ የተጎዱ የሚገኙባቸው በጠቅላላ በመቶዎች የሚገመቱትም ለመቁሰል አደጋ የዳረገው የሸበራ አደጋ ጠንሳሾችን ለመለየት በሁሉም አቅጣጫ ምርመራውን እያፋጣነ መሆኑ ሲነገር፣ የተጠመዱት ሁለት ቦምቦች በተከታታይ በ12 የዳግሚት ልዩነት ውስጥ ተከታትለው መፈንዳታቸውና ይኽ የተጣለው የሽበራ ጥቃት እ.ኤ.አ. መስከረም 11 ቀን 2001 ዓ.ም. ከተጣለው አሰቃቂው የአጥፍተህ ጥፋ የሽበራ ጥቃት ቀጥሎ በዓይነቱ የከፋ ነው ተብሎ የሚነገርለት ሲሆን፣ ስለ ጉዳዩ በማስመልከት ላ ስታምፓ ለተሰኘው የኢጣሊያ ዕለታዊ ጋዜጣ በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ልኡክ ጋዜጠኛ ማውሪዚዮ ሞሊናሪ በስልክ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ “የተጣለው የሽበራው ጥቃት ትልቅ ጠባሳ ጥሎ የሚያልፍ ለቦስተን ከተማ እና እንዲሁም በማራቶን ታሪክ የማይረሳ ጠባሳ ሆኖ እንደሚቀር ነው። የሽበራው አደጋ እንደተከሰተ እዛው አደጋ በተጣለበት ማራቶን ይካሄድበት በነበረው ክልል የነበረው ህዝብ የእርስ በእርስ መደጋገፍና መተባበር መታየቱና ካአደጋው የተረፈው የተጎዳውን ለመርዳት ሲረባረብ ታይተዋል። የተጎዱት የማራቶን ሯጭ ተወዳዳሪዎች ለመርዳት የተደረገው ርብርቦሽ በእውነቱ ቤተ ሰብአዊ መንፈስ ያረጋገጠ ነበር” ብለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ ባን ኪ ሙን የተጣለው የሽበራ ጥቃት በማውገዝ አሁንም ጥቃቱ ንጹሐን ዜጎች ዒላማ ያደረገ አሰቃቂ መሆኑ ጠቅሰው የተሰማቸው ጥልቅ ሐዘን የሚያረጋግጥ ለተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት ርእሰ ብሔር ባራክ ኦባማ የሐዘን የቴሌግራም መልእክት ማስተላለፋቸው ለማወቅ ሲቻል፣ ከትላንትና በስትያ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለቦስቶን ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል ኦማለይ በስማቸውና በኵላዊት ቤተ ክርስትያን ስም የሐዘን የቴልግራም መልእክት በማስተላለፍ የኵላዊት ቤተ ክርስትያን ጸሎት ማረጋገጣቸው ሲታወቅ፣ ብፁዕ ካርዲናል ኦማለይ በበኵላቸውም ቅዱስ አባታችን ላስተላለፉት የሐዘን መግለጫ የቴሌግራም መልእክት አመስግነው የተጎዱትን ለመደገፍ ለሚረባበሩቡት ለጸጥታ ኃይል አባላት ለእሳት አደጋ የመቀላከያ ኃይል አባላት ተራ ዜጎችን ሁሉ ማመስገናቸው ተገልጠዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.