2013-04-10 16:41:58

ር ሊ ጳ ፍራንሲስ የተመድ ዋና ጽሐፊ ባን ኪሙን ተቀብለው አነጋግረዋል፡


ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጽሐፊ ባን ኪሙን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል ።ቅድስነታቸው እና የዓለም አቀፉ ድርጅት ዋና ጽሐፊ ባን ኪሙን በዓለም ዙርያ የሚታዩ ፖሊቲካዊ ማሕበራዊ እና ፖሊቲካዊ ቀውሶች ትኩረት በመስጠት መወያየታቸው በቅድስት መንበር የወጣ መግለጫ አስታውቀዋል።በዚሁ መግለጫ መሠረት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ እና ባን ኪሙን ሶርያ ላይ እየተካሄደ ያለውን ጦርነት በሚገታበት በአፍሪቃ ሀገራት የሚታየውን አለመረጋጋት ለማርገብ በሰሜን ኮርያ ያለውን ፍጥጫ ለመግታት በሚቻለበት ሁኔታ ተወያይተዋል።
ቅድስት ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ሰብአዊ ክብር እንዲታደግ እና ሰብአዊ መብቶች እንዲጠበቁ የምታካሄደው ጥረት በማጠናከር እንደምትጥር ቅዱስ አባታችን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፋራንሲስ መግለጣቸው የተባበሩት መንግስታት ዋና ጽሐፊ ባን ኪሙን በበኩላቸው በሳቸው የሚመራ ዓለም አቀፍ ድርጅቱ በዓለም ዙርያ በተለያዩ ምክንያቶች የሚከሰቱ ግጭቶች ለማረገብ እና ዘላቂ ኤኮንምያዊ እድገት እንዲገኛ ያለሰለሰ ጥረት እያካሄድች መሆንዋ ለቅድስነታቸው መግለጣቸው ግንኝነቱ ከተካሄደበት ቦታ የደረሰ ዜና ዘግበዋል
ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን ለዓለም አቀፋዊ ሰላም ያላትን ሐሳቢነት እና ለችግር የተጋለጡ ህዝቦች የምታቀርበው ሰብአዊ ርዳታ የሚመሰገን መሆኑ ባን ኪሙን ማመልከታቸው ዜናው አክሎ ገልጠዋል።የተባበሩት መንግስታት ዋና ጽሐፊ ባን ኪሙን ከየቅድስት መንበር ዋና ጽሐፊ ከብጹዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ ጋር ተገናኝተው ሐሳብ ለሐሳብ መለዋወጣቸው ተመልክተዋል ።
ይህ በዚህ እንዳለ ሆነ የተባበሩት መንግስታት ዋና ጽሐፊ ባን ኪሙን ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ እና ውና ጽሐፊ ከብጹዕ ካርዲናል ታርቺስዮ በርቶነ ከተገናኙ በኃላ ከየቫቲካን ጋዜጠኞች ጋር ተገናኝተው ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የመለሱ ሲሆን ቫቲካን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በጋራ ለመስራት የሚያስችልዋቸው ዘርፎች እንድያብራሩ ተጠይቀው ሲመልሱ ፡ እንዳሉት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን በዓለም አቀፍ ደረ ጃ ሰብአዊ መብቶች በማስከበር ማሕበራዊ ችግሮች በመቅረፍ ረገድ ብጋርዮሽ ይሰራሉ ይህን በተጠናከረ መልኩ ለመራት ይሻሉ ማለታቸው ተዘገበዋል።
የዓለም አቅፍ ድርጅቱ ዋና ጽሐፊ ባን ኪሙን በማያይዝ እንደገለጡት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው የተሰየሙት ፍራንሲስ የቅዱስ ፍራንቸስኮ ዘ አሲሲ ስም መምረጣቸው ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዓላማ የሚያስተሳስረው ነገር መኖሩ ጠቅሰው ይሄውም ከድሃ የዓለም ማሕበረሰቦች በቅርብ ለመስራት ያለመ እንደሆነ ማመልከታቸው ተገልጠዋል።
ይሁን እና የርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ትሕትና ሰብአዊነት እንደምያደንቁ ያመለከቱት ባን ኪሙን ከቅድስነታቸርው ጋር ማሕበራዊ ፍትሕ በሚገኝበት ሁኔታ ዙርያ ጥልቅ ውይይት ማካሄዳቸው ለቫቲካን ጋዜጠኖች ተናገዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የቀየሰው ሺሔኛው የእድገት ግብ እንዲጠቃለል አንድ ሺ ቀናት ቀረተውታል ያሉት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጽሐፊ ባን ኪሙን ግቡ ገቢራዊ ከሆነ ለድሀ ማሕበረሰቦች እጅግ ጠቃሚ እንደሚሆን ጥርጥር የለም ሲሉ ባን ኪሙን መግለጫ ሰጥተዋል።ዋና ጽሐፊው በማያያዝ እንድገለጡት ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በተለያዩ የዓለም ሃይማኖቶች መካከል አንድ ጠንካራ መገናኛ ድልድይ በማነጽ አብረው ለሰላም እንዲቆሙ ጥረት ማካሄድ ያሻል ማለታቸው አውስተዋል።
ካቶሊካዊት ቤተ ክርስትያን እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በዚች ዓለም ላይ ሰላም ይሰፍን ዘንድ አብረው እንደሚራመዱም ዋና ጽሐፊው ለቫቲካን ጋዜጠኞች ከሰጡት መግለጫ ለመረዳት ተችለዋል።በየተባበሩት መንግስታት ዋና ጽሐፊ ባን ኪሙን አመለካከት ፡ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ የሰላም እና የተግባር ሰው ናቸው ከዚህ ባሻገርም ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ ናቸው ።
ቅድስነታቸው ይላሉ ባን ኪሙን ሶርያ ላይ እየተካሄደ ያለውን አስከፊ እና አሰቃቂ ጦርነት እንዲገታ በሰሜናዊ እና ደቡባዊ ኮርያ ያለውን ውጥረት እንዲረግብ በእስራኤል እና ፍልስጤኖች የሰላም ሂደት እንዲጀመር በኮንጎ ረፓብሊክ እና በመካከለኛው አፍሪቃ ረፓብሊክ የሚታዩ ሁከቶች እንዲገቱ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያለሰለሰ ጥረት እንድያካሄድ ጠይቀውኛል ብለዋል።ትናትና ረፋድ ቫቲካን የጐበኙ እና ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ ጋር ተገናኝተው ሰፊ ውይይት ያደረጉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጽሐፊ ባን ኪሙን ቅድስነታቸው ኒውዮርክ ውስጥ የሚገኘው የድርጅቱ ዋና ጽሕፈት ቤተ ይፋ እንዲጐበኙ መጠየቃቸው አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.