2013-04-15 18:34:52

ቤተ ክርስትያን ከሙታን ተለይቶ የተነሣውን ክርስቶስን በርትታ መስበክ አለባት፣


ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትናንንትና እኩለ ቀን ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ባቀረቡት የንግሥተ ሰማያት ጉባኤ አስተምህሮ “ቤተ ክርስትያን ከሙታን ተለይቶ የተነሣውን ክርስቶስን በርትታ መስበክ አለባት፣ በተለያዩ ምክንያቶች ለሚሰደዱት ክርስትያን ደግሞ ቅርበትዋን በተግባር ማሳየት አለባት፣” ሲሉ የዕለቱን ቃለ ወንጌል በመመርኰዝ ትምህርት አቅርበዋል፣
በላቲኑ ሥር ዓተ አምልኮ ትናንትና ሶስተኛው የትንሣኤ እሁድ በመዘከሩ ከንባባቱ አንዱ የሓዋርያት ስብከትን የሚመለከቱ የሐዋርያት ሥራ ክፍል ነበር፣ “ሐዋርያት ለመጀመርያ ጊዜ በኢየሩሳሌም የሰበኩት ከተማዋን የሞላው ዜና ቅዱስ መጽሓፍ እንደሚለው ነቢያትም መሲሕ ብለው የተናገሩት ክርስቶስ እውነት ከሞት እንደተነሣ የሚለው ነበር፣ የካህናት አለቆችና የከተማዋ ታላላቅ ሰዎች ዜናውን ለማፈን ቢታገሉና የአማኞቹን ማኅበር ሊያወድሙ ቢጥሩም እንዲሁም ሐዋርያትን ቢያስሩም ቤተ ክርስትያንዋ እያደገች መጣች፣ ሐዋርያትን አትስበኩ ብለው ቢከለክልዋቸውም ጴጥሮስ ሌሎቹ አሥራ አንድ ሐዋርያት “ከሰዎች ይልቅ ለእግዚአብሔር መታዘዝ ይገባል፣ የአባቶቻችን አምላክ ክርስቶስን ከሙታን አነሣው እንደ አዳኝና ኃላፊም በቀኝ እጁ አስቀምጦታል የዚህ እውነት ምስክሮች ደግሞ እኛና መንፈስ ቅዱስ ነን” ሲሉ በጽናት ይናገራሉ፣ ለዚህም ሐዋርያት ይገረፋሉ ዳግም በኢየሱስ ስም እንዳይሰብኩም ብርቱ ማስጠንቀቂያ ይሰጣቸዋል፣ ሆኖም ግን እነርሱ እጅግ ደስ ብሎዋቸው ይሄዳሉ፤ ምክንያቱም በጌታ ምክንያት ስቃይ እንዲቀበሉ መብቃታቸው እጅግ ደስ አሰኛቸውና፣
ቅዱስነታቸው ይህንን አስመልክተው እነኚሁ የመጀመርያ ደቀ መዛሙርት በስደትና በብርቱ ዕንቅፋቶች እየተቸገሩ ሳሉ ለምስክርነቱና ለደስታው የሚሆን ይህንን ያህል ብርታት ኃይልና ጽናት ከየት አገኙት ይሆን? ብለው ይጠይቃሉና፣ሌላም መዘንጋት ወይንም መርሳት የሌለብን ጉዳይ ሲገልጡ “ሐዋርያት ከጸሐፊዎቹ ወይንም ከሕግ ሊቃውንቶቹ ወይንም ከካህናቱ ወገን አልነበሩም፣ ገርና ማንም ሰራተኞች ነበሩ፣ ሆኖም ግን ከዚህ ውስንነታቸው እና ከጸቡ ጋር መላው ኢየሩሳሌምን በትምህርታቸው ሊሞልዋት እንዴት ቻሉ?
“ይህንን ለማድረግ የቻሉት ከሙታን ተለይቶ የተነሣ ጌታ በጐናቸው መኖርና የመንፈስ ቅዱስ እርዳታ መሆኑ ግልጥ ነው፣ ይህንን ልዩ ፍጻሜ ሊገልጠው የሚችለው አብሮዋቸው የነበረው ጌታና ለስብከቱ ይገፋፋቸው የነበሩ መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው፣ እምነታቸው ሞቶ ከሙታን ከተነሣው ክርስቶስ ጋር የተሳሰረ ግላዊ ግኑኝነትና ኃያል መሠረት ነበረው፣ ስለዚህም የማንም እና የምንም ፍርሃት አልነበራቸውም እንዲያው ስደቱን እንደ የክብር ስጦታ ይመለከቱት ነበር ምክንያቱም የኢየሱስን ድኳ ለመከተልና በሕይወታቸው እርሱን ሊመስክሩ እርሱን ሊመስሉ ስለሚያስችላቸው ነውና፣ ይህ የሐዋርያት ጽናት ዛሬ ለኛ እጅግ አስፈላጊ ነው፣ አስፈላጊነቱም ለኛ ብቻ ሳይሆን ለሁል ጊዜ ቤተ ክርስትያን ነው፣
“አንድ ሰው ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በእውነት ባወቀበትና በእርሱም ባመነበት ጊዜ በሕይወቱ ውስጥ የጌታ መኖርንና የትንሣኤ ኃይል መልበሱን ያጣጥመዋል፣ ይህንን ተመኵሮ ለሌሎች ከመንገር የሚያደርገው ሌላ ምንም የለም፣ ይህም ሰው አለመግባባትና ጥላቻ በሚያጋጥመው ግዜም ልክ ጌታ ኢየሱስ በሕማማቱ እንዳደረገው በት ዕግሥት ይመላለሳል፣ በፍቅርና በእውነት ኃይል ይመልሳል፣ ካሉ በኋላ እመቤታችን ድንግል ማርያም በመላው ዓለም ለምትገኘውቤተ ክርስትያናችን የጌታን ትንሣኤ በንጽሕናና በብራታት እንድትሰብክና በወንድማማዊ ፍቅር ምልክቶች ተጨባች ምስክርነት እንድትሰጥ ታስችላት ዘንድ ተማጥነዋል፣
“ጌታ ከሙታን ተለይቶ እንደተነሣና ሕያው ሆኖ ከእኛ ጋር መኖሩን ለመመስከር የምንችልበት የወንድማዊ ፍቅር ምስክርነት ነው፣ በአሁኑ ግዜ በስደት ስለሚገኙ ክርስትያኖች እንጸልይ፣ በአሁኑ ግዜ ብዙ እጅግ ብዙ ክርስትያኖች እየተሰደዱና እየተሰቃዩ እንዳሉ እናስታውስ፤ ከሙታን ተለይቶ የተነሣ ክርስቶስ እንዲሸኛቸውና እንዲያጸናቸው በልባችን በፍቅር እንጸልያላቸው፣ ካሉ በኋላ ተፈሥሒ ኦ ንግሥተ ሰማይ ሃሌሉያ ጸሎት የንግሥተ ሰማያት ጸሎት አሳርገዋል፣
ከጸሎተ ንግሥተ ሰማያት በኋላ በዕለቱ በቨነሲያ ከተማ ብፅ ዕናው ለታወጀው የቅድስት ዶሮታ ተግባር እና የቅድስት ዶሮታ መማህራን ደናግል ማኅበር መሥራች የሆኑ አባ ሉካ ፓሲ በማስታወስ ለዚሁ የብፅ ዕና ምስክርነት እግዚአብሔር እናመስግን ብለዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.