2013-04-01 14:58:44

ቅዱስ ከፈን (መግነዝ)


RealAudioMP3 እ.ኤ.አ. መጋቢት 30 ቀን 2013 ዓ.ም. በኢጣሊያ ብሔራዊ የቴሌቪዥንና የራዲዮ ጣቢያ ክፍል በሆነው በራይ ኡኖ በተሰየመው የቴሌቪዥን ጣቢያ “በእርሱ ምስል” በተሰየመው የቴሌቪዥን የሥርጭት መርሃ ግብር ሥር በቅዱስ ከፈን ላይ ያተኮረ የቲዮሎጊያ የሥነ ቅዱስ መጽሓፍ የሥነ ጥንታዊ ቅርስ የታሪክ የፍልስፍና ሊቃንት ያሳተፈ ዓውደ ጥናት መካሄዱ ሲገለጥ፣ ይኽ በዚህ በተገባው የእምነት ዓመት ዘንድ የተካተተ መርሃ ግብር ሲሆን፣ በቀጥታ ቅዱስ መግነዝ ከታቀበበት ከኢጣሊያ የቶሪኖ ከተማ ከሚገኘው ርእሰ አድባራት የተከናወነ ሥርጭት መሆኑም ለማወቅ ሲቻል፣ ስለ መርሃ ግብሩ በማስመልከትም የቶሪኖ ከተማ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ አቡነ ቸሳረ ኖሲሊያ ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ የመጀመሪያው አንድ ሰዓት የፈጀው ሥርጭት 300 በተለያየ ኅመም የተጠቁት በቅዱስ ከፈን የሚገለጠው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቃይ የሚያንጸባርቅ ስቃያቸውን የጌታ ስቃይ ሱታፌ በማድረግ የሚኖሩትን ያሳተፈ በቃለ እግዚአብሔር ላይ ያተኮረ በጸሎት በአስተንትኖ የተሸኘ ቀጥሎም ትኵረቱ ቅዱስ ከፈን ላይ ያደረገ ዓውደ ጥናት መካሄዱ ገልጠው፣ ቅዱስ ከፈን ላይ ያተኮረ መርሃ ግብር በቴሌቪዥን በቀጥታ ሲቀርብ የመጀመሪያው እ.ኤ.አ. በ 1973 ዓ.ም. መሆኑም ያስታወሱት ብፁዕ አቡነ ኖሲሊያ አክለው፣ በዚህ በእምነት ዓመት እና በአዲስ አስፍሆተ ወንጌል መርህ መሠረት የብሥራት ቃልና አስፍሆተ ወንጌል እርሱም ቅዱስ መግነዝ የሚወክለው የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሕማማትና ሞት የሚናገር ሲሆን፣ የሞትና የስቃይ ድል አድራጊነት ሳይሆን፣ ቅዱስ መግነዝ የድል አድራጊነትና የትንሣኤ ምልክት ነው። ስቃይ ላይ ያሚያተኩር ብቻ ሳይሆን ስለ ደስታ እርሱም እግዚአብሔር እጅግ ስላ ፈቀረን አንድ ልጁን ስለ እኛ አሳልፎ መስጠቱንና ከዚህ ቤዛነት የሚገኝ ሕይወት አብሳሪ ነው ብለዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በተደጋጋሚ የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው ከተሾሙበት ቀንና ሰዓት ጀምረው በሚያስደምጡት ሥልጣናዊ መልእክትና ምእዳን እቃቤ የሚል ቃል ሲጠቀሙ ተደምጠዋል። ቶሪኖ ቅዱስ ከፈን የታቀበባት ከተማ በመሆንዋን ይኸንን በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያለን እምነት ለመኖር ቅዱስ አመክንዮ ነው። ቤተ ክርስቲያን ይኸንን ቅዱስ ከፈን አቅባ የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስቃይ በድኾች በተለያየ ችግር የሚሰቃዩት ጎልቶ በተለያየ ወቅት የሚኖርና የሚገለጥ መሆኑ ታስተምራለች። የሌሎች ስቃይ ተካፋይ መሆን ብቻ ሳይሆን የሌሎችን ስቃይ የገዛ እራስ አድርጎ መኖር ስቃይ በሱታፌ መኖር ያለው አሰፈላጊነት ቅዱስ ከፈን ያስገነዝበናል። ቅዱስ ከፈን የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቃብር ጽሞና እርሱም ባዶ የሆነ ጽሞና ሳይሆን ድህነት ቡራኬ ተስፋ ለተሞላው ጽሞና ምስክር ነው በማለት የሰጡት ቃለ ምልልስ አጠቃለዋል።
ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ለዚህ በቴሌቪዥን ለተሰራጨው ቅዱስ ከፈን ላይ ላተኮረው ዓውደ ጥናት በቀጥታ ባስተላለፉት የድምጸ ምስል መልእክት አማካኝነት፦ “በቅዱስ ከፈን ዘንድ ባለው በስቃይ ምክንያት በተበላሸው ምስል የተናንሽና እጅግ በተሰቃዩት ዘንድ ያለው የስቃይ ምስል ተንጸባርቆ እናያለን በጽሞና ፍቅር ዘንድ እንሰምጣለን። ‘ልኡልና ክቡር እግዚአብሔር ሆይ የሰውን ልጅ ጨለማውን ልብ አብራ’” የሚለውን የቅዱስ ፍራንቸስኮ ዘአሲዚ በስቁል ኢየሱስ ፊት የደገመውን ጸሎት ባሰሙት ስልጣናዊ ንግግር በመድገም፦ “ቅዱስ ከፈን ማክበር በፊቱ ሆነን እናስተነትናለን እንጸልያለን፣ በዚህ ብቻ ሳንታጠር በእርሱ እንመራ ዘንድ ገዛ እራሳችንን ለእርሱ እንተው። በቅዱስ ከፈን ዘንድ ያለው ምስል ዓይኑን የከደነ የሙት ገጽ እናያለን፣ ይኽ በጸጥታና በጽሞና የሚናገረን የተዘጋው ዓይን በልባችን የሚናገረን ወደ ጎልጎታ እንወጣ ዘንድ የሚገፋፋን መስቀልን እናይ ዘንድና በጽሞና በጥልቅ በሚናገረው ፍቅር ውስጥ እንሰምጣለን” ብለዋል።
“በዚህ ቅዱስ ምስል እንድንደረስና ዓይናችን ሳይሆን ልባችንን የሚሻ በቅዱስ ከፈን አማክኝነትም እግዚአብሔር የመጨረሻና ልዩ ቃል እኛን ይደርሰናል። ከእኛ ጋር ይገናኛል። ሰው በመሆን በመካከላችን ባደረው ፍቅር አማካኝነት እግዚአብሔር በታሪካችን ሰጋ ለብሶ መጣ። እኛን ከክፋትና ከስቃይ ባርነት ነጻ ሊያወጣን የዓለምን ስቃይ ክፋት ሁሉ በገዛ እራሱ ላይ አደረገ። ይህ በቅዱስ ከፈን ዘንድ ያለው ምስል፣ በዚህ በአሁኑ ወቅት ሰብአዊ ክብራቸው ተረግጦ ተናንሽ የሆኑትን እጅግ በድኽነት ጫንቃ ስር የሚገኙትን በእጅጉ የሚያሰቃየው ጦሮነትና የተለያየ አመጽ ምክንያት የሚሰቃዩት ገጽ ተምሳል ነው። ሆኖም ተስፋ አትቁረጥ የሚል የፍቅር ኃይል ሞትን ያሸንፋል በሁሉ ላይ ድል የነሣው በእኔ ታመኑ የሚል የፍቅር ኃይል ጎልቶ ይታያል” እንዳሉ የቅድስት መንበር መግለጫ አስታወቀ።








All the contents on this site are copyrighted ©.