2013-04-15 15:31:02

ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ.፦ አስመስሎ መሸፋፈን ሳይሆን በእግዚአብሔር ታምኖ ሕይወት በሙላት መቀበል


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 13 ቀን 2013 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በአገረ ቫቲካን ቅድስት ማርታ ሕንፃ በሚገኘው ቤተ ጸሎት የአገረ ቫቲካን የእሳት አደጋ የመከላከያ ኃይል አባላት፣ የሃገረ ቫቲካን የጸጥታ አስከባሪ ኃይል አባላትና የሚሰዋ ፍቅር የደናግል ማኅበር አባላት የተሳተፉበት መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው፦ “ክርስትያን በሕይወት ፈተናና ችግር ፊት አቋራጭ መወጣጫ የሚከተል ሳይሆን ደገፉና እርዳታው ፈጽሞ በማያቋርጠው በእግዚአብሔር የሚታመን ነው” የሚል በእግዚአብሔር መተማመን የክርስትያን ጥሪ መሆኑ በሚያብራራ ሥልጣናዊ ሃሳብ ላይ ማእከል ያደረገ ሥልጣናዊ ስብከት እንዳሰሙ መሥዋዕተ ቅዳሴውን የተከታተሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ ገለጡ።
ሁኔታዎች ሳይሳኩና እንደተጠበቀው ሳይሆኑ ቢቀሩ ይኽ ጉዳይ የሕይወት ጌታ በሆነው በእግዚአብሔር ላይ ያለው እማኔ ለማግለል የሚዳርግ መሆን አይገባውም። ክርስትያን በሕይወቱ የሚያጋጥመውን ሁሉ በመቀበል እምነቱን በእግዚአብሔር ላይ አኑሮ እንዳልከው የሚል መሆኑ ቅዱስነታቸው በግብረ ሐዋርያት ተመልክቶ ያለውን የቀደምት ማኅበረ ክርስቲያን ሁኔታ ላይ ተንተርሰው በማብራራት፣ በቀዳሜ ማኅበረ ክርስቲያን ዘንድ አዳዲስ አባላቱ በእምነት ወንድሞች የሆኑት ግሪካውያን አይሁዳውያን በመካከላቸው ተቀስቅሶ የነበረው ክርክር በተለይ ደግሞ የእርስ በእርስ መተማማቱ ጉዳይ ቅዱስ አባታችን አስታውሰው፦ “እርስ በእርስ መተማማት መፍትሔ አያሰጥም መፍትሔም አይሆንም፣ ሐዋርያት በመንፈስ ቅዱስ ድጋፍ መሠረት ለተቀሰቀሰው ችግር አቢይ ግምት በመስጠት ደቀ መዛሙርትን ይጠራሉ አብረውም ስለ ጉዳዩ ይመክራሉ። ስለዚህ ችግሩን መሸፋፈን ወይንም መደበቅ ሳይሆን ችግሩ እንዳለ ተገንዝቦ ፊት ለፊት ማቅረብና ስለ ጉዳይ መወያየት አስፈላጊ ነው” ምክንያቱን የሐዋርያት ተቀዳሚው ኃላፊነት ጸሎትና ለቃለ እግዚአብሔር አገልግሎት መሆኑ በመገንዘብ የተከሰተውን ችግር ግምት ሰጥቶ ለመፍታቱ የጌታ ድጋፍ እንደማለየን መተማመን ያለው አስፈላጊነት ቅዱስ አባታችን ቀጥለው ሲያስረዱ፦ “የተደቀነብን ችግር ሊያስፈራን አይገባ፣ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ‘አትፍሩ እኔ ንኝ’ ነው ያለው። በተደቀነብን የሕይወት ችግር የተለያዩ ፈተናዎችና ውሳኔ ልንሰጥባቸው በሚገባን ጉዳዮች ፊት፣ ለብቻችን አይደለም እዚያ ጌታ አለ። ልንሳሳት እንችል ይሆናል፣ እርሱን ግን ሁሌ ቅርባችን ነው፣ ተሳስተሃል እትፍራ ቅነኛውን መንገድ ዳግም ምረጥ በእርሱ ላይ መንገድህን አቅና ይለናል። ስለዚህ የተደቀነብን ችግር ለመደበቅ የሚደረገውን ችግሩ እንደሌለ ለማስመስል የመሸፋፈኑ ተግባር ልክ በትያትር መድረክ እንደሚፈጸመው ጭምብል (ሽፋን) ማጥለቅ ሳይሆን ሕይወትን በሙላትና በተጨባጭነቱ ተቀብሎ መኖር ያስፈልጋል። ይኽ ማለትም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድና እግዚአብሔር ይሁን እንደሚለው አድርጎ መቀበል ማለት ነው። ስለዚህ የጌታ መንፈስ መፍትሔ የሚሆነውን ይሰጠናል” እንዳሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ደ ካሮሊስ ገልጠዋል።
ቅዱስ አባታችን በመጨረሻም እኔ ነኝ አትፉሩ ሲል ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ የተናገረው ቃል በማስታወስ፣ የእግዚአብሔር ቃል ችግር ባለበት ጨለማ ባለበት ሁሉ ፈጣን ደራሽና ደጋፊ መሆኑ መዘንጋት እንደሌለብን በማስታወስ፦ “እንዳንፈራ የእግዚአብሔር ጸጋ እንለምን፣ ሕይወትን ጨምብሎ ለመኖር ከመጣጣር ይልቅ፣ በማንኛውም የሕይወት ተመክሮና ሁነት ከጎናችን የማይለውን ኢየሱስ ጋር እንገናኝ እርዳታውን እንጠይቅ” በማለት ያሰሙትን ሥልጣናዊ ስብከት እንዳጠቃለሉ ልኡክ ጋዚጠኛ ደ ካሮሊስ ካጠናቀሩት ዘገባ ለመረዳት ተችለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.