2013-04-05 15:07:45

አገናኝ ድልድይ እንዲታነጽ


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በዓለማችን አገናኝ ድልድይ እንዲታነጽ የሚያበረታቱ መሆናቸው “Civiltà Cattolica-ካቶሊካዊ ሥልጣኔ” የተሰየመው እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 6 ቀን 1850 የመጀመሪያ ሕትመቱን በማቅረብ የተመሠረተው የኢየሱሳውያን ልኡካን ማኅበር ሁለት ሳምንታዊ መጽሔት ዋና አዘጋጅ የኢየሱሳውያን ማኅበር አባል አባ አንቶኒዮ ስፓዳሮ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ ገልጠው በቅርቡ የተረጋገጠው የመጽሔቱ ኅዳሴ አስደግፈው በቅድሚያ መጽሔቱ እ.ኤ.አ. እስከ 1970 ዓ.ም. የተከተለው ቅርጽ ዳግም በማደስ የሚታከሉ ከመጽሔቱ የሚነሱት አምዶች እንደሚኖር መደረጉ ገልጠዋል። ይኽም በዓለማችን የሚታየው የመገናኛ ብዙሃን በተራቀቀና በሥነ ቀመር በተደገፈ ሥነ ምርምር መሠረት እያረጋገጠው ያለው እድገት ግምት የሰጠ ኃዳሴ መሆኑ በማብራራት፣ የመጽሔቱ ዓላማ በቤተ ክርስቲያንና በማኅብረተሰብ መካከል አገናኝ ድልድይ መፍጠር የሚል ነው። በመሆኑም ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ይኽ አገናኝ ድልድይ እንዲታነጽ የሚያበረታቱ የሚያነቃቁ የሚያንጹ ናቸው ብለዋል።
እ.ኤ.አ. ከ 1850 እስከ 2008 ዓ.ም. ያጠቃለለ የመጽሔቱ ቤተ መዘክር ጉግል ለፈጠረው እድል አመስግነው በድረ ገድ አማካኝነት በነጻ የመጽሔቱ ቤተ መዝገብ ለመጎብኘት ይቻላል። መጽሔቱ እንዲመሠረት ያደረጉ የኢየሱሳውያን ማኅበር አባላት ያነቃቃቸው ዓላማ የመጽሔቱ መሠረታዊ ቅርጽ አድርጎ በመከተል ከወቅታዊው ዓለም ጋር በማመላከት የተረጋገጠ ኃዳሴ ነው። መቀጠል የሚገባው ባህል በማስቀጠል በተለያየ ርእሰ ጉዳይ በተለያዩ የሥነ ትምህርት ዘርፎችና ምርምር ሥር የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማኅበራዊ ትምህርት የሚተነትን የሚያስተምር መሆኑ ካብራሩ በኋላ አያይዘውም ለጋዜጠኝነት አስተንፍሶ እውነት መልካም ፈቃድና ውበት የተሰኙት ናቸው። የመጽሔቱ ዓላማም እውነት መልካም ፈቃድና ውበት ላይ ያነጣጠረ ነው። የኢየሱሳውያና ማኅበር መንፈሳዊ ጉልበት የሚያንጸባረቅበት መጽሔት መሆኑ ገልጠው የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.