2013-04-03 18:39:14

የር.ሊ.ጳ ሳምንታዊ የዕለተ ሮብ አጠቃላይ ትምህርተ ክርስቶስ፤


ውድ ወንድሞችና እኅቶች፤ እንደምን አደራችሁ፤ ዛሬ ስለ ዓመተ እምነት የሚመለከት ትምህርተ ክርስቶስ እናቀርባለን፣ በጸሎተ ሃይማኖት “በቅዱስ መጽሐፍ እንደተመለከተው በሶስተኛ ቀን ከሞት ተነሣ” የሚለውን ሓረግ እንደግማለን፣ ባለነው ወቅት እያከበርነው ያለን የክርስትና መልእክት ማዕከል የሆነውና ከመጀመርያ የክርስትና ምስረታ ጀምሮ ወደ እኛ እንዲደርስ ያስተጋባው፣ የኢየሱስ ትንሣኤ ነው፣ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ቆሮንጦስ ሰዎች ሲጽፍ “እኔ ደግሞ የተቀበልሁትን ከሁሉ በፊት አሳልፌ ሰጠኋችሁ እንዲህ ብዬ። መጽሐፍ እንደሚል ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን ሞተ፥ ተቀበረም፥ መጽሐፍም እንደሚል በሦስተኛው ቀን ተነሣ፥ ለኬፋም ታየ በኋላም ለአሥራ ሁለቱ፤”(1ኛ ቆሮ 15፤3-5) ይላል፣ ይህ አጠር ያለ መግለጫ ከሞት የተነሣው ክርስቶስ ለቅዱስ ጴጥሮስና ለአሥራ ሁለቱ ሓዋርያት በመታየት በተገለጠው ምሥጢረ ፋሲካ ማመንን ያመለክታል፣ የኢየሱስ ሞትና ትንሳኤ የተስፋችን አንኳር ነው፣ አለ የኢየሱስ ሞትና ትንሣኤ እምነት ተስፋችን ደካማ በሆነ ነበር፤ እንዲያው ተስፋም ሊሆን አይችልም ነበር፤ እላይ በጠቅሰነው መልእክት ሓዋርያው “ክርስቶስም ካልተነሣ እምነታችሁ ከንቱ ናት፤ እስከ አሁን ድረስ በኃጢአታችሁ አላችሁ” (ቍ 17) በማለት ይህንን ያረጋግጥልናል፣ ባለፉት ዘመናት የኢየሱስ ትንሣኤን ለማጭለም ብዙ ሙከራዎች ተደረጉ፤ በአማኞች ማሃከልም ሳይቀሩ ጥርጣሬዎች ተነሥተው ነበር፣ ያ እምነት ጠንካራ አልነበረም፣ ይህም የሆነበት ምክንያትም ጥልቀት አለመኖር ወይንም ግድየለሽነት ማለትም ከእምነት አብልጠን በምንመለከታቸው ብዙ ነገሮች ተይዘን ስንገኝ ወይንም የዚህን ምድር ሕይወት ብቻ በማሰብ ስንኖር ነው፣ ሆኖም ግን ለላቀው ተስፋ ልባችንን የሚከፍተው ትንሣኤ ነው፤ ምክንያቱም ሕይወታችንና የመላው ዓለም ሕይወት ለዘለዓለማዊው እግዚአብሔር እና ለሙሉ ደስታ ይከፍተዋል፣ ክፋት ኃጢአትና ሞት ሊሸነፉ እንደሚችሉም እርግጠኝነት ይሰጠናል፣ ይህም ዕለታዊ ኑሮ አችንን በመተማመን እና በብርታት እንድንኖረውና ኃላፊነትም እንዲሰማን ያደርገናል፣ የክርስቶስ ትንሣኤ የእያንዳንዱ ቀን ኑሮአችንን በአዲስ ብርሃን ያሸብርቀዋል፣ የክርስቶስ ትንሣኤ ኃይላችን ነው፣
ነገር ግን ይህ በትንሣኤ ክርስቶስ ያለን እምነት እውነት እንዴት ወደ እኛ ተላለፈ? ብለን የጠየቅን እንደሆነ በአዲስ ኪዳን ሁለት ዓይነት ምስክርነቶች አሉ፣ አንዱ የእምነት ምስክርነት ሆነው የእምነቱ አንኳር አጠር ባሉ ሓረጎች የሚገልጡ ናቸው፣ ሌላው ደግሞ የትንሣኤ ሁኔታና ከእርሱ ጋር የሚያያዙ ነገሮች የሚተነትኑ ታሪኮች ናቸው፣ የመጀመርያ የእምነት መግለጫ ሆኖ እላይ እንዳልነው ወይም በሮማውያን መልእክት ላይ ተመልክቶ እንዳለው “በአፍህ ኢየሱስ ጌታ ነው ብለህ ካወጅክ በልብህም እግዚአብሔር ከሞት እንዳነሣው ካመንክ ትድናለህ” (10፤9) የሚለው ነው፣ ቤተ ክርስትያን ከመጀመርያ ይዛ በኢየሱስ ምሥጢረ ሞትና ትንሣኤ ጽኑ እና ጥርት ያለ ትምህርት ነበራት፣ በዛሬው ትምህርታችን ስለሁለተኛው ክፍል ያልነው ታሪካዊ ምስክርነቶች በወንጌል መሠረት እንመለከታለን፣ የኢየሱስ ትንሣኤ አንደኛ ምስክሮች ሴቶች ነበሩ፣ ጥዋት ተነሥተው የኢየሱስ ሬሳን ለመቅባት ወደ መቃብር ሲሄዱ የመጀመርያውን ምልክት ማለት ባዶ መቃብርን ያገኛሉ (ማር 16፤1)፣ ከዛም የእግዚአብሔር መል እክተኛ የሆነ መል አክን ያገኛሉ እርሱም የተሰቀለው ናዝራዊው ኢየሱስ እዚህ የለም ከሙታን ተነሥተዋል (ቍ 5-6) ይላቸዋል፣ ሴቶች በፍቅር ተገፍተው ይህንን የእምነት ብሥራት ይቀበላሉ፣ ያምናሉም፤ ለገዛ ራሳቸው ብቻ ይዘውት ዝም አይሉም፤ ወዲያውኑ ደግሞ ለሌሎች ያስተላልፉታል፣ ኢየሱስ ሕያው እንደሆን ማወቅ የሚሰጠውን ደስታ እና ልብን የሚሞላ ተስፋ አምቀው ሊይዙት አልቻሉም፣ ይህ ዓይነት ለውጥ በሕይወታችንም መከናወን አለበት፣ የክርስትያን መሆን ደስታ ይሰማን! ክፋትንና ሞትን አሸንፎ ከሙታን ተለይቶ በተነሣ እናምናለን! ይህንን ደስታና ብርሃን በሁሉም የሕይወታችን ቦታዎች ለማዳረስ የመውጣት ብርታት ይኑረን፣ የክርስቶስ ትንሣኤ ከሁሉ የላቀ እርግጠኝነታችን ነው፤ ከሁሉ የከበረ መዝገባችንም ነው! እንታይ ይህንን እርግጠኝነት ይህንን መዝገብ ለምን ከሌሎች ጋር አንካፈለውም? ለእኛ ብቻ አይደለም ለሌሎች መስጠት ያለብን ከሌሎች ጋር መካፈል ያለብን ነው፣ ይህ ነው የእኛ ምስክርነት መሆን ያለበት፣
ሌላ ነገርም አለ፣ በአዲስ ኪዳን የእምነት መግለጫ የትንሣኤ ምስክሮች በሚመለከት ወንዶች ብቻ ማለትም ሐዋርያት ብቻ ይዘከራሉ፤ ሴቶች ግን አይዘከሩም፣ ለምን እንዲህ ሆነ ያልን እንደሆነ ያኔት በነበረው የአይሁዳውያን ሕግ የሴት ልጆችና ሕጻናት ተጨባጭ ወይም ታማኝ ምስክርነት ሊሰጡ አይችሉም ነበር፣ በወንጌላውያን የተመለከትን እንደሆነ ግን ሴቶች ተቀዳሚና መሠረታዊ ሚና አላቸው፣ እዚህ ላይ የትንሣኤ ታሪካዊነት በሚመለከት አንድ ድጋፍ ልናገኝ እንችላለን፣ ጉዳዩ የፈጠራ ቢሆን ኖሮ ከሴቶች ምስክርነት ባልተሳሰረም ነበር፣ ወጌላውያን የሆነውን ነገር እንዳለ ያቀርቡልናል፣ ሴቶቹ የመጀመርያ የትንሣኤ ምስክሮች መሆናቸውን አስፍረውታል፣ ይህ የሚያሳየን እግዚአብሔር የሰው ልጆች መለኪያ እንደማይጠቀም ነው፣ የኢየሱስ ልደት የመጀመርያ ምስክሮች እንዲሆኑ የተመረጡት ገሮችና ትሑታን የሆኑ እረኞች ሲሆኑ፤ የትንሣኤው የመጀመርያ ምስክሮች ደግሞ ሴቶች ሆነዋል፣ ይህ ጥሩ ምርጫ ነው፤ የሴቶች ተልእኮም እንደእናቶች ለልጆቻቸው እና ለልጅ ልጆቻቸው ኢየሱስ ሕያው እንደሆነ ከሞት እንደተነሣ ምስክርነታቸውን መስጠት አለባቸው፤ ለእግዚአብሔር የሚያስፈልገው ልባችን ነው፤ ለእርሱ ምን ያህ ክፍት እንደሆንና እንደሕጻናት በእርሱ ምን ያህል እንደምናምን ነው የሚመለከተው፣ ሆኖም ግን ይህ ፍጻሜ በሌላ በኩል ሴቶች በቤተ ክርስትያንና በእምነታችን ጉዞ ለጌታ እምነት የልቦቻችን በር ለመክፈት ልዩ ሚና እንደነበራቸው ገናም እንዳላቸው ያመለክተናል፣ የእምነት ገጽታ የየዋህነት ገጽታትና የፍቅር ጥልቀት ስላለው ጌታን እንድንከተለውና ገጽታውን ለሌሎች እንድናስተላልፍ ሴቶች ይረዱናል፣ሐዋርያትና ደቀ መዛሙርት ለማሳመን ብዙ ይደክማሉ፣ ሴቶች ግን እንደዛ አይደለም፣ ቅዱስ ጴጥሮስ ወደ መቃብር ይሮጣል በባዶ መቃብር ፊትም ይቆማል፤ ቶማስ እንዲያምን እጆቹን በኢየሱስ ቍስሎች ማኖር አለበት፣ በእምነታችን ጉዞ እግዚአብሔር እንደሚያፈእቅረን ማወቅና መስማት እንድታፈቅረው አለመፍራት አስፈላጊ ነው፣ እምነት በአፍና በልብ በቃልና በፍቅር ይምሰከራል፣
ኢየሱስ ከሞት ተነሥቶ ለሴቶች ከተገለጠ በኋል ለሌሎችም ይታያል፣ በአዲስ ባህርይም ይቀርባቸውል፣ የተሰቀለው ኢየሱስ ነው ነገር ሰውነቱ ክብር የሞላበት ሆነ ቀድሞ ወነበረበት ምድራዊ ሕይወት አልተመለሰም አዲስ ባህርይ ለበሰ፣ በመጀመርያ ሊያውቁት አልቻሉም፣ በድምጹና በቃላቱ ዓይኖቻቸው ሊከፈቱ ቻሉ፣ ከሙታን ከተነሣው ክርስቶስ ጋር መገናኘት ይለውጣል፤ አዲስ የእምነት ኃይል የማይነቃነቅ መሠረት ይሰጣል፣ ለእኛም ከሙታን የተነሣ ጌታ ሊያሳውቀን የፈለጋቸው ብዙ ነገሮች ሰጥቶናል፤ መጽሐፍ ቅዱስ፤ ቅዱስ ቍርባንና ሌሎች የቤተ ክርስትያን ምሥጢራት እንዲሁም ምግባረ ሠናይ ሁላቸው ከሙታን የተነሣ ክርስቶስ ብርሃን ይሰጡናል፣ ከሙታን በተነሣ ክርስቶስ ብርሃን እንብራ በኃይሉ እንድንለወጥ እንፍቀድለት፤ እንዲህ በማድረጋችን በዓለም ውስጥ የሞት ምልክቶች ለሕይወት ምልክቶች ቦታ ይለቃሉና፣
በአደባባዩ ብዙ ወጣቶች እየታዩ ናቸው፣ እናንተ ወጣቶች ይህንን እርግጠኝነት አስታውቁ፣ ጌታ ሕያው ነው! በሕይወታችን ጉዞ በጐናችን እየተጓዘ ይሸኘናል፣ ተል እኮ አችሁ ይህ ነው፤ ይህንን ተስፋ ወደፊት እንዲገስግስ አደርጉት፣ በዚሁ ተስፋ እንድትታነጹ ይሁን! ይህ ተስፋ እንደ መልሕቅ ሆኖ በሰማይ ስላለ ጸንታችሁ በእርሱ ተሳስራችሁ ተንጠልጠሉ፤ በመልሕቁ ጠብቃችሁ ተስፋን ወደሁሉ አዳርሱ፣ እናንተ የኢየሱስ ምስክቶች ምስክርነታችሁን ወደፊት አራምዱ፣ ኢየሱስ ሕያው ነው ይህም ተስፋ ይሰጣችኋል! ለዚሁ በውግ ያ በክፋትና በኃጢአት ላረጀው ዓለማችን ተስፋ ይሰጣል፣ ወጣቶች ወደፊት!!








All the contents on this site are copyrighted ©.