2013-04-10 14:10:26

የቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ሥነ እሳቤ


RealAudioMP3 የዘመናችን አቢይ ተደናቂ የቲዮሎጊያ ሊቅ መሆናቸው በሁሉም የሚመሰከርላቸው የቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ሥነ እሳቤ በጀርመን የፍሪቡርግ ጳጳስ የጀርመን ብፁዓን ጳጳሳት ምክር ቤት ሊቀ መንበር ብፁዕ አቡነ ሮበርት ዞሊትሽ የተደረሰው፥ “የጆሰፍ ራትዚንገር የመዝገበ ቃላት እሳቤ (A B C of Joseph Ratzinger” በሚል ርእስ ሥር ያጠናቀሩት 290 ገጽ ያጠቃለለ የመዝገበ ቃላት መጽሓፍ በቫቲካን ማተሚያ ቤት ታትሞ ለንባብ መብቃት የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።
ይኽ መጽሓፍ እርሱም ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ና አባ ለሚለው ቃል ከሰጡበት ትንታኔ በመንደርደር ጥሪ የሚለው ቃል ፍቅር፣ ኢፈሊጣዊነት፣ ተስፋ የመሳሰሉት ቃላቶች ያካተተ እያንዳንዱ ቃል ፍልስፍናዊ ቲዮሎጊያዊ ጥልቅ ፍቹ ላይ ያነጣጠረ ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. የሰጡት ጥቅል ፍችና ትርጉም ማእከል ያደረገ መጽሓፍ መሆኑ ለማወቅ ሲቻል፣ ስለዚህ በዚህ መጽሓፍ ዘንድ ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የሰጡት ቲዮሎጊያዊና ፍልስፍናዊ የቃላት ፍች የሚገልጥ ከመሆኑም ባሻገር የእኚህ አቢይ የቲዮሎጊያ ሊቅ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ሰብአዊነት ጭምር የሚያጎላ መሆኑ ብፁዕ አቡነ ዞሊትሽ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው፣ እውነትና ፍቅር በክርስቶስ ዘንድ ተገናኝተዋል ክርስቶስ የሚመለከት እግዚአብሔርን ያያል የተሰኘው የእምነት እውነት የሚያጎላ ነው ብለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.