2013-04-15 15:42:53

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በባዚሊካ ቅዱስ ጳውሎስ ፉዎሪ ለ ሙራ


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 14 ቀን 201 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. በሮማ ክፍለ ከተማ ፎሪ ለ ሙራ በሚገኘው የቅዱስ ጳውሎስ ቅዱስ አጽም በታቀበበት የቅዱስ ጳውሎስ ባሲሊካ የሮማ ጳጳስ እንደመሆናቸው መጠን የዚህ ጳጳሳዊ ባዚሊካ ሐዋርያዊ ሓላፊነታቸውን በይፋ ለመረከብ በቅዱስ ጳውሎስ ባዚሊካ ሊቀ ካህናት ብፁዕ ካርዲናል ጀምስ ሚካኤል አርቭይ የቅዱስ ጳውሎስ ባዚሊካ ገዳም አበ እምኔት አባ ኤድሙንዶ ፖወር ጋር በመሆን መሥዋዕተ ቅዳሴ ማሳረጋቸው የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ መሥዋዕተ ቅዳሴውን አሳርገው ባሰሙት ሥልጣናዊ ስብከት፦ ቅዱስ ጳውሎስ የአሕዛብ ሐዋርያ፣ ቅዱስ ጴጥሮስና ሁሉም ደቀ መዛሙርት የተከተሉት መንገድ አብሳሪነት ምስክርነትና ኃሴት የሚሉት ሦስት ግሶች የሚያጎላ መሆኑ አስታውሰው፣ ሐዋርያት የተቀበሉት ለማስተላለፍ እትናገሩ የሚለውን የዓለም ትእዛዝ ተጋፍጠው ስደት ግርፋት ስቃይ ሳይበግራቸው እንዳበሰሩ ቅዱስ አባታችን በማብራራት፦ “እኛ ስለ ኢየሱስ ለመናገር እንችላለን፣ በቤተሰብ በዕለታዊ ሕይወታችን ለምንገናኛቸው ሁሉ ክርስቶስ ለእኛ የሆነውን እናበስራለን ወይ? እምነት የሚወለደው ከማዳመጥ ነው። ማዳመጥ ለቃሉ አብሳሪነት ኃይል ነው” እንዳሉ መሥዋዕተ ቅዳሴውን የተከታተሉ የቫቲካን ረዲዮ ልእክት ጋዜጠኛ ደቦራ ዶኒኒ አስታወቁ።
ከክርስቶስ ጋር መገናኘት አዲስ የሕይወት ምዕራፍ የሚከፍት መሆኑና ሐዋርያትም ይኸንን ግኑኝነት በሕይወታቸው እንዳበሰሩ ያስታወሱት ቅዱስ አባታችን፦ ‘የነፍሳት እረኞች እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የማይኖሩ ከሆነ የእግዚአብሔርን መንጋ መጋብያን ሊሆኑ አይችሉም፣ ለክርስቶስ ገዛ እራስ መሥዋዕት አድርጎ ካለ ምንም ስሌት የሕይወት መስዋዕትነት የሚጠይቅ ቢሆንም ቅሉ ካለ ምንም ማመንታት ገዛ ርእራስ እነሆኝ ብሎ በማቅረብ የሚሰበክ ነው” እንዳሉ የገለጡት ልእክት ጋዜጠኛ ዶኒኒ አያይዘውም ቅዱስ ፍራንቸስኮ ዘአሲዚ ለወንድሞቹ የሰጣቸውን ምክር፦ “ወንጌል በቃልም ማበሰር ያለውን ላስታውስ እወዳለሁኝ፣ ስለዚህ ወንጌል በሕይወት ይመሰከራል። የሚሉትንና የሚሰብኩትን እምነትና ዕለታዊ ሕይወታቸውን ሳያጣምሩ የሚኖሩ የሚሉትና የሚያደርጉት የተለያየ ሆነን ስንገኝ የቤተ ክርስቲያን ታማኝነት ለአደጋ እናጋልጣለን” እንዳሉ አስታውቀዋል።
“በእያንዳንዳችን ልብ ውስጥ የታቀበው ጌታን በመንፈስ እና በእውነት ልንሰግድለት የሚከለክለን ጣዖት ሊኖር ይችላል። ስለዚህ ይኽ ጣዖት ማንና ምንድር ነው? ለጌታ መስገድ ከማኛውም ዓይነት በልባችን ተደብቆ ካለው ጣዖት ነጻ መሆንና ገዛ እራስ በሙላት ማቅረብን ይጠይቃል። ስለዚህ ጌታ የሕይወት ማእከል መንገድና ሕይወት አድርጎ መኖርና መከተልን ይጠይቃል” እንዳሉ ልእክት ጋዜጠኛ ዶኒኒ ገልጠው፦ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ካሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ፍጻሜ እ.ኤ.አ. በ 1541 ዓ.ም. የኢየሱሳውያን ማኅበር መሥራች ቅዱስ ኢግናዚዮዝ ዘሎዮላ እና የመጀመሪያ ማኅበሩ አባላት አቢይ መሃላቸውን ለመፈጸምና የማኅበሩ ተልእኮና ምሥረታ በይፋ ለማስጀመር የፈጸሙት ጸሎትና አስተንትኖ የሚያስታውሰው መንፈሳዊ ተግባር ለመፈጸም የ13ኛው ክፍለ ዘመን እመ አምላክ ዘሆዲጅትሪያ ቅዱስ ምስል ፊት ትንበርክከው ለመጸለይ በባዚሊካው ወደ ሚገኘው የቅዱስ መስቀል ቤተ ጸሎት ገብተው የጽሞና ጸሎት እናሳረጉ ልእክት ጋዜጠኛ ዶኒኒ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.