2013-03-29 13:37:20

ከተለያዩ ሃይማኖቶች ጋር ውይይት


RealAudioMP3 ቅዱስ አባታችን ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ ከተለያዩ ሃይማኖቶች ጋር የሚከናወነው ውይይት እንዲሁም ለውህደት ያነጣጠረው ከተለያዩ አቢያተ ክርስትያን ጋር የሚካሄደው ውይይት ካለ ምንም ማመንታት እንዲቀጥልና ሁሉም እንደ የኃላፊነቱ ለዚህ ውይይት ተገቢ አስተዋጽኦ እንዲያበረክት የቅዱስ ጴጥሮስ ተከታይ ሆነው ከተመረጡበትና የቅዱስ ጴጥሮሳዊ ተከታይ ሐዋርያዊ ስልጣናቸው በይፋ ከጀመሩበት ሰዓትና ቀን ጀምረው ያሰሙት ምዕዳን ብቻ ሳይሆን ገና በአርጀንቲና የቡዌኖስ አይረስ ሊቀ ጳጳሳትም እያሉ ያጸኑት እሴት መሆኑ የሚታወስ ሲሆን፣ ስለዚሁ ጉዳይ በተመለከተ በኢጣሊያ የምስልምና ሃይማኖት የባህል ማእከል ጠቅላይ ዋና ጸሓፊ ዶክተር አብደላ ረዱዋን ከቫቲካን ረዲዮ ጋር ባካሄዱት ቃለ ምልልስ፦ ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በቃልም ሆነ በተግባር በተለያዩ ሃይማኖቶች መካከል ውይይት ተገቢ ብቻ ሳይሆን ግዴታም ጭምር መሆኑ አረጋግጠዋል። የምስልምና ሃይማኖት ተከታዮችን ብቸኛው መኃሪው እግዚአብሔር የሚጸልዩ ናቸው በማለት የገለጡት ሃሳብ ጥልቅ ነው። ሁሉንም ደስ አሰኝተዋል። የእሳቸው ትህትና ለተለያዩ ሃይማኖት ተከታዮች አብነትና ሁሉም በእግዚአብሔር ፊት ሊኖረው የሚገባው ባህርይ ነው ብለዋል።
ሁሉም ሃይማኖቶች ሰላም ለመረጋገጥ በሚደረገው ጥረት ያላቸው አቢይ ኃላፊነት መቼም ቢሆን መዘንጋት እንደሌለበት ሁሉም ሰላም ለማረጋገጥ መተባበር መቀራረብና መተዋወቅ እንጂ አንዱ ሌላውን በማግለል ወይንም በማውገዝ ሃይማኖት የሰላም መሣሪያ የመሆን ባህርዩ መጻረር የለበትም። ይኽ ደግሞ ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በስፋት ገልጠውታል። ሁሉም አበይት ሃይማኖቶች በተለይ ደግሞ በአንድ እግዚአብሔር ኅላዌነት የሚያምኑት የክርስትና የምስልምናና የአይሁድ ሃይማኖት ሊከተሉት የሚገባቸው መንገድ ነው። ቅዱስነታቸውን ለሁሉም ሃይማኖቶች እጃቸውን ዘርግተው ያቀረቡት የመተባበር ጥሪ አወንታዊ ነው። ሁሉም ሃይማኖቶች በደስታና በአድናቆት የተመለከቱት ጥሪ ነው በመሆኑም ር.ሊ.ጳ. ፍራንቸስኮ በቃልና በግብር ያሳዩት ዝግጁትነት ሁሉም ሃይማኖቶች እንደ አብነት ሊከተሉት ይገባል ሲሉ የሰጡትን ቃለ ምልልስ እዚህ ላይ አጠቃለዋል።







All the contents on this site are copyrighted ©.