2013-04-05 15:11:44

መካከለኛ አፍሪቃ


RealAudioMP3 በመካከለኛ አፍሪቃ የባንጋሱ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኹዋን ኾሰ አጕይሮ ሙኞስ በሰበካቸው ከህዝባቸው ጋር ለመሆን የሚሹ ቢሆንም ቅሉ አሁንም አገሪቱ በተከሰተው ውጥረት ሳቢያ በርእሰ ከተማ ባንጉዪ ታጥረው ለመቆየት መገደዳቸው ገልጠው። አማጽያኑ ታጣቂ ኃይሎች ርእሰ ከተማ ባንጉዪ ከተቆጣጠሩ ወዲህ በአገሪቱ አሁንም መረጋገት የሌለና ብጥብጥ ፍርሃት የተሞላው ነው። ብዙዎች የታጣቂ ኃይል አባላት ነን በሚል የሐሰት ሽፋን የተለዩ ወንጀል ሲፈጽሙም ይታያል እንዳሉ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።
ስርቆት ዝርፍያ ግድያ ተስፋፍቶ ይታያል። ወደ ሰበካቸው የሚወስደው አውራ ጎዳና እ.ኤ.አ. ከባለፈው ታህሳስ ወር 2012 ዓ.ም. ወዲህ መዘጋቱና እንዲሁም የአየር ማረፊያዎች ጭምር በተለያዩ የአገልግሎት መስጫና በነዳጅ እጥረት ሳቢያ ከአገልግሎት ውጭ መሆኑ የገለጡት ብፁዕ አቡነ ኹዋን ኾሰ አጕይሮ ሙኞስ አያይዘውም የገዳማት ንብረት እየተዘረፈ ነው። ብዙ ወራት እያስቆጠረ ያለው በባንጋሱ የአገልግሎት መሳጭ መቋረጥ ሳቢያ የክልሉ ነዋሪ ሕዝብ ለተለያየ ችግር ተጋልጦ ይገኛል፣ ስለዚህ ጸጥታና መረጋጋት ካልተረጋገጠ የሕዝቡ ሁኔታ እጅግ እየተባባሰ እንደሚሄድ ነው። በትክክል የአመጽያኑ ኃይል አባላትና የሃሰት አባላት ለመለየት እጅግ አስቸጋሪ ሆኖ ነው ያለው። የክልሉ ሁኔታ በርግጥ ታጣቂ ኃይሉ ርእሰ ከተማይቱ ከተቆጣጠረበት ቀዳሜ ቀን ወዲህ መጠነኛ መሻሻል እያሳየ ቢሆንም ቅሉ የጸጥታና ደህንነት ጉዳይ በሚገባ ተሻሽሎ ሰላም እንደሚረጋገጥ ተስፋ አለን እንዳሉ ፊደስ የዜና አገልግሎት አስታወቀ።







All the contents on this site are copyrighted ©.