2013-04-03 15:19:46

ብፁዕ ካርዲናል ስኮላ፦ ቅዱስ አባታችን ኤውሮጳ በገዛ እራስ ውስጥ ከመዘጋት ፈተና ትላቀቅ ዘንድ አቢይ ድጋፍ ናቸው


RealAudioMP3 በኢጣሊያ የሚላኖ ከተማ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ስኮላ ትላትና ከሰበካቸው የተወጣጡት 10 ሺሕ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ መንፈሳዊ ንገደት የፈጸሙትን ምእመናን መርተው እዛው በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ለመንፈሳዊ ነጋድያን መሥዋዕተ ቅዳሴ አሳርገው ባሰሙት ስብከት፦ “ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ኤውሮጳ በራስ ተዘግታ ከመኖር ፈተና ትላቀቅ ዘንድ አቢይ ድጋፍና መሪ ናቸው” ካሉ በኋላ አክለውም፦ “በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ በቅዱሳት ሐዋርያት ቅዱስ መቃብር ሥፍራ መንፈሳዊ ንግደት መፈጸም አቢይ ጸጋ እምነትን የሚያጎለብት በእምነት እንዲበረታ የሚደገፍ ቅዱስ ተገባር ነው። ቅዱስ አባታችን ለሁሉም ቅርብ በመሆን በሚፈጽሙት ቅዱስ ተግባር ሁሉ በሁሉም የሚነገር ብቻ ሳይሆን ትህትናቸውና ቅርበታቸው የሚያስደንቅ ነው። በገዛ እራስ መዘጋት ልምድ ያደረገው በእምነት የዛለው ጥንታዊው የኤውሮጳ ክፍለ ዓለም በራስ ከመዘጋት ተላቆ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አብሮ እንዲጓዝ ለማድረግ የሚያስችለው መንገድ በቃልና በሕይወት ጠቋሚ ናቸው” ብለዋል።
“ከኢየሱስ ጋር አብሮ መሆኑ ከእርሱ ጓር አብሮ መጓዝ ማለት” ሉት ብፁዕ ካርዲናል ስኮላ፦ ለሁሉም “በምህረት እጅግ የላቀው መኃሪ ከሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር መሆንና የተስፋ አናሥር የኢየሱስ መኃሪነት መኖር ማለት ነው። እኛ የኽንን የጌታችን ኢየሱስ ምኅረት አብሳሪዎች ለመሆን የተጠራን ነን፣ ስለዚህ ምኅረቱ መኖርና ኢየሱስን በሙላት ለመስበክ የተጠራን ነን” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.