2013-04-08 15:13:38

ኵላዊት ቤተ ክርስቲያን በጸረ የወሲብ ዓመጽ ትግል


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 5 ቀን 2013 ዓ.ም. ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን አንቀጸ አምነት ተንከባካቢ ቅዱስ ማኅበር ኅየንተ ብፁዕ አቡነ ገርሃኣርድ ልድዊግ ሚዩለርን በሐዋርያዊ መንበራቸው ተቀብለ እንዳነጋገሩ ለማወቅ ሲቻል፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በቅድስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ መሪነት ሥር የተያያዘውቸው ጸረ የወሲብ ዓመጽ ትግል እንደምትቀጥልበት በማረጋገጥ፣ ውሁዳን የውሉደ ክህነት አባላት የፍጸሙት የወሲብ ዓመጽ የብዙሃኑ የውሉደ ክህነት አባላት የሚሰዋ ፍቅር አብነት በመከተል ለእግዚአብሔርና ለሰው ዘር የሚፈጽሙት የላቀው ወንጌላዊ ሰብአዊ አገልግሎት ፈጽሞ የሚሰርዝ እንዳልሆነም አስገንዝበው፣ ሆኖም ጸረ የወሲብ ዓመጽ ትግል መቼም ቢሆን መዛል እንደሌለበት ማሳሰባቸው ግኑኝነቱን የተከታተሉ የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ አለሳንድሮ ጂሶቲ ገለጡ።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ባሰሙት ንግግር፣ ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ ካለ መታከት ያንን ጸያፍ አስነዋሪ በተለይ ደግሞ በሕፃናት የኅብረተሰብ ክፍል ላይ በአንዳንድ ውሁዳን የውሉደ ክህነት አባላት የተፈጸመው የወሲብ ዓመጽ በማውገዝ የወንጀሉ ተጠያቂዎች ሁሉ በቤተ ክርስቲያንና በአገሮች ብሔራዊ የሕግና የፍትኅ ሂደት አማካኝነት ተገቢ ፍርዳቸው ሊቀበሉ እንደሚገባቸው ካለ ምንም ማመንታት የሰጡት መመሪያ ቀጣይነቱ ማረጋገጣቸው የጠቀሱት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዜጠኛ ጂሶቲ አያይዘውም፣ ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ እ.ኤ.አ. ግንቦት 11 ቀን 2010 ዓ.ም. ለሐዋርያዊ ጉብኝት ወደ ፖርቱጋል በተነሱበት አይሮፕላን ውስጥ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፦ ጸረ ር.ሊ.ጳ. ጸረ ቤተ ክርስቲያን የሚሰነዘረው ጥቃት ከቤተ ክርስቲያን ውጭ ብቻ ሳይሆን ከቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚመጣ መሆኑና ይኽም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚፈጸመው ኃጢአት ቤተ ክርስቲያንን የሚያሳድደው ከቤተ ክርስቲያን የሚሰነዘረው ክፋት እጅግ የከፋና አሰቃቂ ነው። በመሆኑም ከውጭ ከሚሰነዘረው ይልቅ ከቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሚሰነዘረው ጸረ ቤተ ክርስትያን ክፋት የባሰና ነው። ቤተ ክርስቲያን መንጻትና ይቅርታና ምኅረት የሚያስፈልጋት ቢሆንም ቅሉ ምኅረትና ይቅርታ የሕግና ፍትህ ሂደት የሚተካ አይደለም፣ ተጠያቂው ሁሉ በሕግ ፊት መቅረብ አለበት” እንዳሉ አስታውሰዋል።
ቅዱስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ 16ኛ የውሉደ ክህነት አባላት በፈጸሙት የወሲብ ዓመጽ ሰለባ የሆኑትን በመቀበል በተባበሩት የአመሪካ መንግሥታት በአስትራሊያ በእንግልጣር ብሎም በማልታ በፈጸሙዋቸው ዓለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ጉብኝት ወቅት ያነጋገሩ ቀዳሜ ር.ሊ.ጳ. መሆናቸው የሚታወስ ሲሆን፣ ይኽ በአንዳንድ የውሉደ ክህነት አባላት የተፈጸመው አሰቃቂው አመጽ ቤተ ክርስቲያን ከሚሰነዘርባት ጸረ ክርስቲያን ድርጊት እጅግ የከፋ መሆኑ በተደጋጋሚ እንዳሳሰቡ የሚታወስ ሲሆን፣ የክህነት ዓመት ባወጁበት ወቅት፦ “የክህነት ምሥጢር ቅዋሜ የደስታ ምክንያት ቢሆንም ቅሉ፣ በዚህ የክህነት ዓመት በአንዳንድ የውሉደ ክህነት አባላት የተፈጸመው በተለይ ደግሞ በሕጻናት ላይ የተፈጸመው የወሲብ ዓመጽ ገሃድ መውጣቱ ቤተ ክርስቲያንና ውሉደ ክህነት እንዲነጹ እግዚአብሔር ለሰው ልጅ እርባና የሰጠው ልዩ ምልክት ነው” እንዳሉ ጂሶቲ ባጠናቀሩት ዘገባ አስታውሰዋ።
ቅድስነታቸው ልኂቅ ር.ሊ.ጳ. በነዲክቶስ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 20 ቀን 2010 ዓ.ም. የአንዲት ቅድስት ሮማዊት ካቶሊካዊ ቤተ ክርስቲያን የቅርብ ተባባሪዎቻቸው ፊት ተገኝተው ባሰሙት ንግግር፦ “ከግብረ እምነትና መልካምነት የመነጨ ቁርጥ ፈቃድ ሊኖረን ይገባል፣ ለኑዛዜ ለመንጻት ዝግጅዎች መሆንና በተለይ ደግሞ የዚህ አይነቱ አሰቃቂው ወንጀልና ኃጢአት በውሉደ ክህነት አባላት ዳግም እንዳይከሰት ለክህነት ጥሪ የሚሰናዱትን በሚገባ በመከታተልና ለይቶ በማጤን ማነጽ ወሳኝ ነው” እንዳሉ ያስታወሱት የቫቲካን ረዲዮ ልኡክ ጋዚጠኛ ጂሶቲ ያጠናቀሩት ዘገባ እዚህ ላይ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.