2013-04-10 14:07:47

የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ


RealAudioMP3 20ኛው ዓመቱ ያጠናቀቀው የካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ምክንያት በማድረግ የቫቲካን ረዲዮ በተከታታይ ዕለተ ማክሰኞ በሥነ አቢያተ ክርስቲያን ጉባኤዎችና የቲዮሎጊያ ሊቅ የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል አባ ዳሪዩዝ ኮውልዝይክ አማካኝነት የሚያቀርበው የሥርጭት መርሃ ግብር በመቀጠል አባ ኮውልዝይክ ባቀረቡት 21ኛው ተከታታይ አስተምህሮ በዚህ በአሁኑ ወቅት በማኅበራዊ ፖለቲካዊ እንዲሁም ሃይማኖታዊ ዘርፍ አቢይ ርእሰ ጉዳይ ሆኖ ብዙ የሚያናግረው ስለ ጋብቻ ወይንም ምሥጢረ ተክሊል ላይ በማተኮር የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ ወንድና ሴት አድርጎ የፈጠረው እግዚአብሔር የገዛ እራሱ ምስልና አርአያ በማኖር የፈጠራቸው መሆኑ ግልጽ በሆነ አነጋገር በማብራራት፣ በዚህ በምንኖርበት ዘመን ፍርሃተ ክርስቲያን ርእዮተ ዓለም እርሱም ክርስቲያንን የሚጠላ በገዛ እራሱ በራሱ ርእዮተ ዓለም ልከነት ሰውን ማኅበርሰብን ልፍጠር የሚለው ርእዮተ ዓለም በስፋት የሚታይበት መሆኑ ገልጠው፣ ይኽ ደግሞ በትክክል እንደ እግዚአብሔር ልሁን ያለው ሰይጣናዊ ተግባር ነው። ጾታ ሰብአዊ ባህርይ ጋብቻ አባታ እናት ቤተ ሰብ የተሰኙትን የሥልጣኔ መሠረት የሆነው የመለያ ክብር ጨርሶ ለመሰረዝ የሚቃጣው የተዛባ የሥነ-ሰብእ ባህል ቤተ ክርስቲያን ስህተት ነው ብቻ ሳይሆን የተዛባ አመለካከት መሆኑ በሥነ-ሰብእ እውነት እርሱም “እግዚአብእሔርም ሰውን በእግዚአብሔር አምሳል ፈጠረው፣ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው” (ዘፍ. 1,27) በሚል ቃል ተገቢና አጥጋቢ መልስ ሰጥታበታለች እየሰጠችበትም ነው ብለዋል።
ሴት መሆን ወንድ መሆን የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ መዝገብ በቁጥር 369 በእግዚአብሔር የተፈቀደ እኩልነትና ልዩነት እርሱም ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው የሚለው የሥነ ሰብእ እውነታ ርእስ በማድረግ እንደሚገልጠው፦ ወንድና ሴት ሆነው ተፈጥረዋል፣ የእግዚአብሔር ፍላጎትና መልካም ፈቃድም ነው” ስለዚህ ይኽ እውነት የሰው ልጅ አእምሮ እንዲሁ የሚገምተው ወይንም ግላዊ ስሜት አይደለም፣ ሁለት ጾታዎች አሉ፣ ተባእትነት አንስትነት ስለዚህ አንዳንድ ሰዎች ያላቸው ጾታዊ መለያ ስነ አእምሮዋዊ መዛባት ወይንም መቃወስ ምክንያት የሚኖሩት ባለ ቤታዊ (ግላዊ የመለያ መዛባት) ችግር ያንን የሥነ ስበእ እውነት አይሰርዘውም።
ወንድና ሴት በሰብአዊነታቸው በፍጹም እኩልነት በሌላው በኩል ደግሞ እንደየሕላዌያቸው ወንድና ሴትና ሆነው የተፈጠሩ መሆናቸውና፣ ተመሳሳይ የሆነ ክብር ያላቸው ይኽም የእግዚአብሔር አምሳልና አርአያ ከመሆናቸው የሚታደል የፈጣሪ ጥበብና መልካምነት ያንጸባርቃሉ፣ በቁጥር 372፦ “ወንድና ሴት ሆነው የተፈጠሩት አንዳቸው ለሌላው እንዲሆኑ እንጂ እግዚአብሔር በግማሹ ፈጥሮ ስለ ተዋቸውና ስላላሟላቸው አይደለም” ይኸንን መለያ በምሥጢረ ተክሊል አማካኝነት የሚተገበር በብዙ ተባዙ ተግባር አማካኝነት በእግዚአብሔር ፈጣሪነት ባህርይ ሱታፌ ተለግሶላቸዋል። ጎደሎዎች ስለ ሆኑ በጋብቻ ሙሉ ይሆናሉ ማለት ሳይሆን እያንዳንዳቸው ሙሉ ናቸው ስለዚህ አንዳቸው ለሌላው እንዲሆኑ ተፈጥረዋል በሚለው የሚግለጥ መሆኑ ያብራሩ አባ ኮዋልዝይ አክለው ወንድ እና ሴት፦ በእግዚአብሔር እቅድ ውስጥ እንደ እግዚአብሔር ባለሟልነታቸው ምድርን እንዲገዟት ሥልጣን” የተሰጣቸው ሆኖም ይኽ ሥልጣን “በዘፈቀደ የሚመራ አፍራሽ የበላይነት” ማለት እንዳልሆነና እግዚአብሔር ለሰው ልጅ የሰጠው ተልእኮ እርሱም በእግዚአብሔር የፈጣሪነት ተግባር ተሳታፊ መሆኑ ነው የሚያረጋግጠው (ቁጥር 373 ተመልከት) በማለት ያቀረቡትን አስተምህሮ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.