2013-04-08 15:17:09

መለኰታዊ ምኅረት


RealAudioMP3 የላቲን ሥርዓት የምትከተለው ቤተ ክርስቲያን ትላትና ዕለተ ሰንበት ሚያዝያ 7 ቀን መለኰታዊ ምኅረት ማክበሯ የሚታወስ ሲሆን፣ የዚህ በዓል ቅዋሜ ውሳኔ ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓንስ ጳውሎስ መሆናቸውም በሮማ ቅዱስ መንፈስ ዘሳሲያ በሚገኘው የመለኰታዊ ምኅረት አምልኮ ማእከል እንዲሆን ያደረጉበት ቤተ ክርስቲያን ቆሞስ ብፁዕ አቡነ ጆሰፍ ባርት ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው፦ የዚህ በዓል መንፈሳዊነት በገዛ እራሱ ጌታ በመገናኘትና በግልጸቱ አማካኝነት ለቅድስት ፋውስቲና ከለገሰው ጸጋ የመነጨ መንፈሳዊነት መሆኑ አብራርተው፣ ይኽም የእግዚአብሔር ምኅረት ከስቃዩ ከሞቱና ከትንሣኤው የሚመነጭ መሆኑ የሚያረጋገጥ በዓል ሲሆን፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በበዓለ ፋሲካ አለም አቀፋዊ ሐዋርያዊ ቡራኬ ሲሰጡ፦ በዓለ ፋሲካ የእግዚአብሔር ምኅረት ድል ያደረገበት ዕለት ነው” በማለት የሰጡት ቃል የዚህ በዓል ትርጉም በጥልቀት ገልጠውልናል ብለዋል።
ር.ሊ.ጳ. ብፁዕ ዮሓነስ ጳውሎስ ዳግማዊ እ.ኤ.አ. በአቢይ ቅዱስ 2000 ሺሕኛው ዓመት ሚያዝያ 30 ቀን 2000 ዓ.ም. ለብፅዕት ፋውስታ ኮዋልስካ ቅድስና ሲያውጁ ከበዓለ ፋሲካ ቀጥሎ ያለው እሁድ የመለኰታዊ ምኅረት ሰንበት ተብሎ በኵላዊት ቤተ ክርስቲያን እንዲከበር ወስነው መለኰታዊ ምኅረት በሞት ላይ ድል የነሣው ክርስቶስ ያደለው ጸጋ ነው በማለት ገልጠው፣ ቅድስት ፋውስታ እ.ኤ.አ. ጥቅምት 5 ቀን 1938 ዓ.ም. በ 33 ዓመት ዕድሜዋ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየች የቅድስት ድንግል ማርያም ዘምኅረቱ ደናግል ማኅበር አባል የግብረ ምኅረት ልኡክት በመሆን በዚህ ተልእኮ የተናቁት ሴቶች የኅብረተሰብ ክፍለ አባላትን በመንከባከብና በማነጽ ያገለለገለች፣ እ.ኤ.አ. የካቲት 22 ቀን 1931 ዓ.ም. በበዓለ ሓዋርያዊ መንበረ ቅዱስ ጴጥሮስ እግዚአብሔር ለቅድስት ፋውስታ በመገለጥ የምኅረቱ ጸጋና ምስል ታረጋግጥ ዘንድ የምኅረት መንፈሱ በማኖር ለዚህ ጥሪ እንደመራት ብፁዕ አቡነ ባርት ባደረጉት ቃለ ምልልስ ገልጠው፣ ቅድስት ፋውስታ አዲስ የመለኰታዊ ምኅረት አምልኮ መንፈሳዊነት ያነቃቃች ቅድስት ነች በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.