2013-04-10 08:46:48

ክርስትያን ለመሆንና እንደክርስትያን ለመኖር አትፍሩ፣


ክርስትያን ለመሆንና እንደክርስትያን ለመኖር አትፍሩ፣ ክርስቶስን በዓለም አደባባዮች ሁሉ እንዲደርስ አድርጉ፣
ቅ.አ.ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ትናንትና እኩለ ቀን ላይ በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ አብሮዋቸው የንግሥተ ሰማያት ጸሎት ለማሳረግና ሐዋርያዊ ቡራኬአቸውን ለመቀበል ለተሰበሰቡ ምእመናንና ነጋድያን በላቲኑ ሥር ዓተ አምልኮ ለሚከበረው ዳግማይ ትንሣኤ አመልክተው “ሰላም የምሕረት ፍሬ ናት፤ የእምነት ብርታት ኖሮአቸው ክርስትያን በሚመሰክርዋት የእግዚአብሔር ፍቅር የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው” ሲሉ ክርስትያኖች ሁላቸው በየአደባበዩ ክርስቶስን እንዲሰብኩ ዘንድ ጥሪ አቅርበዋል፣
ስመ ጥር ነፍሰኄር ብፁዕ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ ባወጁት መሠረትም የዳግማይ ትንሣኤ እሁድ የመለኮታዊ ምሕረት እኁድ መሆኑን በማስታወስም ይህ እኁድ የመለኮታዊ ምሕረት እኁድ ብቻ ሳይሆን የብርታት እኁድም ነው ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው ይህንን ብርታት ሲገልጹ ለእያንዳንዱ ክርስትያን ማንነቱን ለመመስከርና ለሌሎች የወንጌል መጕያ ለመሆን የሚያስፈልገው ይህ ብርታት ነው ብለዋል፣
ቅዱስነታቸው ትናንትና በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ብቅ ሲሉ ልክ ጌታ ኢየሱስ ከትንሣኤ በኋላ ለሐዋርያት እንዳላቸው ሰላም ከእናንተ ጋር ይሁን ሲሉ ሰላምታ ካቀረቡ በኋላ የዚህ ሰላም ትርጉም እንዲህ ሲሉ ገልጠውታል፣
“ሰላም ለእናንተ ይሁን የሚለው ማንኛው ሰላም ወይም የመልካም ምኞት መግለጫ አይደለም፤ አንድ ስጦታ ነው፤ ክርስቶስ በሞትና በሲኦል ካለፈ በኋላ ለሐዋርያቱ የሚያቀርበው ክቡር ስጦታ ነው፣ ይህ ሰላም የእግዚአብሔር ፍቅር በክፋት ላይ ያሸነፈውና የምሕረት ፍሬ ነው፣ እውነታኛና ጥልቅ ሰላምም እንዲሁ የእግዚአብሔር ምሕረትን ካጣጣሙ በኋላ ይገኛል፣” ሲሉ የእውነተኛ ሰላም ትርጉም ከግለጡ በኋላ ሌላው ያተኰሩበት ነጥብ ጌታ ኢየሱስ ለቅዱስ ቶማስ ባለው ነበር፣ ጌታ ከሙታን ከተነሣ በኋላ ሐዋርያትን እንደተገልጠላቸውና ቅ.ቶማስም እዛ ባለመኖሩ ስለ ጌታ መነሣት በነገሩበት ጊዜ በቍስሎቹ እጆቼን ካላኖርኩ አላምንም ባለው መሠረት ጌታ ኢየሱስ ስላም ለእናንተ ይሁን ብሎ በመሃከላቸው ከቆመ በኋላ ቅዱስ ቶማስን አይቶ እንዲያምን ነግሮት እሱም ጌታየና አምላኬ ብሎ እምነቱን ከገለጠ በኋላ ኢየሱስ አንተ ስላየህ አመንክ ሳላዩ የሚያምኑ ግን ብፁ ዓን ናቸው ባለው መሠረት ይህንን ብፅ ዕና ሲገልጡ እንዲህ ብለዋል፣
ይህች ቃል እጅግ አስፈላጊ ቃል ናት፣ የእምነት ብፅ ዕና ብለን ልንሰይማት እንችላለን፤ የእምነት ብፅ ዕና የምንለው “ያላዩ ግን ያመኑ ብፁዓን ናቸው” የሚለውን ነው፣ በሁሉም ጊዜና በሁሉም ቦታ በቤተክርስትያን የተሰበከውንና በክርስትያኖች የተመሠከረውን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ የለበሰው የእግዚአብሔር አብ ፍቅር ሥጋ የለበሰው ምሕረት መሆኑን የሚገልጠውን የእግዚብሔር ቃል በመስማት የሚያምኑ ብፁዓን ናቸው፣ ይህም እያንዳንዳችንን ይመለከታል፣ የቤተ ክርስትያን ተልእኮም ከሐዋርያት ልብ ፍርሓትን ባራቀው መንፈስ ቅዱስ እርዳታ ይህንን የክርስቶስ የፍቅር መንግሥትንና የሐጢአት ምሕረትን ማወጅ ነው፣
“እኛም ከሙታን ተለይቶ በተነሣው ክርስቶስ ማመንን ለመመስከር ብዙ ብርታት አለን! ክርስትያን በመሆናችንና እንደ ክርስትያን ለመኖር ፍርሃት ሊሰማን አይገባም፤ ከሙታትን ተለይቶ የተነሣው ክርስቶስ ስላማችን በመሆኑ በፍቅሩ በይቅር ባይነቱ በደሙና በምሕረቱ ስላም ስላደረገና ሰላማችን ወጥተን ከሙታን የተነሣውን ክርስቶስ ለመስበክ ይህ ብርታት ሊኖረን ያስፈልጋል፤ ሲሉ ካስተማሩ በኋላ ከም እመናኑ አብረው ተፈሥሒ ኦ ንግሥተ ሰማይ ሃሌ ሉያ ሲሉ የንግሥተ ሰማያት ጸሎት አሳርገዋል፣ ከጸሎቱ በኋላ ሐዋርያዊ ቡራኬ በመቸርና ሰላምታ በማቅረብ ከ100 ሺ በላይ ለሚሆኑት ም እመናንና ነጋድያንን ተሰናብተዋቸዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.