2013-04-08 15:25:16

አርጀንቲና


RealAudioMP3 የተለያዩ የኵላዊት ቤተ ክርስቲያን የተራድዖ ማኅበራትን የሚያቅፈው “Cor Unum-ውሁደ ልብ” የተሰየመው ጳጳሳዊ ምክር ቤት በአርጀንቲና በላ ፕላታ ርእሰ ሰበካ ክልል በተከሰተው የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ ሳቢያ ለተጎዱት የአገሪቱ ዜጎች መርጃ የሚውል አርጀንቲና በሚገኘው በቅድስት መንበር ሐዋርያዊ ወኪል ቢሮ አማካኝነት 50 ሺሕ ዶላር መለገሱ የገለጠው የቅድስት መንበር መግለጫ አክሎ በተከሰተው የጎርፍ መጥለቅለቅ አደጋ ሳቢያ 57 ሰዎች ለሞት መዳረጋቸው ለማወቅ ሲቻል የተጎዳው ሕዝብ ለመደገፍ በክልሉ የምትገኘው የካቶሊካዊት ቤት ክርስትያን የተራድኦ ማኅበር መንቀሳቀሱ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.