2013-04-01 15:03:48

እመ ወድንግለ ጽሙረ


RealAudioMP3 በቢዛንታይን በምትገኘው ቤተ ክርስትያን ጥንታዊ የሃይማኖት ቅርስ የሆነው ቀዳም ዘስኡር ይኽም የምእመናን እይታ በአመ አምላክ ላይ የሚጸናበት ሁሉም እይታውን በእርሷ ዘንድ የሚያኖርበት ሰዓተ ዘማርያም ተብሎ የሚገለጠ ማርያም በኢየሱስ ክርቶስ መስቀል ሥር በመሆን የርእሱን የላቀው ጥልቅ ስቃይ ተካፋይ በመሆን የሚሰቃየው ልጅዋን በእቅፍዋ በመቀበል እመ ቤተ ክርስትያን የሆነችበት ዕለት የሚስተነተንበት ቀን መሆኑ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ቃለ ምልልስ ያካሄዱት ጳጳሳዊ የሥነ ማርያም ቲዮሎጊያ መንበረ ጥበብ ዋና አስተዳዳሪ የሥነ ማርያም ቲዮሎጊያ ሊቅ አባ ሳልቫቶረ ማሪያ ፐረላ ገልጠው፣ ይኽ በምሥራቃውያን ጥንታዊ ሊጡርጊያና መንፈሳዊነት አናስር ያለው ቅዱስ ባህል ነው። ይኸ የምስራቅ ሥርዓት መንፈሳዊነትም የዚህ የሥነ ማርያም ቲዮሎጊያ ሊቅ አባ ቶኒዮሎ በቀዳም ዘስኡር እንዲኖር ጥልቅ ትብብር ማድረጋቸውንም አስታውሰው፣ ቀዳም ዘስዑር ኵላዊት ቤተ ክርስቲያን በጽሞና በጸጥታ በመሆን ቀኑ የማርያም ጽሞናና ጸላይነቷ የሚኖርበት ቀን ሲሆን፣ እግዚአብሔር በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አንድያ ልጁ ለሰው ልጅ የፈጽመው ተስፋ ሁሉ በእምነት የመጠባበቅ መንፍሳዊነቷና ማርያም ለቤተ ክርስቲያንና ለሰው ዘር አብነት መሆንዋ የሚስተነተንበት ዕለት ሲሆን፣ ማርያም የእምነት ብስለቷ በሙላት የተረጋገጠበት እርሱም በመስቀል ስር በመሆን ከተሰቀለው ልጇ ሥር በመሆን የኖረቸው ፍጹም እምነት የተገለጠበትና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ማርያም የቤተ ክርስትያን እናት የመሆንዋ ቅዋሜ ያረጋገጠበት ትንሳኤን በእምነት በጸሎት በተስፋ የምትጠባበቅበት ዕለት ነው ብለዋል።
ደቀ መዛሙርቱ ቅዱስ መጽሐፍ በሙላትና በፍጻሜ ካለ መረዳታቸው ምክንያት ኢየሱስን ሲክዱት ታይተዋል። ሆኖም ግን ቅዱስት ድንግል ማርያም ገና ከመጀመሪያ አንስታ በእምነት ልጇን ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስ ተክትላዋለች፣ ከእርሱ በመንፈስ ቅዱስ መሆን ምን ማለት መሆኑ በመማርዋ እርሱን መካድ የሚቻላትም አይደለችም፣ በእርሱ ቃል ዘንድ በመኖር እንደ ካዱትና ከእርሱ እንደራቁ ገዛ እራሷን ከእርሱ አላገለለችም፣ ቀዳም ዘስዑር የማርያም ሰዓት እመ ወድንግለ ጽሙረ በእግዚአብሔር ዘንድ በተወለደው በመስቀል ላይ ዛሬ በተሰቀለውና ነገ በሚነሳው እግዚአብሔር ዘንድ እንዴት መሆን እንደሚገባ በቃልና በሕይወት ታስተምረናለች።
የቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው መመረጥ የፋሲካ ጸጋ ነው። ከማርያም ጋር መሆን ከኢየሱስ ጋር መሆን ማለትና በተለይ ደግሞ እንደ ማርያም መሆን የእግዚአብሔር አብ እግዚአብሔር ወልድ መምህርና ጌታ ሐዋርያ ሆኖ ከእርሱ ጋር መሆን ማለት ነው ብለዋል። እመ ወድንግለ ጽሙረ የቤተ ክርስትያን ብቸኛው ኵላዊ ተጨባጭነት ምልክት ነው። ስለዚህ ምስራቅናን ምዕራብን የሚያስተባብር መንፈሳዊ ሁነት ነው። ማርያም የውህደት ምልክት ነች በማለት የሰጡትን ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።








All the contents on this site are copyrighted ©.