2013-04-10 09:11:23

በርዮ ደ ጃነሮ ሊካሄድ ተወጥሮ ያለው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ዝግጅት፣


እፊታችን ሓምሌ ወር በርዮ ደ ጃነሮ ሊካሄድ ተወጥሮ ያለው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ዝግጅት በታላቅ ጉጉት እየተካሄደ መሆኑ ከቦታ የሚደርሱ ዜናዎች ያመልክታሉ፣ እንደ አጋጣሚ ሆኖ ብራዚላዊትዋ የርዮ ደ ጃነሮ ከተማ የመጀመርያውን ደቡብ አመሪካዊ ር.ሊ.ጳ የመጀመርያ ዓለም አቀፍ ጉዞና የመጀመርያው በዓለም ዓቀፍ ወጣቶች መሳተፉቸውን ሲያመልክት፤ ር.ሊ.ጳ የሥልጣን ስማቸው እንዲሆን የመረጡት ቅ.ፍራንቸስኮስ ምሳሌ በመከተልም በዚሁ የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ልዩ ትኵረት ተሰጥቦት እየተሰራበት ያለው ተፈጥሮ በኃላፊነት የመጠበቅ ግዳጅንና ይህንን እግምት ውስጥ ያስገባ የሥልጣኔ እንቅሳቃሴ እንዲደረግ በእጅጉ እየተጣረበት መሆኑም ተመልክተዋል፣
አጋጣሚ ሆኖ ደግሞ ከአንድ ዓመት በፊት ዓለም አቀፍ ተፈጥሮን እግምት ውስጥ ያስገባ የሥልጣኔ ጉባኤ (ሳስተይናብል ደቨሎፕመንት) ተካሂዶ ነበር፣ እንዲሁም የርዮ ደ ጃነሮ አከባቢ የተባበሩት የዓለም መንግሥታት ድርጅት ዓለም አቀፋዊ ባህርያዊ አከባቢዎች ብሎ ከከለላቸው ክፍሎች ውስጥ ስለምትገኝ ይህ የተፈጥሮ ጥበቃ ወቅታዊና በትክክለኛ ቦታው የሚካሄድ መሆኑን የተለያዩ አካሎች ያመልክታሉ፣ የአገሩ የአከባቢ ሚኒስትር ሚኒስተር ኮራዶ ክሊኒ እ.አ.አ እፊታችን ሓምሌ ከ21 ቀን እስከ 28 ቀን ለሚካሄደው ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን በሚመለከት ይህንን መግለጫ ሰጥተዋል፣
“ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን አስደናቂ ነው ምክንያቱም ልክ ከአንድ ዓመት በፊት ዓለም አቀፉ አከባቢን እግምት ውስጥ ያገባ የሥልጣኔ ጉባኤ (ሳስተይናብል ደቨሎፕመንት) ርዮ ርዮ 20 በሚል ዓለም አቀፍ ግኑኝነቶችን የፈጠረና እኩልና ተጨባጭ ስልጣኔ ለሁሉም በሚል ር እስ ብዙ አገሮችና የአገር ቡድኖች ያስተሳሰረ ነበር፣ ጉባኤው አምና ሰኔ ወር 2012 ዓም ሲካሄድ በምጣኔ ሃብት የበለጸጉትንና ገና ለመበልጸግ ጥሩ መንገድ ይዘው ያሉ በብሪክስ የሚታወቀው ብራዚል ህንድ ቻይናና ደቡብ አፍሪቃ ያካተተ ጉባኤ የተካሄደበት አጋጣሚ ነበር፣ ይህ ጉባኤ ዓለም አቀፉን የምጣኔ ሃብት እንቅስቃሴ አረንጓዴ ኤኮኖሚ በሚል መሪ ሐሳብ እንዲንቀሳቀስና ባህርያዊና ተፈጥራዊ መስመርንና የሃይል ምንጮችን ሳያቃውስ በጥንቃቄ መደረግ ያለበት የብልጽግና እንቅስቃሴ እንዲሆንም አሳስቦ ነበር ሲሉ የዚሁ ጉባኤ ዓላማ አሁንም እንደገና በዚሁ ዓለም አቀፍ የወጣቶች ቀን ጉባኤ ተነሥቶ ሲሰራበት ኃልፊነታችንን እንድንወጣ የሚያሳስብ ነው ብለዋል፣
በሪዮ ዲ ጃነሮ የሚገኘው ካቶሊካዊ ዪኒቨርሲቲም የተቻለውን ያህል እያበረከተ መሆኑም ተገልጠዋል፣ ለዓለም አቀፉ የወጣቶች ቀን ይጠቅማል መሪ አሳብም ይሰጣል ተብሎ የሚዘጋጀውን ሰንድም ዘ ፍዩቸ ዊ ዎንት የምንፈልገው መጻኢ በሚል ር እስ ፍጻሜ ላይ እንደሆነም ተመልክተዋል፣








All the contents on this site are copyrighted ©.