2013-04-08 15:29:47

ሩዋንዳ


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. ሚያዚያ 7 ቀን 2013 ዓ.ም. በሩዋንዳ እ.ኤ.አ. በ 1994 ዓ.ም. የእርስ በእርስ ግጭት ሳቢያ በተከሰተው የዘር ምንጠራ ተግባር በሦስት ወራት ውስጥ ለሞት የተዳረገውን አንድ ሚሊዮን ሕዝብ ዕልቂት ታስቦ መዋሉ ሲገለጥ፣ የዚህ በቱትዚ ጎሳ ላይ የሁቱ ጎሳ የፈጸመው የዘር ምንጠራ አደጋ ጠንሳሾችና ቀዳሚ ተጠያቂዎችን ለፍርድ ለማቅረብ እ.ኤ.አ. ባለፈው ዓመት ህዳር ወር ላይ በታንዛኒያ እርሻ ከተማ እንዲቆም የተደረገው ልዩ ዓለም አቀፋዊ ፍርድ ቤት የማጣራትና የምርመራ ሂደቱ እያፋጠነ መሆኑ ለማወቅ ሲቻል፣ ስለዚሁ ዝክረ አሥረኛ ዓመት ምክንያት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት ከዘር ምንጠራው አደጋ የተረፉት በኢጣሊያ የሚኖሩት ጆርጅ ጋተራ የዘር ምንጠራ አደጋ በተቀጣጠለበት ወቅት በሩዋንዳ እንደነበሩና ሁኔታን የኖሩት በጎሳ ልዩነት የሕዝቦች መከፋፈል በሩዋንዳ በተነሳሳበት ወቅት ያደጉ ያንን ሁኔታ በቀጥታ የተሞከሩበት ጸያፍ ድርግት የቱትዚ ጎሳ በመሆናቸውም በገዛ አገራቸው ሁለተኛ ዜጋ ሆነው እንዲኖሩ ማድረጉንም ዘክረው ሁቱ 85 በመቶ ቱትዚ ደግሞ 14 በመቶ የሩዋንዳ ክፍለ ኅብረተስብ የሚሸፍን መሆኑ የውሁዳን የህብረተሰብ ክፍል ኣባል መሆን ለአደጋ የሚያጋልጥ ሆኖ ስታገኘው በእውነቱ የሚዘገንን ጸረ ሰብአዊ ተግባር ነው። እ.ኤ.አ. በ 1994 ዓ.ም. የቱትዚ ጎሳ አባላት ከምድረ ሩዋንዳና ከአገሪቱ ኅብረተሰብ ጨርሶ ለማጥፋት በወቅቱ የነበረው መንግሥት የፈጸመው የዘር ምንጠራ ድርጊት ነው ሲሉ፣ መቀመጫው በሮማ ለሆነው መልካም ስለ ሩዋንዳ የተሰየመው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ሊቀ መምበር ፍራንኮይሰ ካንድኪዲ በበኩላቸውም፣ የዘር ምንጠራው ተግባር ጸረ ሩዋንዳዊ ተግባር ነው። ስለዚህ ፈውሱም ብሔራዊ እርቅ ማረጋገጥ መሆኑ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ አስታውቀዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.