2013-04-03 15:10:41

ቀዳሜ ሰዓተ ክርስትና


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ትላትና በቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ ትሕተ መሬት በሚገኘው የእምነት ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ ቅዱስ አጽም በታቀበበትና እንዲሁም የቅዱስ ጴጥሮት ተከታይ አርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት መቃብር ሥፍራ በመሄድ ቀዳሜ ሰዓተ ክርስትና መፈጸመማቸው ሲገለጥ፣ ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ስለ ፈጸሙት መንፈሳዊ ንግደት በማስመልከት የቅዱስ ጴጥሮስ ባሲሊካ ሊቀ ካህናት ብፁዕ ካርዲናል አንጀሎ ኮማስትሪ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ “ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የአንድ ሺሕ ስምንት መቶ ዓመታት ታሪክ ያለው ቅዱስ ሥፍራ ዘንድ በመሄድ የፈጸሙት መንፈሳዊ ንግደት በቅድሚያ የሁለት ሺሕ ክፍለ ዘመን ግብጻዊ የመቃብር ሥፍራ በብዙ እምነት ያልተቀበሉ መካከል ክርስትና የተቀበለ የአንድ ክርስቲያን አጽም እንዳለ እንደተገለጠላቸው ቅዱስነታቸው እኛም በዚህ እምነት እምቢ ባለው ዓለም መካከል የምንገኝ ክርስቲያኖች ነን በማለት፣ ቀጥለውም የኢስታቲሊዩስ ከሁሉም ጋር ተግባብቶ አለ መግባባትን በማስውገድ ይኖር ነበር የሚል ጽሑፍ ያረፈበት መቃብር ከተመለክቱ በኋላ የሚገርም ነው ይህ ጽሑፍ የሕይወት መርሃ ግብር መሆን አለበት በማለት አስተያየት ሰጥተው፣ ቀጥለውም የቅዱስ ጴጥሮስ ሰማዕት ቅዱስ አጽም ያረፈበት ቅዱስ ቀለመንጦስ ቤተ ጸሎት ደርሰው ተንበርክከው በጽሞና ጸልየው እንዳበቁ እሳቸውና ከሳቸው ጋር የነበርን ሁላችን የቅዱስ ጴጥሮስ የእምነት ኑዛዜ ‘ጌታ ሆይ ወዴት እንሄዳለን አንተ የዘለዓለም ቃለ ሕይወት አለህና’ የሚለውን ጸሎት በመድገም፣ በመቀጠምል የኣርእስተ ሊቃነ ጳጳሳት የመቃብር ሥፍራ ሐዋርያዊ ንግደት በመፈጸም ጸልየዋል” ካሉ በኋላ ይኽ የቅዱሳንና የሰማዕታት ቅዱስ አጽም ያረፈበት ቅዱስ ሥፍራ በአሁኑ ዘመን ስለ እምነት የደም ሰማዕትነት የሚቀበሉት የቤተ ክርስቲያን ልጆች በመንፈስ የሚያቅፍ ቅዱስ ሥፍራ ነው፣ እምነት ጽናት ይጠይቃል በጽናትና በታማኝነት የሚኖር እምነት ብርቱ ስለ ክርስቶስ የሚኖር ሕይወት ምስክር ነው በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.