2013-04-10 14:04:52

ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ.፦ አትፍረድ አትማ፣ ክርስቲያን የዋህና ለጋስ (በጎ ፈቃድ የተሞላ) ነው


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 9 ቀን 2013 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በሃገረ ቫቲካን በሚገኘው በቅድስት ማርታ ህንፃ ውስጥ ባለው ቤተ ጸሎት የሃገረ ቫቲካን የጤና ጥበቃ አገልግሎት ባለ ሙያዎችና የጤና ጥበቃ መሥተዳድር አባላት እንዲሁም የሃገረ ቫቲካን መሥተዳድር አባላትና ተጠሪዎች በተገኙበት ባሳረጉት መሥዋዕተ ቅዳሴ ባሰሙት ሥልጣናዊ ስብከት፦ “መንፈስ ቅዱስ ሰላሙን በማኅበረ ክርስቲያን ዘንድ ያኑር የማኅበረ ክርስቲያን አባላትንም የዋሆችና ከማማት የተቆጠቡ እንዲሆኑ ያድርጋቸው” በማለት ሁሉም የዋሆችና በጎ ፈቃድ የተሞላቸው ይሆኑ ዘንድ አደራ እንዳሉ የቅዳሴው ሥነ ሥርዓት የተከታተሉት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ደ ካሮሊስ ገለጡ።
ለአዲስ ሕይወት ዳግም እንዲወለዱ ላደረጋቸው መንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁነውና ሁሉም ማኅበረ ክርስትያን አንድ ልብና አንድ መንፈስ ነበሩ፣ ይኽም በመጀመሪያው የክርስትና ቅዋሜ የነበረው የመለያው ባህርይ ለወቅታዊት ቤተ ክርስቲያን የማይታበልና የማይጠልቅ ዘላቂ አርአያ መሆኑ ቅዱስ አባታችን በማብራራት፣ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና በኒቆዲሞስ መካከል የተካሄደው ወንጌላዊ ውይይት ላይ ተንተርሰው፣ ቆዲሞስ አንደ ሰው እንዴት ዳግም ሊወለድ ይችላልን? በሚለው ጥያቄ ላይ ገዛ እራሱን በማኖር በርግጥ ዳግም መወለድ በመንፈስ ቅዱስ ማለት ነው፣ ይኽም በምሥጢረ ጥምቀት የተቀብለው ጸጋ ነው። ስለዚህ ይኽ የተቀበልነው አዲስ ሕይወት ዕለት በዕለት መታነጽ የሚገባው እንጂ አንዴ ተኩኖ የሚኖር አይደለም፣ የተሆነውን ዕለት በዕለት መኖር ያስፈልጋል። ስለዚህ አዲስ ሰው ሆነህ መኖር የዕለት በዕለት ጉዞ መሆኑ ቅዱስነታቸው እንዳብራሩ ልኡክ ጋዜጠኛ ደ ካሮሊስ ገለጡ።
“ቀዳሜ ማኅበረ ክርስቲያን አዲስ ሕይወት ነበራቸው፣ ይኽም በዕለታዊ ኑሮአቸው አንድ ልብና አንድ መንፈስ በመሆን ይገልጡት ነበር፣ ይኽ ዓይነት ውኅደት አንድነትና ሰብአዊነት የተሞላው ጥዑም ውሁድ የፍቅር ሕይወት በመኖር እርስ በእራሳቸው በመተሳሰብና በመዋደድ ይገልጡት ነበር። ዛሬ የተዘነጋው ይኽ ዓይነቱ የክርስት አድማስ በእውነቱ ዳግም መጎናጸፍ ወሳኝ ነው። ስለዚህ የማኅበረ ክርስቲያን መለያ የሆነው ብዙ ጠላት ያለው የዋህነት ሕይወት ዳግም መጎናጸፍ ያስፈልጋል። የየዋህነት ጠላት በቅድሚያ ሓሜት፣ ሌላውን ማማት በምላስ ሌላውን መግረፍ ማሰቃየት፣ በዕለታዊ ሕይወት የተለመደ የየዋህነት ጠላት ተግባር ነው። ብዙዎቻችን የምንፈጽመው ጎጂ ተግባር ነው። ይኸንን ውስጣዊ ትግል በዕለታዊ ሕይወታችን በቤተሰብ በቁምስና በማኅበር በጓደኞች መካከል በመንፈሳዊ ማኅበር አባላት ዘንድ የምንኖረው ጉዳይ ነው። ሆኖም ግን ይኽ ዓይነቱ ሕይወት የአዲስ ሕይወት መግለጫ አይደለም። መንፈስ ቅዱስ ዳግም አዲሱን ሕይወት በእኛ ውስጥ ያነቃቃ” እንዳሉ የገለጡት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዚጠኛ ደ ካሮሊስ አያይዘው ቅዱስ አባታችን ክርስቲያን ሊኖረው የሚገባው ቅን ጸባይና ተግባር፦ ፈራጁ ዳና አንድ እርሱ እግዚአብሔር ብቻ ነውና አለ መፍረድ ከዛም ዝምታ፣ በሐሜታ ልንለው የፈለግነውን ለሦስተኛው አካል በሐሜት መልክ ከማጉረምረም ይልቅ ለሚመለክተው ባለ ቤት በቀጥታ መናገር፣ ከማማት ልናማው ለሚቃጣን ሰው ቀርበን ማነጋገር የሆነው ሁሉ የመናገር ብርታት ይኑረን። በመንፈስ ቅዱስ ድጋፍ ከመፍረድና ከማማት ነጻ ከሆን ለእኛና ለሁሉም መልካም ይሆንልናል” በማለት ያሰሙትን ሥልጣናዊ ስብከት እንዳጠቃለሉ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.