2013-04-01 16:24:45

የር.ሊ.ጳ የዕለተ ፋሲካ መልእክት፤


ውድ የሮማና የመላው ዓለም ወንድሞችና እኅቶች! መልካም ፋሲካ! መልካም ፋሲካ!
ክርስቶስ ከሙታን ተነሣ! የሚለውን ይህንን የምስራች ዜና ሳበስራችሁ ታላቅ ደስታ እየተሰማኝ ነው፣
ይህ ምስራች በእያንዳንዱ ቤት በእያንዳንዱ ቤተሰብ በተለይ ደግሞ ብዙ ሥቃይ ባለበት በሆስፒታሎች በወህኒ ቤቶች ሊደርስ ምኞቴ ነው፣ ከሁሉ በላይ ደግሞ በሁላችን ልብ እንዲደርስ እፈልጋለሁ፣ ምክንያቱም እግዚብሔር ይህንን ምስራች በልባችን ስለሚያኖረው ነው፣ ክርስቶስ ከሙታን ተነሣ! ላንተ የሚሆን ተስፋ አለ! ከእንግዲህ ወዲህ በኃጢአትና በክፋት ግዛት አይደለህም፣
ፍቅር አሸነፈ! ምሕረት አሸነፈ! ዘወትር የእግዚአብሔር ምሕረት ያሸንፋልና፣ እኛም! ወደ ኢየሱስ መቃብር ሄደው መቃብሩን ባዶ እንዳገኙት የኢየሱስ ደቀመዛሙርት የነበሩ ሴቶች ይህ ፍጻሜ ምን ትርጉም ይኖረው ይሆን ብለን መጠየቅ እንችላለን (ሉቃ 24፡4) ኢየሱስ ከሙታን ተነሣ ስንል ምን ትርጉም አለው? የእግዚአብሔር ፍቅር ከክፋትና ከሞት እጅግ ያየለ እንደሆነ ያመለክታል፣ የእግዚአብሔር ፍቅር ሕይወታችንን ሊለውጥ ይችላል ማለት ነው፣ በልቦቻችን ውስጥ ያሉትን ምድረበዳዎች እንዲያብቡ ያደርጋቸዋል ማለት ነው፣ የእግዚአብሔር ፍቅር ሊያደርገው የሚችለው ይህንን ነው፣ የእግዚአብሔር ልጅ ሰው የሆነውም በዚህ ፍቅር ነው፣ በዚህም የትሕትና መንገድ በመምረጥ ራሱን እስከ መሰዋት ደርሰዋል፣ ከእግዚአብሔር ይለይ ወደ ነበረው እስከ ሲኦል ወረደ፣ ይህ የምሕረት ፍቅር ሞቶ የነበረው የኢየሱስ ሬሳን በብርሃን እንዲፈነድቅ አደረገው፤ ለወጠው ወደ ዘለዓለማዊ ሕይወትም አሸጋገረው፣ ኢየሱስ ከሙታን ሲነሳ ወደ ቀድሞው ምድራዊ ሕይወት አልተመለሰም፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ክብር ገባ፤ እዛም የገባው ሰብ አውነታችንን ለብሶ ነው፤ በዚህም የተስፋ መጻኢ በር ከፈተልን፣ እየውላችሁ! ፋሲካ ማለት ይህ ነው፣ የሰው ልጅ ከኃጢአት እና ከክፋት ባርነት ወደ ፍቅርና ወደ በጎ ነጻነት የሚሸጋገርበት ፀአት ነው፣ ምክንያቱም እግዚአብሔር ሕይወት ነው፣ ሕይወት ብቻ ነው፤ እኛ ሕያው ሰዎችም የእርሱ ክብር ነን (ቅ.ኤረነዎስ)
ውድ ወንዶምችና እኅቶች! ክርስቶስ ላንዴና ለመጨረሻ ስለሁላችን ሞቶ ከሙታን ተነሣ፤ ነገር ግን ይህ ከኃጢአት እና ከክፋት ባርነት ወደ ፍቅርና ወደ በጎ ነጻነት የሚያሸጋግር የትንሣኤ ኃይል ተጨባጭ በሆኑ የኑሮአችን ሁኔታዎች በማንኛው ዕለታዊ ጉዞአችን ሁል ጊዜ እውን መሆን አለበት፣ ዛሬም ቢሆን! የሰው ልጅ ማቋረጥ ያለባቸው ስንት ምድረበዳዎች አሉ? ከሁሉ በላይ ደግሞ የእግዚአብሔር እና የጓደኛ ፍቅር በሚጎድልበት በሰው ልብ ውስጥ ያለው ምድረበዳ! እንዲሁም ፈጣሪ በሰጠንን በሚሰጠን ፍጥረት ማድረግ ያለበትን ጥበቃ በመዘንጋት! ሆኖም ግን እጅግ የደረቀውን መሬትን ሳይቀር ሊያለማና ሊያሳብብ የሚቻለው የእግዚአብሔር ምሕረት በደረቁት አጥንቶች ሕይወት ለመዝራት ይችላል (ሕዝ 37፤1-14) ለሁላችሁ የማቀርበው ጥሪ እነሆ! የክርስቶስ ትንሣኤ ጸጋን እንቀበል፣ በእግዚአብሔር ምሕረት እንድንታደስ እንፍቀድ፣ ኢየሱስ እንዲያፈቅረን እንፍቀድለት፣ የእርሱ ፍቅር ኃይል ሕይወታችንን ሊለውጠው እንፍቀድለት፣ እግዚአብሔር መሬትን ሊያጠጣበት የሚችልበት መስኖ እና ፍጥረትን ሁሉ በመጠበቅ ፍትሕና ሰላምን እንድያሳብብ፤ የዚህ ምሕረት መሣርያም እንሁን፤እንዲህ በማድረግም ከሙታን የተነሣው ኢየሱስን፤ ሞትን ወደ ሕይወት፤ ጥላቻን ወደ ፍቅር፤ ቂም በቀልን ወደ ምሕረት፤ ጦርነትን ወደ ሰላም እንዲለውጠው እንለምነው፣አዎ! ክርስቶስ ሰላማችን ነው፤ በእርሱ አማካኝነትም ለመላው ዓለም ሰላም እንማጠናለን፣ሰላም ለመሃከለኛው ምሥራቅ! በተለይ ደግሞ በእስራኤላውያንና በፍልስጥ ኤማውያን መሃከል ሰላም ይሁን፣እነኚህ ሰዎች የስምምነት መንገድ ለማግኘት እየጣሩ ስለሆነ ብዙ ጊዜ ያስቆጠረውን ግጭት እንዲቆጩ በብርታትና በዕርቀ ምሕረት ወደ ድርድር እንዲመለሱ ዘንድ እንጸልይ፣ ሰላም ለኢራቅ ይሁን፤ ሁሉ ዓመጽ ላንዴና ለመጨረሻ እንዲቆም ይሁን፤ከሁሉ በላይ ደግሞ ለተወዳችዋ ሲርያ፤ በግጥቱ ለቆሰሉ ሕዝቦችዋ እና እርዳታና መጽናናት እየተጠባበቁ ላሉ ስፍር ቍጥር ለሌላቸው ስደተኞችዋ ሰላም ይሁን፣ ስንት ደም ነው የፈሰሰው! ለፖሎቲካዊ ቀውሱ መፍትሔ እስኪገኝ ድረስ ሕዝቡ ገና ስንት ስቃይ መቀበል አለበት?የብዙ ደማዊ ግጭቶች ሜዳ ሆና ላቸው አፍሪቃ ሰላም ይሁን፤በማሊ አንድነትና መረጋጋት እስዲገኝ ዘንድ እንጸልይ፤የብዙ ንጹሓን ሕይወቶች በስጋት ውስጥ የዘፈቀው ሕጻናትም ሳይቀሩ እያገቱ ያሉ የአሸባሪዎች ቡድኖችና በማያቋርጡ የጥፋት ደፈጣዎች እየተራመሰች ላለችው ናይጀርያ ሰላም ይሁን፣በምሥራቃዊው ደሞክራስያዊ ኮንጎ እና ብዙ ሰዎች ቤት ንብረታቸውን ጥለው በመሸሽ ገና በፍርሓት በሚኖርባት በመሃከላኛ የአፍሪቃ ሪፓብሊክ ሰላም ይንገሥ፣ በኤስያ ሰላም ይሁን፤ ከሁሉ በላይ ደግሞ በኮርያ ደሴት፤ በሁለቱም ኮርያዎች ያሉ ልዩነቶች ተቀርፈው ወደ አዲስ የዕርቅ መንፈስ እንዲያመሩ እንጸልይ፣ በስስት ተከፋፍሎ በቀላሉ ትርፍ ለማግኘት ለሚጥረው ለመላው ዓለም ሰላም ይሁን፤ በግል ጥቅም ታውሮ የሰው ልጅ ሕይወትና ቤተሰብን እየተፈታተነ ነው፣ ይህ የግል ጥቅም በዚሁ በሃያኛው ክፍለ ዘመን የሰው ልጅ ባርነት እንዲስፋፋ እያደረገ ነው፣ በሰው ልጅ መዋዋል የዚሁ የሃያኛ ክፍለ ዘመን የሰፋ ባርነት ነው፣ በዕጸ ፋርስ ዝውውርና እኩል ባልሆነ የባህርያዊ ሃብት ክፍፍል በሚፈልቁ ዓመጾች ተተራምሳ ለሚገኘው ለመላው ዓለም ሰላም ይሁን፣ ለዚችው ምድራችን ሰላም ይሁን! ከሙታን የተንሣው ኢየሱስ የባህርያዊ አደጋ ሰላብ ለሆኑ ሁሉ መጽናናቱን በመስጠን እያንዳንዳችን ኃላፍነታውያን የተፈጥሮ ጠባቂዎች እንድሆን ያስችለን፣
ውድ ወንድሞችና እኅቶች! ከሮማና ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ለምታዳምጡኝ ሁላችሁ የመዝሙረ ዳዊት ጥቅስን ላቅርብላችሁ እወዳለሁ፤ “ቸር ስለሆነና ፍቅሩም ዘላለማዊ ስለሆነ እግዚአብሔርን አመስግኑ፣ የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ “የእግዚአብሔር ፍቅር ዘለዓለማዊ ነው” ይበሉ”፣ (መዝ 117፡1-2)
ውድ ወንድሞችና እኅቶች፤ በዚሁ የክርስትና ማእከል በሆነችው አደባባይ ከሁሉም የዓለም ክፍሎች የመጣችሁ፤ እንዲሁም በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን አማክኝነት እየተከታተላችሁ ለምትገኙ ሁሉ፤ መልካም ፋሲካ እያልኩኝ መልካም ምኞቴን እንደገና እገልጣለሁ፣
በየዓመቱ በዚሁ ዕለት በሙሉ ኃይል የሚታደሰውን የደስታ የተስፋና የሰላም መልእክትን ወደ ቤተሰቦቻችሁና ወደ ሃገሮቻችሁ እንድታደርሱ ይሁን፣ ኃጢአትንና ሞትን ያሸነፈ! ከሙታን የተነሣ ጌታ የሁላችሁ መከታ ይሁን በተለይ ደግሞ ለደካሞችና ለድሃዎች!እዚህ በመገኘታችሁ ስለ እምነት ምስክርነታችሁን አመሰግናለሁ፣ እጅግ ውብ የሆኑ አበቦች ላበረክተችው ነዘርላንድ ልዩ ምስጋናየና አሳብየን እገልጣለሁ፣ በድጋሚ ሁላችሁ እና መላው ዘመደ አዳም፤ የፍትሕ የፍቅርና የሰላም ጠባቂዎች እንድትሆኑ ከሙታን የተነሣው ክርስቶስ ይምራችሁ፣








All the contents on this site are copyrighted ©.